Get Mystery Box with random crypto!

ቤት ፈላጊ መምህራን በህብረት ስራ ማህበራት በመደራጀት የጋራ መኖሪያ ህንጻ ገንብተው የቤት ባለቤት | Addis Ababa Education Bureau

ቤት ፈላጊ መምህራን በህብረት ስራ ማህበራት በመደራጀት የጋራ መኖሪያ ህንጻ ገንብተው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁ ተገለጸ።

(ቀን የካቲት 27/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከከተማው መምህራን ማህበር ጋር በጋራ በመሆን በጉዳዩ ዙሪያ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት ያካሄደ ሲሆን በውይይቱ የክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችን ጨምሮ ርዕሳነ መምህራን ፣ ከየትምህርት ቤቱ የመጡ የመሰረታዊ መምህራን ማህበር ሰብሳቢዎች እንዲሁም የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኮሚሽን አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ከተማ አስተዳደሩ መምህራን የቤት ባለቤት ሆነው ከተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ተላቀው ትውልድ የመገንባት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲከናወኑ መቆየቱን ገልጸው ትምህርት ቢሮ ቤት ፈላጊ መምህራን በህብረት ስራ ማህበራት ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ህንጻ ገንብተው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ከመምህራን ማህበር እንዲሁም ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና ከህብረት ስራ ኮሚሽን ጋር ሲያከናውን የቆየው ቅድመ ዝግጅት በመጠናቀቁ ከነገ ጀምሮ ወደ ተግባር እንደሚገባም አስታውቀዋል።