2023-06-06 19:42:41
#ጉብኝት-3( የአረንጓዴ አሻራ ልማት ሥራዎች)
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር «ውጤታማ ተግባቦት ለኢትዮጵያ ልዕልና» በሚል ርዕሰ ጉዳይ ያዘጋጀውን ስልጠና ለመሳተፍ ከ 47 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና ተጠሪ ተቋማት የመጡ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች በዩኒቨርሲቲው እስካሁን የተከናወኑ እና ቀጣይ ለሚካሄደው ሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
እንደ ተቋም ባለፉት አራት ዓመታት በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን የደን እና የሚበሉ የፍራፍሬ ችግኞችን በራሱ «ችግኝ ጣቢያ» አፍልቶ የመትከል እንዲሁም ለተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እና ተቋማት ተደራሽ ሲያደርግ መቆየቱን በዩኒቨርሲቲው የአረንጓዴ አሻራ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት መ/ር ገለታው ከበደ ለጎብኝቱ ተሳታፊዎች አሳውቀዋል።
ዩኒቨርሲቲው ለሚበሉ የፍራፍሬ ዝርያዎች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል በማለት ለጎብኝዎች ገላጻ ያደረጉት ዳይሬክተሩ፤ ተቋሙ ባቋቋመው ችግኝ ጣቢያ ከሚፈሉ ችግኞች አብዛኞቹ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬ ዝርያዎች እንዲሆኑ ጠቁመዋል።
በ2014 ዓም በዩኒቨርሲቲው በተካሄደ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በአንድ ጀምበር የደቡብ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት 10 ሺሕ የተዳቀለ ምርጥ የአቦካዶ ችግኝ ዝርያ መተከሉንም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። ይህን ተሞክሮ በመቀመር ለሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ተገቢው ዝግጅት መደረጉን በመጠቆም
በሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ሙሉ በሙሉ የሚበላ የፍራፍሬ ችችግኞችን ማዕከል ያደረገ እንዲሆን አቅጣጫ መቀመጡን የገለጹት መምህር ገለታው፤ ከመጀመሪያው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ ትግበራ በተሻለ መልኩ በሁለተኛው ምዕራፍ በጥራት፣ በእውቀትና በቴክኖሎጂ የታገዘ ትግበራ እንዲኖር ሰፊ ዝግጅት መደረጉንም ለጎብኝዎች አብራርተዋል።
በዘንድሮው ዓመት ለሚጀመረው የሁለተኛው ምዕራፍ 5ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዩኒቨርስቲው ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸውን 330 ሺሕ ምርጥ የአቦካዶ ችግኝ ዝርያዎችን በማፍላት ዩኒቨርሲቲው ሙሉ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀም ዳይሬክተሩ አሳውቀዋል።
ለተከላ ከተዘጋጁ የአቦካዶ ችግኝ ዝርያዎች 40,000 ያህሉን ሙሉ በሙሉ የማዳቀል (graft) የማድረግ ስራ የተከናወነ መሆኑን ለጎብኝዎቹ አሳውቀዋል።
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በገንደባ ካምፓስ የሚገኘውን የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ(ዶ/ር) ፓርክ ጨምሮ ከዚህ ቀደም ተተክለው የጸደቁ ችግኞችን እና ለሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ የተዘጋጁ ችግኞችን ተዟዙረው ምልከታ አካሂደዋል።
የየዓመቱ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዕቅድ እና አፈጻጸም መረጃ
➧ በ2011 ለመትከል የታቀደው 80 ሺህ ችግኝ ሲሆን፣ በድምሩ 100 ሺህ የደን ችግኝ ተተክሏል፣
➧ በ2012 ለመትከል የታቀደው 120 ሺህ ችግኝ ሲሆን ከዚህም ውስጥ፦
የፍራፍሬ ችግኝ 20,000
የደን ችግኝ 130,000
በድምሩ 150,000 ችግኝ ተተክሏል፣
➧ በ2013 ለመትከል የታቀደው 500,000 ችግኝ ሲሆን፣
የፍራፍሬ ችግኝ 200,000፣
የደን ችግኝ 100,000፣
በድምሩ 300,000 ችግኝ ተተክሏል፣
➧ በ2014 ለመትከል የታቀደው ዕቅድ 550,000 ችግኝ ሲሆን፣
የፍራፍሬ ችግኝ 300,000፣
የደን ችግኝ 250,000፣
በድምሩ 550,000 ችግኝ በዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች እና በአካባቢው ተተክሏል።( ለተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ተደራሽ ሆኗል)
➧ በ2015 ሁለተኛው ምዕራፍ 5ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርር 330,000 የአቦካዶ ችግኝ ለመትከል እንዲሁም ለተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን ከዩኒቨርሲቲው አረንጓዴ አሻራ ልማት ዳይሬክቶሬት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!
➤ ግንቦት 29/2015 ዓ.ም
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063820159424
ቴሌግራም፡ https://t.me/WolaitaSUniversity
ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos
ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/
ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09
ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/
ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን
129 viewsedited 16:42