Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት በ201 | Addis Ababa Education Bureau

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት በ2016 ዓ.ም 6 ወራት በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን ገመገመ፡፡

(ቀን ጥር 14/2016 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የቢሮውን ጨምሮ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ክላስተር ሱፐር ቫይዘሮችና የክፍለ ከተማ የዘርፉ አስተባባሪዎች የተሳተፉ ሲሆኑ በዳይሬክቶሬቱና በተመረጡ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ክላስተር ማዕከላት በ6 ወራት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዱዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት በሱፐርቪዥን ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ስርአተ ትምህርቱ በአግባቡ ተግባራዊ መሆኑንም ሆነ ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርትቤት ድረስ በትምህርት ዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው በዛሬው ውይይት በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን በአግባቡ በመገምገም በ2ኛ መንፈቅ አመት የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ አሰፋ በበኩላቸው የዛሬው መርሀ-ግብር በአማርኛና አፋን ኦሮሞ ዘርፎች ከቢሮ ጀምሮ በሁሉም ክላስተሮች በ6ወራት ውስጥ የተከናወኑ የሱፐር ቪዥን ተግባራትን በመገምገም በሂደት የታዩ ጠንካራና ደካማ አፈጻጸሞችን መሰረት በማድረግ በቀጣዩ የትግበራ ምዕራፍ የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑን ጠቁመው በውይይቱ በዳይሬክቶሬቱ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ከመቅረቡ ባሻገር በክፍል ውስጥ የተደረገ ሱፐርቪዥን ሪፖርት ቀርቦ ውይይት መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡