Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ በበኩላቸው መምህራን በህብረት | Addis Ababa Education Bureau

የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ በበኩላቸው መምህራን በህብረት ስራ ማህበራት ተደራጅተው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ የትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ላደረጉት አስተዋፅዎና የከተማ አስተዳደሩ ለመምህራን ቅድሚያ በመስጠቱ ምስጋና አቅርበው መምህራኖችም የቁጠባ ባህላቸውን በማሳደግ የቤት ባለቤት የሚያደርጋቸውን ዕድል በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።



በመርሀግብሩ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና ከህብረት ስራ ኮሚሽን መምህራኑ በህብረት ስራ ማህበራቱ ለመደራጀት መከተል ስለሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችና እስካሁን የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን በተመለከተ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ በተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን ለተነሱ ጥያቆዎች የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዲሳ አራርሳ፣ የህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሉሊት ግደይ እንዲሁም በመምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት ድንቃለም ቶሎሳ እና በዶክተር ዘላለም ሙላቱ ምላሽ ተሰቷል።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/