Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ ከተማ ክፍለከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት የ1ኛ መንፈቀ ዓመት ስራ አፈጻጸም ግምገማ | Addis Ababa Education Bureau

የአዲስ ከተማ ክፍለከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት የ1ኛ መንፈቀ ዓመት ስራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።


(ቀን የካቲት 21/2016 ዓ.ም) በመድረኩ የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት የ2016 ዓ.ም የ1ኛ ሴምስተር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የተማሪዎች ውጤት ትንተና እና የቀጣይ ትኩረት መስኮች ቀርበው ውይይት ተካሂዷል ።


በጽህፈት ቤቱ የመምህራን የሱፐርቪዥን እና የትምህርትቤት መሻሻል የስራዎች አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ቱጂ በመድረኩ በ2016 በ1ኛ መንፈቀ ዓመት የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በዚህም በ11ግቦች ስር የተከናወኑ የተለያዩ ተግራትን እና በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን አቅርበው ውይይት ተካሂዱዋል፡፡


የስርዓተ ትምህርት ክትትልና ትግበራ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ቤኩማ ደበሎ በበኩላቸው የተማሪዎችን ውጤት ትንተና በማቅረብ ውይይት ተደርጎበታል ፡፡