2023-03-16 19:54:25
በዩኒቨርሲቲው የወላይትኛ ቋንቋ ሰዋሰው መጽሐፍ ተመረቀ። (ወሶዩ፤ መጋቢት 07/2015 ዓ.ም)
በታሪክ የመጀመሪያው የሆነና ደረጃውን የጠበቀ የወላይትኛ ቋንቋ ሰዋሰው መጽሐፍ ተመረቀ።
_______በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት፤ በማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ የታተመ መሆኑ በምረቃው ሥነ ስርዓት ተገልጿል።።
በመጽሐፉ ዝግጅት ከዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብ ኮሌጅ ከወላይትኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል 4 መምህራን እንዲሁም ከወላይታ ዞን የተውጣጡ ሁለት የቋንቋ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።
ከወላይትኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል አባል በመሆን መጽሀፉን በማዘጋጀት የተሳተፉት ወ/ሮ አየለች በመድረኩ እንደገለጹት፡ "ይህ የሰዋሰው መጽሐፍ በዓይነቱ የመጀመሪያ እና ደረጃውን ጠብቆ ለየት ባለ መልኩ የታተመ ነው" ብለዋል።
የመጽሐፉ ዝግጅት 3 ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑን የገለጹት መምህርት አየለች፤ ከ2012–2015 ዓ.ም ደረስ ባሉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት መጽሀፉን ለማዘጋጀት የጥናትና ምርምር ስራ ተሰርቷል ሲሉም ገልጸዋል።
ሥነ ቃላቱ በአጠቀላይ ከሕብረተሰቡ የተሰበሰቡ መሆኑን በመግለጽም፤ የሥራው ባለቤት የወላይታ ሕዝብ መሆኑን ተናግረዋል።
መጽሐፉ ሕዝብን በመጠየቅ እና በማወያየት መልሶ ሕዝብን እንዲያገለግል መዘጋጀቱን የገለጹት መምህርት አየለች፤ መጽሐፉ ለተማሪዎች፥ ለመምህራን እንዲሁም ለመላው ሕዝብ ጥቅም ይውላል ሲሉ አሳውቀዋል።
የወላይትኛ ቋንቋ ራሱን የቻለ የአጻጻፍ ይትብሃል አለው ያሉት መምህርቷ፤ በቋንቋው በዘፈቀደ አይጻፍም በማለትም ቋንቋው "ደረጃውን የጠበቀ" እንዲሆን በቀጣይ ሰፊ ስራ ለመስራት እቅድ ተይዟል ብለዋል።
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ መምህር እና ተመራማሪ እንዲሁም የመጽሐፉ አርታኢ የሆኑት ዶክተር ፍሬው ደጀኔ በበኩላቸው፡ ቋንቋውን የበለጠ በማሳደግ ረገድ ከሁላችን የጋራ ርብርብ ይጠበቃል በማለት ተናግረዋል።
በዩኒቨርሲቲው ምሁራን ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ይህ የወላይትኛ ቋንቋ ሰዋሰው መጽሐፍም በታሪክ የመጀመሪው በመሆን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የታተመ መጽሐፍ መሆኑን ጠቁመዋል።
ወላይትኛ "የጽሑፍ ቋንቋ" የሆነው በ1916 ዓ.ም መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ፍሬው፤ ቋንቋው በሚፈለገው ልክ አላደገም፥ እስከአሁን የሥራ ቋንቋም አልሆነም ብለዋል። የመጽሐፉ መዘጋጀት ከማጣቀሻነት ባለፈ ለጥናትና ምርምር እንዲሁም በሂደት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እንደሚኖረው በመጠቆም።
መጽሐፉ ደረጃውን ጠብቆ በጥራት የተዘጋጀ የመጀመሪያው «የወላይትኛ ቋንቋ ሰዋሰው መጽሐፍ» መሆኑን አርታኢው ተናግረው፤ መጽሐፉ በሚገባ ተገምግሞ ተገቢው እውቅና የተሰጠውና ለህዝብ አገልግሎት ጥቅም ላይ እንዲውል ይሁኝታ ማግኘቱን ገልጸዋል።
በመድረኩ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተወካይና የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ዴአ፡ መጽሐፉ በቋንቋ ባለሙያዎች መዘጋጀቱ ለቋንቋውን ዕድገት እና ለቋንቋው ባለቤት ህዝብ እጅግ ከፍተኛ ፋይዳ አለው፥ የዘርፉን የቋንቋ ዕድገትም አንድ እርምጃ ከፍ ያደርገዋል ብለዋል።
መጽሐፉ በዛሬው ዕለት መመረቁን እና ለንባብ መብቃቱን በተቋሙ እና በራሴ ስም አበስራለሁ ያሉት ዶ/ር ሙላቱ፤ ከዚህ በኋላም ለመሰል የህትመት ስራዎች እናበረታታለን ሲሉም አሳውቀዋል።
የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ማሕበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር መስፍን ቢቢሶ በበኩላቸው፡ ለባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክ እና ቅርስ ዕድገት በምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ሰፊ ስራዎች የተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ከቋንቋ እድገት አንጻር የወላይትኛ ቋንቋ ሰዋሰው መጽሐፍ ድጋፍ የተደረገለት የመጀመሪያው የመጽሐፍ ህትመት አለመሆኑን ምክትል ፕሬዝዳንቱ ጠቁመው፤ ከዚህ ቀደም ለተለያዩ የመጽሐፍ ሕትመቶች መሰል ድጋፍ መደረጉንም አሳውቀዋል።
መሰል ሕዝብን የሚጠቅሙ፥ ዘላቂ ለውጥ የሚያመጡና ፋይዳ ያላቸውን ፕሮጀክቶች በቀጣይ ጊዜያትም በገንዘብ እና በቁስ እና በሀሳብ እንደግፋለን በማለት ዶ/ር መስፍን ተናግረዋል።
ለመጽሐፉ አዘጋጆች እና ለቋንቋው አርታኢያን ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የምስጋና ምስክር ወረቀት በመድረኩ ተበርክቶላቸዋል።
በዛሬው ዕለት የተመረቀው ባለ 192 ገጽ «የወላይትኛ ቋንቋ ሰዋሰው መጽሐፍ» ለንባብ መብቃቱ በመጽሐፉ የምረቃ ሥነ-ስርዓት ተመላክቷል።
➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!
➤ መጋቢት 07/2015 ዓ.ም
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስWolaita Sodo Universityty4/
ቴሌግራም፡https://t.me/WolaitaSUniversity
ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos
ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/
ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09
ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/
ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን
2.6K views16:54