2023-03-05 18:21:39
ለመውጫ ፈተና (Exit Exam) እየተካሄደ ያለው የቅድመ ዝግጅት ተግባር አፈጻጸም ከትምህርት ሚኒስትር በመጡ ግብረ-ኃይል አባላት ተገምግሟል።
የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርም «አንድም ተማሪ በመውጫ ፈተና (Exit Exam) ምክንያት መውደቅ የለበትም» በሚል አቋም እየሰራ መሆኑን አሳወቋል።
___
ለመውጫ ፈተናው እየተካሄደ ያለው የቅድመ ዝግጅት ተግባር ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ በተካሄደ የግምገማ መድረክ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅማንት አባላት፣ የኮሌጅ እና የትምህርት ቤት ዲኖች ተሳትፈዋል።
በመድረኩ ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የቅድመ ዝግጅት ሥራው በታቀደው አግባብ እና በተቀናጀ መልኩ ተግባራዊ እየሆነ መምጣቱ ተብራርቷል።
ዩኒቨርሲቲው “አንድም ተማሪ በመውጫ ፈተና ምክንያት መውደቅ የለበትም” የሚል አቋም ይዞ የቅድመ ዝግጅት ስራውን በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰራት እየሰራ መሆኑን አሳውቋል።
መውጫ ፈተናው በኦንላይን እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ባሳወቀው መሰረት በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች አዲስ የለማ መተግበሪያ ሶፍትዌር በፈተናው ወቅት ጥቅም ላይ እንዲውል መዘጋጀቱም ተጠቁሟል።
መውጫ ፈተናው የሚወስዱ ተማሪዎች በየጊዜው የመውጫ ፈተናን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ እንዲሰጣቸው በማድረግ ተገቢው የሥነ ልቦና እና የዕውቀት ዝግጅት እንዲኖራቸው መደረጉም ተመላክቷል።
የአይሲቲ መሠረተ ልማት ዝርጋታ፣የሞጁል
እና የሞዴል ፈተና አደረጃጀት እንዲሁም ተማሪዎችን በአእምሮና በስነ ልቦና ከማዘጋጀት አንፃር የተከናወኑት ስራዎች አበረታች በመሆን በግብረ ኃይሉ በጥንካሬ ተገምግሟል።
ለተመራቂ ተማሪዎች ግንዛቤ በመፍጠር በእውቀት፥ በክህሎት፣ በአመለካከት እና በስነ ልቦና ዝግጁ እንዲሆኑ እየተሰራ ያለው ተግባር የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ግብረ ኃይሉ አቅጣጫ አስቀምጧል።
የዩኒቨርሲቲው የመውጫ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ዕቅድ አፈጻጸም አሁን ያለበት ደረጃ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበለጠ ቅንጅት እና ትብብር አስፈላጊ መሆኑን ግብረ ኃይል አባላቱ አመላክተዋል።
መውጫ ፈተናው ተማሪዎች በተማሩበት የትምህርት መስክ የሚፈለግባቸውን ክህሎት ማግኘታቸውን የሚለካ በመሆኑ ተፈታኞች ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል በማለት አስተያየት ሰጥተዋል።
የዩኒቨርሲቲው ማናጅመንት፣ የኮሌጅ እና የትምህርት ቤት ዲኖች ከግብረ-ኃይል አባላት ጋር በመሆን የአይ.ሲ.ቲ ላብራቶሪዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ቤተ-መጻሕፍቶችን፣ የማንበቢያ ክፍሎችን እንዲሁም ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
══════════════════
The implementation of the preparatory work for the Exit Exam was evaluated by the task force members from the Ministry of Education.
The administration of the university announced that "no student should fail due to the exit exam".
___
Members of the university management, college and school deans participated in an evaluation forum on the status of the preparation for the exit exam.
According to the direction set by the Ministry of Education, it was explained that the preparatory work is being implemented in the planned and in a coordinated manner.
The university has stated that "no student should fail due to the exit exam" and is doing the preparatory work according to the standards.
According to the Ministry of Education's announcement that the exit exam will be offered online, a new application software to be used during the exam has been developed by the university's technologists.
It was also pointed out that the students taking the exit exam should be regularly informed about the exit exam so that they have the appropriate psychological and knowledge preparation.
ICT infrastructure development;the organization of the module and model test as well as the motivational work done in terms of preparing students intellectually and psychologically was strongly evaluated by the task force.
The task force has set a direction that the work being done to create awareness for graduate students in terms of knowledge, skills, attitudes and psychology should be strengthened.
The members of the task force pointed out that more coordination and cooperation is necessary to strengthen the implementation of the university's exit exam preparation plan.
The task force finally said that the exit exam measures whether students have acquired the required skills in the field of study, so the examinees should prepare themselves properly.
The university management, college and school deans along with the task force members visited the ICT laboratories, electronic libraries, reading rooms and other preparatory works.
1.4K viewsedited 15:21