Get Mystery Box with random crypto!

Wolaita Sodo University

የቴሌግራም ቻናል አርማ wolaitasuniversity — Wolaita Sodo University W
የቴሌግራም ቻናል አርማ wolaitasuniversity — Wolaita Sodo University
የሰርጥ አድራሻ: @wolaitasuniversity
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.27K
የሰርጥ መግለጫ

This is the official telegram channel of Wolaita Sodo University
Our Official Website :
http://www.wsu.edu.et/
Our Official Facebook page :
https://m.facebook.com/Wolaita-Sodo-University-246568056057804

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-24 18:14:29 በዩኒቨርሲቲው የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አስፈጻሚ መምህራን ከፈተና አሰጣጥ ሂደት ጋር የተያያዙ ሕገ-ደንቦችን በተመለከተ ገለጻ (Orientation) ተሰጠ።
_____________
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከሐምሌ 19 እስከ 28/2015 ዓ.ም በሚካሄደው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በአስፈጻሚነት ለተመደቡ ፈታኝ መምህራን ገለጻ (Orientation) ተሰጥቷል።

በመድረኩ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ፈተናውን ለማስፈጸም ወደ ዩኒቨርሲቲው ለተመደቡ ፈታኝ መምህራን አረንጓዴ፣ ጽዱ፣ ሠላማዊ፣ ሕብረ-ብሔራዊ እና ተወዳዳሪ ወደሆነው ተቋም እንኳን በደህና መጣችሁ ብለዋል።

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ መንግስት እየወሰደ ያለውን ቁርጠኛ አቋም እውን ለማድረግ መምህራን የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱ መሆኑን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ የፈተናው ሂደት ፍጹም ሠላማዊ፣ ከደንብ ጥሰት እና ከኩረጃ የጸዳ እንዲሆን ፈታኝ መምህራን ትልቅ ሀላፊነት እንዳለባቸው አሳውቀዋል።

እንደ ሀገር ከገባንበት የትምህርት ጥራት አዘቅት ለመውጣት ፈታኝ መምህራን የተጣለባቸውን ታላቅ ሀገራዊ ሀደራ በሚገባ በመወጣት ትውልድን ከኩረጃ እንዲሁም ከሥነ-ምግባር ዝቅጠት የመታደግ ተልዕኮን ኃላፊነት ወስደው እንዲያስፈጽሙ ፕሮፌሰር ታከለ ጥሪ አቅርበዋል።

በመድረኩ የፈታኝ መምህራን መብትና ግዴታ ምን እንደሆን እንዲሁም ለፈታኝ መምህራን የተከለከሉና የተፈቀዱ ነገሮችን በተመለከተ ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በመጡ የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ ተሰጥቷል።

ፈታኝ መምህራን ወደ መፈተኛ ክፍል እና አካባቢ ስልክ፣ ስማርት ስዓት፣ ማጂክ ብዕር፣ እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት እና ሌሎች ማንኛውንም ፎቶ፥ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን መያዝና መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ በገለጻው ተብራርቷል።

በተጨማሪም ፈታኝ መምህራን ማንኛውንም ዓይነት መጽሐፍት፣ መጽሔት እና ጋዜጣ በመፈተኛ ክፍል ይዞ መገኘት ሆነ መጠቀም የተከለከለ መሆኑ በመድረኩ ተጠቁሟል።

ፈታኝ መምህራን የፈተና ደንብ ጥሰትን የመከላከል ተግባር ላይ በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ጭምር ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

«የፈተና ኩረጃና ስርቆትን በጋራ እንከላከል! ትውልድ ይዳን!»

➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!

➤ ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063820159424

ቴሌግራም፡ https://t.me/WolaitaSUniversity

ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos

ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/

ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09

ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/

ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን
2.5K viewsWubishet Ermias, edited  15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 18:14:27
2.2K viewsWubishet Ermias, 15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 17:37:21 በዩኒቨርሲቲው ለተመደቡ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አስፈጻሚዎች ተቢው ገለጻ (Orientation) ተሰጠ።

በፈተና ወቅት የፈተና የስፈጻሚዎች መብትና ግዴታ እንዲሁም የተከለከሉና የተፈቀዱ ነገሮችን በተመለከተ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
_________
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከሐምሌ 19 እስከ 28/2015 ዓ.ም በሚካሄደው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በአስፈጻሚነት ለተመደቡ የፈተና ማዕከል ኃላፊ፣ የፈተና የጉድኝነት ማዕከል አአስተባባሪ፣ የፈተና ጣቢያ ኃላፊ እና ሱፐርቫይዘሮ ገለጻ (Orientation) ተሰጥቷል።

በመድረኩ የተፈታኞችና የፈተና አስፈጻሚዎች መብትና ግዴታ እንዲሁም አጠቃላይ የተከለከሉና የተፈቀዱ ነገሮችን በተመለከተ ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በመጡ የሥራ ኃላፊዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ማዕከል ኃላፊ፣ የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ፣ ጣቢያ ኃላፊ፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ ፈታኝ፣ የዓይነ ስውር ተፈታኝ አንባቢ፤ የፊተና ግብአቶች ቆጣሪ እና ሌሎች የፈተና ግበረ ኃይል አባላት ወደ መፈተኛ ክፍል እና አካባቢ ስልክ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር፣ እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት እና ሌሎች ማንኛውንም ፎቶ፥ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን መያዝና መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ በመድረኩ ተብራርቷል።

በፈተና አስፈጻሚነት የተመደበ ማንኛውም ፈታኝ፤ ሱፐርቫይዘርና የፈተና ግብአቶች አደራጅ ማንኛውንም ዓይነት መጽሐፍት፣ መጽሔት እና ጋዜጣ በመፈተኛ ክፍል ይዞ መገኘት ሆነ መጠቀም የተከለከለ መሆኑም ተመላክቷል።

ለፈተና ደህንነት መረጋጥጥ አጋዥ በሆኑ አካሄዶች እንዲሁም የደንብ ጥሰት መከላከልን በተመለከት ሠፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፤ ፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና ደንብ ጥሰትን የመከላከል ተግባር ላይ በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል፡፡

➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!

➤ ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063820159424

ቴሌግራም፡ https://t.me/WolaitaSUniversity

ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos

ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/

ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09

ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/

ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን
2.2K viewsWubishet Ermias, 14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 17:37:18
2.1K viewsWubishet Ermias, 14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 12:18:58 የማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች–የ2ኛ ቀን ቅበላ!!

በጥብቅ የፍተሻ ሥርዓት ማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች አሁንም በመግባት ላይ ይገኛሉ።

በዩኒቨርሲቲው ከሐምሌ 19 እስከ 21/2015 ዓ.ም በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 19 ሺሕ 324 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ይፈተናሉ።

ሐምሌ 18/2015 ዓ.ም ለተፈታኞች ፈተናውን በትመለከተ አጠቃላይ የሥነ ምግባር ደንብ ላይ ያተኮረ ገለጸ ይሰጣቸዋል።

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን በሚውስዱበት ጊዜ የፈተናውን ህግና ስርዓት እንዲያከብሩ በጥብቅ አሳስቧል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተናው ግልጋሎት ከሚሰጡ የፅህፈት መሳሪያዎች እርሳስ፣ ላጲስ፣ መቅረጫ እና ስክቢቶ ውጭ ወደ ፈተና ክፍል ይዞ መግባት ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን እንዲያውቁትም አሳስቧል።

ውድ የ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች እንኳን አረንጓዴ፣ ጽዱ፣ ሠላማዊ፣ ተወዳዳሪ እና ሕብረብሔራዊ ወደሆነው ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በደህና መጣችሁ።

የ12 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ቆይታችሁ ወደሚያበቃበትና አዲስ ሌላ የሕይወት ምዕራፍ ወደሚጀመርበት ጊዜ እንኳን አደረሳችሁ በማለት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

መልካም ፈተና

«የፈተና ኩረጃና ስርቆትን በጋራ እንከላከል! ትውልድ ይዳን!»

➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!

➤ ሐምሌ 16/2015 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063820159424

ቴሌግራም፡ https://t.me/WolaitaSUniversity

ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos

ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/

ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09

ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/

ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን
2.6K viewsWubishet Ermias, edited  09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 12:17:18
2.4K viewsWubishet Ermias, 09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 18:09:18
National Mock Exit Exam Session at Wolaita So University

The 3rd Day National Mock Exit Exam has been successfully done

Today, in its 3rd day, National Mock Exit Exam Prepared by Ministry of Education successfully delivered for all graduating students of Wolaita Sodo University.

Many thanks for the University ICT experts to their efforts to make it happen all as planned.

Having a good ICT infrastructure is the only means to be move forward exceptionally.

«Knowledge in Action!!»

Wolaita Sodo University!!

https://www.facebook.com/100063820159424/posts/pfbid0oxmg4csDSKnimzo1EyZvmmEc3G7oY4mEGcJV79LLM1oNu66Q6WK2uuJg5R2ngrM2l/?app=fblbl
1.9K views15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 17:19:16 #Remedial_Exam

የሪሜዲያል ሀገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና የሦስተኛ ቀን ውሎ

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች እየተሰጠ ያለው ሀገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና ሦስተኛ ቀኑን ይዟል።

ዛሬ ሰኔ 28/2015 ዓ.ም ዕለተ ረቡዕ በሁለቱም የተፈጥሮ እና ማሕበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎቹ የኬሚስትሪ እና የጄኦግራፊ ፈተና ተፈትነዋል።
_________

በዩኒቨርሲቲው ሦስተኛ ቀኑን በያዘው የሪሜድያል ሀገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና በሁለቱም የተፈጥሮ እና ማሕበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች የኬሚስትሪ እና የጄኦግራፊ ፈተና ተፈትነዋል።

ዛሬ በተሰጠው የኬሚስትሪ እና የጄኦግራፊ ፈተና በአጠቃላይ 5 ሺሕ 625 ተማሪዎች የተፈተኑ ሲሆን፤ ከጠቅላላ ተፈታኝ ተማሪዎች 3 ሺሕ 282 የተፈጥሮ እና 2 ሺሕ 374 የማሕበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ናቸው።

የፈተናው ሂደት ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ ያሳወቁ ሲሆን፤ የፕሮግራሙ ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ የፈተና ሂደት እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በዩኒቨርሲቲው የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም፤ ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተናውን ህጎች በማክበር እና ሥነ-ምግባር ተላብሰው እንዲፈተኑ ያሳሰቡ ሲሆን፤ በቀጣይ አመት መደበኛ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን መቀጠል የሚያስችላቸውን ማለፊያ ውጤት እንዲያስመዘግቡ መልካም ምኞታቸውንም ገልጸዋል።

የፈተናው ሂደት ሰኔ 28/2015 ዓ.ም ዕለተ ሐሙስ ከቀኑ 9 ሰዓት ሲቀጥል ለሁለቱም የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ፈተና የሚሰጥ መሆኑ ተመላክቷል።

➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!

➤ ሰኔ 28/2015 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063820159424

ቴሌግራም፡ https://t.me/WolaitaSUniversity

ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos

ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/

ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09

ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/

ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን
1.9K views14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 17:19:14
1.6K views14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 16:36:54 #Exit_Exam

# የ3ኛ_ቀን ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ሙከራ ፈተና/National Mock Exit Exam/ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ!!

በዩኒቨርሲቲው በትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በኦንላይን እየተሰጠ ያለው ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ሙከራ ፈተና ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።

ዛሬ ሰኔ 28/2015 ዓ.ም ዕለተ ረዕቡ ጠዋት እና ከሰዓት በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የሙከራ መልቀቂያ ፈተና 826 ተመራቂ ተማሪዎች ተፈትነዋል።

የሙከራ ፈተናው ዓላማ፦ ተፈታኝ ተማሪዎች የኮምፒውተር አጠቃቀም ክዕሎታቸውን እንዲያዳብሩ በማድረግ ከፈተና መተግበሪያ ሶፍትዌሩ ጋር እንዲለማመዱ ማድረግ፤ ለፈተናው ያላቸውን የዕውቀት እና የሥነ-ልቦና ዝግጁነት ማላቅ፤ ዋናውን የመውጫ ፈተና ስርዓት ቀድመው እንዲረዱት ማስቻል እንዲሁም የተቋሙን የኢንተርኔት አቅርቦት እና አማራጭ በጄኔሬተር የታገዘ የኤሌክትሪክ አቅም ለገምገም እንደሆነ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር አሳውቋል።

እስከ ሰኔ 29/ 2015 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በሚሰጠው ሀገር አቀፍ የሙከራ መልቀቂያ ፈተና (National Mock Exit Exam) በዩኒቨርሲቲው በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 3 ሺሕ 26 ተመራቂ ተማሪዎች እንዲሁም 7 ሺሕ 800 ያህል ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡ የ2015 ዓም ተመራቂ ተማሪዎች የሙከራ ፈተናውን የሚፈተኑ መሆኑን አስተዳደሩ ጠቁሟል።

የ3ኛ ቀን ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ሙከራ ፈተና በሚፈለገው ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ የፈተናው ሂደት በታቀደው አግባብ እንዲሳካ የድርሻቸውን ሚና ለተወጡ ፈተኞች፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ የአይ.ሲ.ቲ እና የኤሌክትሪክ ባለሙያዎች ላደረጉት አስተዋጽኦ አስተዳደሩ ልባዊ ምስጋና አቅርቧል።

ሰኔ 29/2015 ዓ.ም ጠዋት እና ከሰዓት የሙከራ ፈተና መርሃ ግብሩ ሲቀጥል በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞ 699 ያህል ተመራቂ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ የሚሰጠውን ብሔራዊ የሙከራ መልቀቂያ ፈተና ሚወስዱ መሆኑ ተመላክቷል።

➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!

➤ ሰኔ 28/2015 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063820159424

ቴሌግራም፡ https://t.me/WolaitaSUniversity

ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos

ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/

ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09

ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/

ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን
1.8K views13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ