Get Mystery Box with random crypto!

Wolaita Sodo University

የቴሌግራም ቻናል አርማ wolaitasuniversity — Wolaita Sodo University W
የቴሌግራም ቻናል አርማ wolaitasuniversity — Wolaita Sodo University
የሰርጥ አድራሻ: @wolaitasuniversity
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.46K
የሰርጥ መግለጫ

This is the official telegram channel of Wolaita Sodo University
Our Official Website :
http://www.wsu.edu.et/
Our Official Facebook page :
https://m.facebook.com/Wolaita-Sodo-University-246568056057804

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-02-09 19:28:38 ዩኒቨርሲቲው በጀርመን ሀገር ከሚገኘው ከሳሃይ ሶላር (Sahay Solar) ኢንስቲትዩት ጋር በአጋርነት ሊሰራ መሆኑ ተገለጸ።

ኢንስቲትዩቱ የፀሐይን ሀይል በመጠቀም በፀሃይ እና በታዳሽ ሃይል ልማት ላይ በስፋት የሚሰራ መሆኑ ተመላክቷል።
_______
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በጀርመን ሀገር ከሚገኘው ከሳሃይ ሶላር ኢንስቲትዩት (Sahay Solar) ጋር በፀሃይ እና በታዳሽ ሃይል ልማት ዘርፍ በአጋርነት የትብብር ማዕቀፍ ለመስራት እእንቅስቃሴ መጀመሩን የዩኒቨርሲቲው ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አሳውቋል።

የፀሐይን ሀይል በመጠቀም የህብረተሰቡን የሐይል አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ ከኢንስቲትዩቱ ጋር የተለያዩ ተግባራትን በአጋርነትና በትብብር በጋራ ለመስራት በሚያስችል ጉዳዮች ላይ ውይይት መካሄዱንም ዳይሬክቶሬቱ ገልጿል።

በፕሮጀክቱ አተገባበር ላይ በማተኮር በተካሄደው አውደ ምክክር የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከሳሃይ ሶላር (Sahay Solar) ኢንስቲትዩት ከመጡ አካላት መክረዋል።

በውይይት መድረኩ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተወካይና የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብርሃም ቦሻ በአጋርነትና በትብብር ማዕቀፍ የህብረተሰቡን ችግር በቅርበት መቅረፍ የሚያስችሉ ተግባራትን ለመሥራት ዩኒቨርሲቲው ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ዶ/ር አብርሃም አክለውም ኢትዮጵያ ሞቃታማ ሀገር በመሆኗ ከፀሐይ ሀይል የሚገኘውን ኢኔርጂ ለበርካታ ተግባራት ማዋል ስለሚቻል ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ለማድረግ ዩኒቨርሲቲው ጉልህ ሚና እንደሚጫወት አሳውቀዋል፡፡

በውይይቱ የተሳተጉት የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር መስፍን ቢቢሶ ዩኒቨርሲቲው ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው ዘርፎች አንዱ በፀሃይ እና በታዳሽ ሃይል ልማት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

በኃይል አቅርቦት እጥረት ምክንያት የሚከሰቱ ችግሮችን በተጨባጭ ለመቅረፍ ከተቋሙ ጋር በትብብር መስራት ተገቢ መሆኑንም ምክትል ፕሬዝዳንቱ አሳውቀዋል።

በውል ስምምነት ውስጥ ሊካተቱ የሚችሉ ተግባራትን በጋራ በመለየት፣ በመወያየትና በማጎልበት ሁለቱ ተቋማት ተጠቃሚ በሚሆኑበት ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት እንሰራለን ሲሉም ተናግረዋል።

በኢንጂነሪንግ ኮሌጅ በኤሌክትሪካል እና ኮምፒውተር ምህንድስና ትምህርት ክፍል ለሚገኙ መምህራን እና ተማሪዎች የአጭር ጊዜ የተግባር ስልጠና መስጠት፤ የላቦራቶሪ ቴክኒሻኖችን በማሰልጠን ላብራቶሪዎችን ማደራጀት እንዲሁም የፀሃይ ሃይልን በማምረት በገጠር የሚገኙ የጤናና የግብርና ዘርፎችን መደገፍ የፕሮጀክቱ የወደፊት የትብብር መስኮችን መሆናቸው በውይይቱ ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ በዩኒቨርሲቲው ኢንጂነርንግ ኮሌጅ በኢንጂነሪንግ ኮሌጅ በኤሌክትሪካል እና ኮምፒውተር ምህንድስና ትምህርት ክፍል ጋር በትብብር ተፈጻሚ እንደሚሆን በውይይቱ ተመላክቷል፡፡

ሳሃይ ሶላር (Sahay Solar)ኢንስቲትዩት በፀሃይ እና በታዳሽ ሃይል መስክ ልምድ ያላቸው የጀርመን እና የስዊዘርላንድ መሐንዲሶች፣ መምህራን እና የልማት ባለሙያዎች ማህበር ነው።

➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!

➤ የካቲት 02/2015 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/Wolaita-Sodo-University-246568056057804/

ቴሌግራም፡https://t.me/WolaitaSUniversity

ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos

ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/

ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09

ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/

ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን
657 views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 19:28:34
538 views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 19:27:35 ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የ10ኛነት ደረጃ ማግኘቱ ተገለጸ።
_______
"Webometrics Ranking of World Universities" የተሰኘ የበይነ መረብ ትስስር ገጽ በዓለም አቀፍ፣ በአፍሪካ እና በኢትዮጵያ የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን (ዩኒቨርሲቲዎችን) በተለያዩ መስፈርቶች በማወዳደር ደረጃ/Rank በማውጣት ይታወቃል።

ድህረ ገጹ በጥር ወር 2023 ዓ.ም (January 2023) ባወጣው መረጃ በዓለም፥ በአፍሪካ እንዲሁም በኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲዎችን ደረጃ ይፋ አድርጓል።

በዩኒቨርሲቲዎች የደረጃ ምደባ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፦ ከኢትዩጵያ 10ኛ፤ ከአፍሪካ ፣252ኛ እንዲሁም ከዓለም 5063ኛ ደረጃ ያገኘ መሆኑን ድህረ ገጹ አሳውቋል።

"Webometrics Ranking of World Universities" የበይነ መረብ ትስስር ገጽ ለዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የደረጃ አሰጣጥ እ.አ.አ በ2004 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን፤ ይህኛው የደረጃ አሰጣጥ 20ኛው መሆኑ ተጠቁሟል።

"ደረጃ ድረ-ገጽ" የዩኒቨርሲቲዎች ድረ-ገጾች ደረጃ ሳይሆን የዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ድህረ ገጹ ሁለቱንም ዌቦሜትሪክ (ሁሉንም የተቋም ተልዕኮዎች) እና ቢቢሊዮሜትሪክ (የምርምር ተልዕኮ) አመላካቾችን ለደረጃ ፍረጃ ይጠቀማል።

እንኳን ደስ አለን Congratulations!!

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከአለም፥ ከአፍሪካ እና ከኢትዮጵያ ያገኘውን ደረጃ ለመመልከት ከታች ባለው ሊንክ ይመልከቱ።
https://www.webometrics.info/en/Africa/Ethiopia

➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!

➤ ጥር 28/2015 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/Wolaita-Sodo-University-246568056057804/

ቴሌግራም፡https://t.me/WolaitaSUniversity

ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos

ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/

ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09

ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/

ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን
637 viewsedited  16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 19:27:23
620 views16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 19:38:54 በዩኒቨርሲቲው “የሀገር በቀል ዕውቀቶች/ተቋማት ሚና በኢትዮጵያ እያቆጠቆጠ ያለውን የዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦች በማቀራረብ ረገድ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት ተካሄደ።

ግጭቶችን በመቀነስ ሀገራዊ መግባባትን ለማስፈን “ሀገር በቀል ዕውቀት” አይነተኛ ሚና እንዳለው በውይይት መድረኩ ተመላክቷል፡፡
_______
በዩኒቨርሲቲው “የሀገር በቀል ዕውቀቶች/ተቋማት ሚና በኢትዮጵያ እያቆጠቆጠ ያለውን የዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦች በማቀራረብ ረገድ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ ዩኒቨርሲቲው ተወዳዳሪ፣ አረንጓዴ፣ ጽዱ እና ሰላማዊ መሆኑን ገልጸው፤ ህብረ ብሔራዊነትን አጉልቶ የሚያስተናግድ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ሀገር በቀል ዕውቀት ለሀገር ሁለንተናዊ የዕድገት ጉዞ የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ በዚሁ ረገድ በዩኒቨርሲቲው ሰፋ ያለ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር እየተካሄደ መሆኑንም አሳውቀዋል።

ታሪክን በመመርመር ለበጎ አላማ ማዋል ለሀገር ዕድገት አዎንታዊ ሚና እንዳለው ፕ/ር ታከለ ጠቁመው፤ መሰል የውይይት መድረክ ለሀገራዊ መግባባት አስተዋጽዖ የሚያበረክቱ ዜጎችን ለማፍራት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።

በመድረኩ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር መስፍን ቢቢሶ በበኩላቸው፤ ታሪክንና ሀገር በቀል ዕውቀትን ከትውልድ ወደ ትውልድ በማሸጋገር ረገድ ምሁራን ከፍተኛ ሀላፊነት እንዳለበቸው ተናግረዋል።

የሀገርን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማፋጠንና ለማዝለቅ በጥልቅ ጥናት ላይ በመመስረት ታሪክን እና ሀገር በቀል ዕውቀትን መመርመር ተገቢ መሆኑንም ምክትል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

የምክክር መድረኩ አገራዊ ችግሮችን በሀገርኛ ዘይቤ ለመፍታታት ጉልህ ፋይዳ ስላለው ተሳታፊዎች በተገቢው እንዲከታተሉ አሳስበዋል።

በመድረኩ “የዋልታ ረገጥ አስተሳሰብ ምንነት፣ ምክንያቶት፣ ውጤትና በዲሞከራሲ ግንባታ ላይ ያለው ተፅዕኖ”፤ “የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል እና ዲሞክራሲያዊ ሽግግር፤
“የታሪከ ሚና ለብሄራዊ መግባባት”፤ እና “የሀገር በቀል ዕውቀት/ተቋማት ሚና የዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦችን በማቀራረብ ረገድ” የውይይት ሀሳቦች በመሆን ቀርቧል።

“የዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦችን በማቀራረብ ረገድ የሀገር በቀል ዕውቀት/ተቋማት ሚና ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጥናታዊ ጽሑፍ በዩኒቨርሲቲው የታሪክ፣ ባህልና ቅርስ መምህርና ተመራማሪ በሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር አበሻ ሽርኮ ቀርቧል፡፡

በጥናታዊ ጽሑፉ፦የፖለቲካ ዋልታ ረገጥነት ምንነት፣ መንስዔዎች፣ በሀገር ዕድገት ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ጫና እና መፍትሔዎቹ የሚሉ ሀሳቦች ተመላክቷል።

በውይይት መድረኩ በአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ የተገኙ ሲሆን፤ “የታሪከ ሚና ለብሄራዊ መግባባት” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል፡፡

ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር ባህሩ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ እንደ ሀገር በኢትዮጵያ ከሚያለያዩ ነገሮች ይልቅ የሚያግባቡና የሚያቀራርቡ ነገሮች በርካታ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የቀደመውን ዘመንና የአሁኑን ታሪክ ማወቅ ለሀገር መግባባት የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ከፍተኛ መሆኑንም ተመራማሪው አብራርተዋል።

ታሪክን ማወቅና የሀገር በቀል ዕውቀቶችን መጠቀም የፖለቲካ ዋልታ ረገጥነትን ለማክሰም ብሎም ለአንድ ሀገር ዕድገት ወሳኝ መሆኑ በውይይቱ ተሳታፊዎች በስፋት ተመክሮበታል፡፡

የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ከማሕበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው የምክክር መድረክ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና የተለያዩ የማህበረሰብ ተወካዮች የተሳተፉ መሆኑ ተመላክቷል።

➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!

➤ ጥር 30/2015 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/Wolaita-Sodo-University-246568056057804/

ቴሌግራም፡https://t.me/WolaitaSUniversity

ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos

ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/

ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09

ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/

ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን
894 views16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 19:38:50
786 views16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 18:07:53 በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ (ገንደባ ካምፓስ) ስለሚገኘው የወላይታ ብሔር ባሕላዊ ሙዚየም እነሆ በጥቂቱ

➤ ሙዚየሙ «ቅርስ ያለው ታሪክ አለው» በሚል መርህ በ2012 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ተመሠረተ።

➤ ሙዚየሙ በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ገንዳባ ካምፓስ የሚገኝ ሲሆን፤ በሀገር በቀል ዕውቀት ተቋም ዳይሬክቶሬት ይተዳደራል።

➤ ሙዚየሙ በወላይታ ብሔር ባህላዊ የጎጆ ቤት ቅርጽ የተሰራ ሲሆን፤ የብሔሩን ታሪክ እና ባህል እንዲገልጽ ተደርጎ የተደራጀ ነው።

➤ ሙዚየሙ ከ300 የሚበልጡ የተለያዩ ባህላዊ እና ታሪካዊ ይዘት ያላቸው ቅርሶች አደራጅቶ ይዟል።

➤ ሙዚየሙ የወላይታን ቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክና ቅርስ መጠበቅ፣ ማሳደግና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ተቀዳሚ ዓላማው ነው።

➤ በሙዚየሙ የተደራጁት ባህላዊ እና ታሪካዊ የቅርስ ሀብቶች ለተግባራዊ መማር ማስተማር፥ ለጥናትና ምርምር፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግርና ስርጸት፣ ለስልጠና እንዲሁም ቀጣይነት ላለው የቱሪዝም ዕድገት ጉልህ ፋይዳ አላቸው።

➤ ሙዚየሙ በቋንቋው፣ በታሪኩ እና በቅርሱ የሚኮራ እና ማንነቱን የሚገልጽ ትውልድ ለመቅረጽ የላቀ ጠቀሜታ አለው።

➤ ሙዚየሙን የአካባቢውን ማህበረሰብ ጨምሮ ከ35 ሺሕ የሚበልጡ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ዜጎች ጎብኝተውታል፡፡

➤ ሙዚየሙ በሚገኝበት ስፍራ የተለያዩ የወላይታ ባህላዊ የቅመማ ቅመም ዝርያዎችን (ናቲራ፣ ጣሎቲያ፣ አጉፒያ፣ ሞርዳሊያ፣ ደቡዋ፣ ከፑዋ፣ ጉጨቻ...) አካቶ ይዟል።

➤ ሙዚየሙን በተለያዩ ቅርሶች የበለጠ ለማበልፀግ ተጨማሪ ባሕላዊ እና ታሪካዊ ቅርሶችን የማሰባሰብና የማደራጀት ተግባር አፅንዖት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው።

➤ ሙዚየሙ ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጧቱ 2:00 እስከ ምሽቱ 1:00 ድረስ እንዲሁም ዕለተ እሁድ ከቀኑ 8:00 እስከ 12:00 ለጉብኝት ክፍት ነው።

➤ ይምጡ ይጎብኙ–ብዙ አትርፈው፤ ተደስተው ይመለሳሉ!!

➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!

➤ ጥር 30/2015 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/Wolaita-Sodo-University-246568056057804/

ቴሌግራም፡https://t.me/WolaitaSUniversity

ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos

ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/

ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09

ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/

ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን
1.1K views15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 18:07:50
895 views15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 18:06:59 በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ ምረቃ የሚሰጡ የትምህርት መርሃ ግብሮችን ያውቁ ኖሯል!?

በ2022 ዓ.ም «ቴክኖሎጂ መር የግብርና እና የጤና ልዕቀት ማዕከል» ለመሆን ራዕይ የሰነቀው ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ 62 ያህል የቅድመ ምረቃ የትምህርት መርሃ ግብሮች ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል። አሁንም አዲስ ገቢ (የ2014 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግብያ ፈተና ወስደው ማለፍያ
ውጤት ያመጡ) ተማርዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል።

እነሆ! በዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የቅድመ ምረቃ (የመጀመሪያ ድግሪ) የትምህርት መርሃ ግብሮች የሚሰጡ የትምህርት መርሃ ግብሮችን ከታች ይመልከቱ

በጤና እና ሕክምና ኮሌጅ በቅድመ ምረቃ የሚሰጡ የትምህርት መርሃ ግብሮች (12)

1. Medicine

2. Public Health

3. Anesthesia

4. Neonatal Nursing

5. Operation Theatre Nursing

6. Emergency & Critical Care Nursing

7. Pediatrics And Child Health Nursing

8. Surgical Nursing

9. Midwifery

10. Nursing

11. Pharmacy

12. Medical Laboratory Science

በግብርና ኮሌጅ በቅድመ ምረቃ የሚሰጡ የትምህርት መርሃ ግብሮች (07)

1. Natural Resource Management

2. Animal and Range Science

3. Plant Science

4. Agri-business and value chain

4. management

5. Horticulture

6. Agro-Economics

7. Rural Development and Agricultural Extension

በተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በቅድመ ምረቃ የሚሰጡ የትምህርት መርሃ ግብሮች (09)

1. Biology

2. Biotechnology

3. Chemistry

4. Environmental Science

5. Geology

6. Mathematics

7. Physics

8. Sport Sciences

9. Statistics

በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በቅድመ ምረቃ የሚሰጡ የትምህርት መርሃ ግብሮች (06)፡

1. Economics

2. Management

3. Accounting and Finance

4. Public Administration & Development Management

5. Marketing and Sales

6. Hoteling and Tourism

በኢንጂነሪንግ ኮሌጅ በቅድመ ምረቃ የሚሰጡ የትምህርት መርሃ ግብሮች (06)

1. Architecture Engineering

2. Civil Engineering

3. Construction Technology
Management Eng.

4. Electrical and Computer Engineering

5. Hydraulic and Water Resource Engineering

6. Mechanical Engineering

በማሕበራዊ ሳይንስ እና ስነ ሰብ ኮሌጅ በቅድመ ምረቃ የሚሰጡ የትምህርት መርሃ ግብሮች (12)

1. Geographic & environmental Studies

2. Archeology& Heritage Management

3. English Language and Literature

4. Amharic Language and Literature

5. History & Heritage Management

6. Civic & Ethical Studies

7. Sociology

8. Public R/n & Communication

9. Wolaita Language and Literature

10. Dawuro Language and Literature

11. Social Anthropology

12. Film and Television Production

በትምህርት እና ባሕሪ ጥናት ኮሌጅ በቅድመ ምረቃ የሚሰጡ የትምህርት መርሃ ግብሮች (03)

1. Education Planning and Leadership

2. Psychology

3. Earlier childhood care and Education

በእንስሳት ህክምና ትምህርት ቤት በቅድመ ምረቃ የሚሰጡ የትምህርት መርሃ ግብሮች (01)፡

1. Veterinary Medicine

በሕግ ትምህርት ቤት በቅድመ ምረቃ የሚሰጡ የትምህርት መርሃ ግብሮች (01)

1. Law

በኢንፎርማቲክስ ትምህርት ቤት በቅድመ ምረቃ የሚሰጡ የትምህርት መርሃ ግብሮች (03)

1. Computer science

2. Information system

3. Information technology

«ዕውቀትን በተግባር» በሚል መሪ ቃል የሚታወቀው እንዲሁም በ2022 ዓ.ም “ቴክኖሎጂ መር የግብርናና ጤና ልዕቀት ማዕከል” ለመሆን ራዕይ የሰነቀው ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ምርጫዎ ይሁን

➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!

➤ ጥር 23/2015 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/Wolaita-Sodo-University-246568056057804/

ቴሌግራም፡https://t.me/WolaitaSUniversity

ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos

ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/

ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09

ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/

ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን
936 views15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 18:06:43
733 views15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ