Get Mystery Box with random crypto!

በከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ በተካሄደው የትምህርት ቤት አመራሮች ውድድር አልፈው ለተመደቡ ርዕሳነ | Addis Ababa Education Bureau

በከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ በተካሄደው የትምህርት ቤት አመራሮች ውድድር አልፈው ለተመደቡ ርዕሳነ መምህራን ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።

(ቀን የካቲት 2/2016 ዓ.ም) ስልጠናውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ለተከታታይ ስድስት ቀናት እንዲሰጥ በማድረግ በዛሬው እለት ተጠናቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በስልጠናው ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርም ሆነ ስልጠናውን የሰጡ ምሁራን የትምህርት አመራሮቹ በየተመደቡባቸው ተቋማት ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል ግንዛቤ በመፍጠራቸው ምስጋና አቅርበው ርዕሳነ መምህራኑም በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀትም ሆነ ክህሎት መሰረት በማድረግ የተቋማቸውን ደረጃ ማሳደግና የተማሪዎቻቸውን ውጤትና ስነ-ምግባር ማሻሻል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒ ቨርሲቲ ምክትል ፕሬዘዳንት ዶክተር አብዱላዚዝ መሀመድ በበኩላቸው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ሴክተሩን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በጋራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ዩኒቨርሲቲው በቀጣይም ለትምህርት አመራሮችም ሆነ መምህራን ስልጠናዎችን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርግ አስረድተዋል።