Get Mystery Box with random crypto!

Wolaita Sodo University

የቴሌግራም ቻናል አርማ wolaitasuniversity — Wolaita Sodo University W
የቴሌግራም ቻናል አርማ wolaitasuniversity — Wolaita Sodo University
የሰርጥ አድራሻ: @wolaitasuniversity
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.46K
የሰርጥ መግለጫ

This is the official telegram channel of Wolaita Sodo University
Our Official Website :
http://www.wsu.edu.et/
Our Official Facebook page :
https://m.facebook.com/Wolaita-Sodo-University-246568056057804

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 23

2022-06-29 15:58:17 ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን(EBC) ለቀጣይ 5 ዓመታት አብሮ መስራት የሚያስችል የጋራ ውል ስምምነት አደረጉ፡፡

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ ዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የትብብር ስምምነት ሰነዶችን ተፈራርሞ ወደ ስራ ገብቷል።

ዩኒቨርሲቲው በሃገሪቱ አንጋፋ የመንግስት ሚዲያ ተቋም ከሆነው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን(EBC) በተለያዩ መስኮች በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ከሰሞኑን ተፈራርሟል።

የስምምነቱ ዓላማ ዩኒቨርሲቲው የሚሰራቸውን የመማር ማስማር፥ ምርምር፥ ማህበረሰብ አገልግሎት፥ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ሌሎች ልማታዊ ስራዎችን በኢቢሲ የሚዲያ አማራጮች በማቅረብ ተቋሙ ለሀገር እያበረከተ ያለውን ሁለገብ አስተዋፅኦ በህብረተሰቡ ዘንድ ግንዛቤ እንዲኖር ለማስቻል እንደሆነ ተገልጿል።

በዩኒቨርሲቲው የሚዘጋጁ አዎንታዊና ተፅእኖ ሊፈጥሩ የሚችሉ መልዕክቶችን በኢቢሲ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን እና ዲጂታል ሚዲያ ለህብረተሰቡ ለማስተላለፍ እንዲሁም በጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን መስክ የሚማሩ ተማሪዎችን በኢንተርንሽፕ ለማሳተፍ ሁለቱ ተቋማት ከስምምነት መድረሳቸው ተጠቁሟል።

ዩኒቨርሲቲው ለሚያከናውናቸው አበይት ተግባራት በቂ የዜና ሽፋን ለመስጠት፤ ለጥናትና ምርምር አስፈላጊውን ግብአት ለማቅረብ፤ ለተማሪዎች የስራ ላይ ስልጠና/lnternship ለመስጠት፤ በዩኒቨርሲቲው ለሚማሩ የጋዜጠኝነት (ኮሚዩኒኬሽን) ተማሪዎች እና የተቋሙ ኮሚዩኒኬሽ፣ የሚዲያ እና የቴክኒክ ባለሙያዎች “በኢቢሲ የስልጠና ተቋም” የአጭር ጊዜ ተግባራዊ የሙያ ስልጠና ለመስጠት ኢቢሲ መስማማቱ ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ አገልግሎቶቹን በኢቢሲ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለማሰራትና ለማስተዋወቅ፤ ፕሮግራሞችን በአጋርነት ለማዘጋጀት፤ ዘጋቢ/ዶክመንተሪ ፊልሞችን በኢቢሲ ሬድዮና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በማሰራት አየር ላይ ለማዋል፤ ኤቨንቶችን በጋራ ለማዘጋጀት፤ የማስታወቂያ ፕሮዳክሽን ለማሰራት፤ የቀጥታ ስርጭት ኩነቶችን በኢቢሲ ሬድዮና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለማስተላለፍ ዩኒቨርሲቲው መስማማቱም ተገልጿል።

ስምምነቱ በጋዜጠኝነት እና ስነ-ተግባቦት መስክ የጋራ ጥናትና ምርምር ማካሄድን፣ የጋራ ሴሚናሮችን የማዘጋጀት እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችና ማቴሪያሎችን መለዋወጥ እንደሚያጠቃልል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ አሳውቀዋል፡፡

ይህ የሁለትዮሽ ስምምነት ለቀጣይ 5 ዓመታት በአጋርነትና ትብብር መስራት የሚያስችል ስምምነት መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል፡፡
6.6K viewsedited  12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 15:58:13
5.3K views12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 12:21:25
#Tips-Undergraduate Academic Programs in WSU

List of Undergraduate Programs MD/DVM/BSc/BA in WSU:

★★★★★★★★★★

College of Health Science and Medicin(12)፡

1. School of Public Health

2. Anesthesia

3. Neonatal Nursing

4. Operation Theatre Nursing

5. Emergency & Critical Care Nursing

6. Pediatrics And Child Health Nursing

7. Surgical Nursing

8. School of Medicine

9. Midwifery

10. Nursing

11. Pharmacy (B.Pharm)

12.…

http://www.wsu.edu.et/tips-undergraduate-academic-programs-in-wsu/
5.7K views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 20:45:22
4.9K views17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 20:44:50 #Tips(2)

List of Undergraduate Programs MD/DVM/BSc/BA In WSU:

★★★★★★★★★★

College of Health Science and Medicin(12)፡

1. School of Public Health

2. Anesthesia

3. Neonatal Nursing

4. Operation Theatre Nursing

5. Emergency & Critical Care Nursing

6. Pediatrics And Child Health Nursing

7. Surgical Nursing

8. School of Medicine

9. Midwifery

10. Nursing

11. Pharmacy (B.Pharm)

12. Medical Laboratory Science

College of Agriculture)(07)፡

1. Natural Resource Management

2. Animal and Range Science

3. Plant Science

4. Agri-business and value chain

4. management

5. Horticulture

6. Agro-Economics

7. Rural Development and Agricultural Extension

College of Natural and Computational Sciences)(09)፡

1. Biology

2. Biotechnology

3. Chemistry

4. Environmental Science

5. Geology

6. Mathematics

7. Physics

8. Sport Sciences

9. Statistics

College of Business and Economics (06)፡

1. Economics

2. Management

3. Accounting and Finance

4. Public Administration & Development Management

5. Marketing and Sales

6. Hoteling and Tourism

College of Engineering (06)፡

1. Architecture Engineering

2. Civil Engineering

3. Construction Technology
Management Eng.

4. Electrical and Computer Engineering

5. Hydraulic and Water Resource Engineering

6. Mechanical Engineering

College of Social Science and Humanities (10)፡

1. Geographic & environmental Studies

2. Archeology& Heritage Management

3. English Language and Literature

4. Amharic Language and Literature

5. History & Heritage Management

6. Civic & Ethical Studies

7. Sociology

8. Public R/n & Communication

9. Wolaita Language and Literature

10. Dawuro Language and Literature

11. Social Anthropology

12. Film and Television Production

College of Education and Behavioral Studiies (03)

1. Education Planning and Leadership

2. Psychology

3. Earlier childhood care and Education

School of Veterinary Medicine (01)፡

1. Veterinary Medicine

School of Law (01)፡

1. Law

School of Informatics (03)፡

1. Computer science

2. Information system

3. Information technology

12.1K views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 19:18:47
4.1K views16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 19:18:35 የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ10 ሄክታር መሬት ላይ ለተማሪዎቹ የምግብ ፍጆታ የሚውል የጓሮ አትክልት እያለማ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ ገለጹ።

አራተኛውን ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተከትሎ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ችግኝ መትከል ጀምሯል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ፤ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ለተማሪዎች የምግብ ፍጆታ የጓሮ አትክልት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም በ10 ሄክታር መሬት ላይ ለተማሪዎቹ የምግብ ፍጆታ የሚውል የጓሮ አትክልት እያለማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

“ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን በእንክብካቤ እንዲጸድቁ ማድረግ ያስፈልጋል” ያሉት ፕሮፌሰር ታከለ፤ የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራ ሁሉም በባለቤትነት ሊያከናውነው የሚገባ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በዩኒቨርሲቲው የአረንጓዴ ልማት ፕሮግራም አስተባባሪ ገለታው ከበደ፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት በዩኒቨርሲቲው የአረንጓዴ ልማት ሥራ በተደራጀ መንገድ ሲሰራበት ቆይቷል ብለዋል።

በዚህም የራሱ የሆነ አደረጃጀትና መዋቅር በመዘርጋት ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ እንዲጸድቅ በማድረግ ተጨባጭ ለውጥ ተመዝግቧል ብለዋል፡፡

በደን ልማት ላይ ብቻ ያተኮረ ከነበረው የችግኝ ተከላ በተጨማሪ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚያስችሉ የፍራፍሬ ተክሎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን ተናግረዋል።

ዘንድሮ ከ500 ሺህ በላይ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰው ከችግኞቹ አብዛኛዎቹ የፍሬፍሬ ተክሎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከ3 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን መትከሉም ተገልጿል።
3.9K views16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 19:16:16
3.5K views16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 19:15:14 ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ACCA ከተሰኘ አለም አቀፍ የፋይናንስና ቢዚነስ ማህበር ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የውል ስምምነት ተፈራረመ።

•••••••••••••••••••••••••

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት Assocation of Chartered Certified Accountants ከተሰኘ ዓለም አቀፍ ፋይናንስና ቢዚነስ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ከሚገኝ ማህበር ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የውል ስምምነት መፈራረሙ ተገልጿል።

በዩኒቨሲቲው ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍልን መደገፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችል የውል ስምምነት ነው ሁለቱ ተቋማት የተፈራረሙት።

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕረዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ ከተቋሙ ጋር የተደረገው የውል ስምምነት መሰረት በዩኒቨርሲቲው ሆነ በአከባቢው ከፋይናንስ አሰራር ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ይረዳል ብለዋል።

እንደ ተቋም ግልፅ ራዕይ፥ ተልዕ፥ የትኩረት መስክ እንዲሁም የቀጣይ አስር አመት ዕቅድ አውጥተን እየሰራን እንገኛለን ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህን ዕቅድ ለማሳካት አጋዥ ከሆኑ አለም አቀፍና አገር አቀፍ ተቋማት ጋር ለመስራት ሁልጊዜም በራችን ክፍት ነው ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም፤ በአሁን ሰዓት የፋይናንስ ዘርፍ ብዙ ችግሮች ያለበት ሲሆን ይህንን ችግር ለመቅረፍ ባለሙያዎች ዘርፉ በሚፈልገው ልክ ዕውቀትና ልምድ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ በመሆን ዘርፉንና እራሳቸው ማዘመን ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የፋይናንስ አሠራሮችን ከማሻሻል ባለፈም ለመምህራን እና ለዘርፉ ተማሪዎች የእውቀት እና ልምድ ሽግግር ለማድረግ ይህ የውል ስምምነት አገዥ እንደሆነም ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል።

ዩንቨርስቲው ቀጣይ ከማህበሩ ጋር በመቀናጀት የፋይናንስ አጠቃቀም ሥርዓት ለማሻሻል በቅንጅት እንደሚሰራ ፕ/ር ታከለ ታደሰ ተናግረዋል።

በመድረኩ የተገኙት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨረስቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕረዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ዴአ በበኩላቸው ከተቋሙ ጋር የተደረገው የውል ስምምነት በዘርፉ ከዩኒቨርሲቲው ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎችን በሰፊው ያግዛል ብለዋል።

እንደ ተቋም የዘመነ የፋይናንስ ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል የእውቀትና ልምድ በማካፈል ስምምነቱ አጋዥ እንደሆነና የተረጋጋ ፋይናንሻል አሰራር ለመገንባት አስቻይ ነው ሲሉም ዶ/ር ሙላቱ ገልጸዋል።

መቀመጫውን በሀገረ እንግላሊዝ ያደረገው ACCA ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ዓለም ሀገራት ተመሳሳይ ሥራ እየሠራ እንደሚገኝ የተናገሩት በኢትዮጵያ የማህበሩ ዳይሬክተር ወ/ሮ ዮዲት ካሳ ናቸው።

ዳይሬክተሯ የፋይናንስ አሰራርን በትክክል መተግበር ሲቻል ከፋይናንስ አሰራር ጋር የሚነሱ ችግሮችን መቅረፍ ይቻላል ሲሉ ገልጸዋል። ማህበሩ ተመሳሳይ ዓላማን አንግቦ በተለያዩ ሀገራት እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል ።

ማህበሩ ከዩንቨርሲቲው ጋር በመተባበር ስልጠና በማዘጋጀት፣ የአቅም ግንባታ ሥራዎች በመስጠት እና የልምድ ልውውጥ በማድረግ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ሲሉም ወ/ሮ ዮዲት አሳውቀዋል።

የዩኒቨርቲው ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ አካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ብርሀኑ አለሙ በበኩላቸው ከዚህ ዕድሜ ጠገብ ተቋም ጋር መስራት ለዘርፉ መምህራንና ተማሪዎች የሚሰጠው ፋይዳ ላቅ ያለ ነው ብለዋል።

በመርሃ ግብሩ ከፊርማ ስነ-ስርዓት በተጨማሪ ከአለም አቀፍ የተፈቀደላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ማህበር/ACCA ለአካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል መምህራንና ተማሪዎች ስለጠና ተሰጥቷል።

የአለም አቀፍ የተፈቀደላቸው የሂሳብ ባለሙያዎ ማህበር በ176 አገራት ሁለት መቶ ሺህ አባላት እና ከአምስት መቶ ሺህ በላይ ተማሪዎች እንዳሉት ታውቋል።
3.4K views16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 19:14:55
3.0K views16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ