Get Mystery Box with random crypto!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለበዓለ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ! (ቀን ጥር 10 | Addis Ababa Education Bureau

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለበዓለ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!


(ቀን ጥር 10/2016 ዓ.ም) የጥምቀት በዓል ከሃይማኖታዊ እሴትነቱ ባሻገር ለማህበራዊ ትስስራችን መጎልበት ከፍተኛ ሚና ያለው ነው፡፡ በሀገራችን በአደባባይ ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል ከሀይምኖታዊ ስርዓቱ ባለፈ የሀገራችን ቱባ ባህላዊ ትእይንቶች ጎልተዉ የሚወጡበት ፣ ብሄር ብሄረሰቦች በአልበሳትና በብዝሃ ቋንቋቸዉ ደምቀዉ የሚታዩበት ፣ የኢትዮጵያዊነት ማሳያ የብዝኀነትና የአንድነት ነጸብራቅ በመሆን ያገለግላል፡፡


በጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶች ተጋምደው አንዱ የሌላው ውበትና ጉልበት ድምቀትና ሕይወት የሚሆኑበት ብቻ ሳይሆን የአለምን አይን በሙሉ የሚስብ ታላቅ በዓል ነዉ፡፡ ለዛም ነው የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ በማይዳሰሱ ቅርሶች በአለም ቅርስነት ተመዝግቦ በአለም አደባባይ ደምቀን እንድንታይ የሆነዉ።


በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ዘንድሮ ጥር 10 እና 11 ቀን የሚከበሩት የከተራ እና የጥምቀት በዓላት ከሃይማኖታዊ በዓልነት ባሻገር የሀገርን መልካም ገጽታን ከመገንባት እና የቱሪስት ፍሰትን ከማጎልበት አንጻር ጉልህ ሚና የሚጫወቱ በመሆኑ እንግዶችን በፍቅር ተቀብሎ በማስተናገድ በዓሉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ በተለይም ደግሞ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ከፀጥታ አካላት ጋር እጅና ጋንት በመሆኑ መስራት ይኖርባችዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ብዝኀ ማንነቶቻችን በማክበርና አንድነታችን በማጠናከር የጋራ ቤታችን የሆነችውን ሀገራችንን ለማልማትና ሰላሟን ለማስጠበቅ ሁላችንም በአንድነትና በመከባበር እንድንቆም በዚሁ አጋጣሚ መልእክቴን ለማስተላለፍ እወዳለሁ፡፡