Get Mystery Box with random crypto!

ለመምህራን ተላልፈው በተለያዩ ምክንያቶች ውል ያልተፈጸመባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የማውጣት | Addis Ababa Education Bureau

ለመምህራን ተላልፈው በተለያዩ ምክንያቶች ውል ያልተፈጸመባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የማውጣት መርሀ ግብር ተካሄደ።

(ቀን መጋቢት 6/2016 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቅአለም ቶሎሳ እንዲሁም የካቢኔአባላት፣በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች እና መምህራን የተገኙ ሲሆን በ2009 ዓ.ም ለመምህራን ከተላለፉ 5000 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል በተለያዩ ምክንያቶች ውል ሳይፈጸምባቸው የቆዩ 435 ቤቶች በዛሬው እለት ፍትሀዊ በሆነ የዕጣ ማውጣት ስነስርአት ለቤት ፈላጊ መምህራን ተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ መርሀ ግብሩ እንዳስታወቁት ከተማ አስተዳደሩ የመምህርነት ሙያ ለትምህርት ልማት ስራው ውጤታማነት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን በመረዳት ለመምህራን የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ከነዚህ ድጋፎች መካከልም የትምህርት ዕድል በመስጠት፣የቤት ኪራይ አበል ቀደም ሲል ከነበረው ከፍ እንዲል መደረጉ፣ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉ እንዲሁም በ2009 ዓ.ም በኪራይ የተላለፈላቸውን የጋራ መኖሪያ ቤት በወቅቱ ዋጋ ወደ ግል እንዲያዘዋውሩ መደረጉ ከብዙ ድጋፎች መካከል ጥቂቶቹ መሆናቸውን አስታውቀዋል።