Get Mystery Box with random crypto!

ዶክተር ዘላለም አክለውም ቢሮው በየደረጃው ከሚገኙ የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር አመራሮች እና አ | Addis Ababa Education Bureau

ዶክተር ዘላለም አክለውም ቢሮው በየደረጃው ከሚገኙ የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር አመራሮች እና አባላት እንዲሁም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ባከናወናቸው የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ውል ያልተፈጸመባቸውን 435 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በመለየት ለዛሬው የዕጣ ማውጣት መርሀ ግብር ማብቃቱን ጠቁመው በዕጣው መካተት ያልቻሉ መምህራን በማህበር ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ህንጻ በመገንባት የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩንም አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አ ስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የዕጣ ማውጣት መርሀግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ከተማ አስተዳደሩ የመምህራንን ጨምሮ ቤት ፈላጊ የሆኑ የከተማውን ነዋሪዎች ጥያቄ ለመመለስ በተለያዩ አማራጮች ቤት በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው መምህራንም በቅርቡ በማህበር ተደራጅተው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ የቀረበላቸውን እድል በአግባቡ መጠቀም እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቅአለም ቶሎሳ ከተማ አስተዳደሩ የመምህራንን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ እያደረገ ለሚገኘው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበው በዛሬው ዕጣ እድለኛ መሆን ያልቻሉ መምህራን የቁጠባ ባህላቸውን በማሳደግ በማህበር ተደራጅተው የቤት ባለቤት መሆን እንደሚገባቸው አስረድተዋል።




መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/