Get Mystery Box with random crypto!

Wolaita Sodo University

የቴሌግራም ቻናል አርማ wolaitasuniversity — Wolaita Sodo University W
የቴሌግራም ቻናል አርማ wolaitasuniversity — Wolaita Sodo University
የሰርጥ አድራሻ: @wolaitasuniversity
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.46K
የሰርጥ መግለጫ

This is the official telegram channel of Wolaita Sodo University
Our Official Website :
http://www.wsu.edu.et/
Our Official Facebook page :
https://m.facebook.com/Wolaita-Sodo-University-246568056057804

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-18 18:09:02 WOLAITA SODO UNIVERSITY ACADEMIC CALENDAR OF 2015 A.Y: SECOND AND SUMMER SEMESTER
2.6K views15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 16:35:20
2.5K views13:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 16:34:59 በኢትዮጵያ ከሚገኙ አጠቃላይ ዩኒቨርሲቲዎች በምርምር እና በቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች 6ኛ

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ "በምርምርና በቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች" በኢትዮጵያ ከሚገኙ አጠቃላይ ዩኒቨርሲቲዎች ስድስተኛ ደረጃ መያዙ ተገለጸ።
_______
SCIMAGO INSTITUTIONS RANKINGS የተሰኘ የበይነ መረብ ትስስር ገጽ በዓለም፣ በአፍሪካና በኢትዮጵያ የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን (ዩኒቨርሲቲዎችን) በምርምር፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎችና በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ያከናወኑትን ተግባራት ላይ ትኩረት በማድረግ ተቋማቱን በተለያዩ መስፈርቶች በማወዳደር ደረጃ በመስጠት ይታወቃል።

ድህረ ገጹ እ.አ.አ በግንቦት ወር 2023 ዓ.ም (May 2023) ባወጣው መረጃ በዓለም፥ በአፍሪካ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን በምርምር፣ በፈጠራ ሥራዎች እና በማህበረሰብ አገልግሎት ያከናወኑትን ተግባራት መሰረት በማድረግ የተቋማቱን የደረጃ ሰንጠረዥ ይፋ አድርጓል።

SCIMAGO INSTITUTIONS RANKINGS ድህረ ገጽ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በምርምር እና በቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች በኢትዩጵያ ከሚገኙ አጠቃላይ ዩኒቨርሲቲዎች ስድስተኛ/6ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።

በደረጃ ሰንጠረዥ መሰረት "በምርምር መስክ" ጎንደር፣ አዲስ አበባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ጅማ፣ ሀረማያ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ወሎ፣ አክሱም፣ ባህርዳር፣ መቐሌ፣ አርባ ምንጭ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች በቅደም ተከተል ከ 1-12 ያለውን ደረጃ የያዙ መሆኑን ድህረ ገጹ ጠቁሟል።

እንዲሁም "በፈጠራ ስራዎች" አክሱም፣ ጅማ፣ ሀረማያ፣ አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር፣ ወላይታ ሶዶ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ወሎ፣ መቐሌ፣ አርባ ምንጭ፣ ጎንደር እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች በቅደም ተከተል ከ 1-12 ያለውን ደረጃ መያዛቸው በድህረ ገጹ ተመላክቷል።

ምርምር ለማካሄድ የሚያስችል ምቹ ከባባዊ ሁኔታን በመፍጠር፣ የተሳለጠ መልካም አስተዳደር በማስፈን፣ ተመራማሪዎች የበለጠ እንዲመራመሩ እና የምርምር ውጤታቸውን እንዲያሳትሙ ድጋፍ፣ ክትትል እና አመራር በመስጠት እንዲሁም ማበራተቻ በመስጠት የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በትብብር መስራት ተገቢ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር አስገንዝቧል።

ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ ችግር ፈች ምርምሮችን በመስራት እና የማህበረሰብ አገልግሎት በመስጠት የጀመረውን ስራ አጠናክሮ ሚያስቀጥል መሆኑን እየገለጸ፤ በምርምርና በፈጠራ ሥራዎች ለተገኘው ደረጃ እንኳን ደስ አለን በማለት መልዕክት አስተላልፏል።

SCIMAGO INSTITUTIONS RANKINGS ድረ ገጽ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ያገኘውን ደረጃ ለመመልከት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
https://www.scimagoir.com/rankings.php?country=ETH&ranking=Research

➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!

➤ ግንቦት 10/2015 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/Wolaita-Sodo-University-246568056057804/

ቴሌግራም፡https://t.me/WolaitaSUniversity

ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos

ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/

ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09

ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/

ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን
2.4K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 18:54:28
2.5K views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 18:52:42 ከአየርላንድ "ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ዱብሊን" ለትምህርታዊ ጉብኝት ለመጡ ተማሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት ከአየርላንድ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ዱብሊን ለይፋዊ ትምህርታዊ ጉብኝት ለመጡ ተማሪዎች ደማቅ አቀባበል አደረገ።
________
በሀገረ አየርላንድ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ዱብሊን(UCD) ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጋር ዓመታትን ያስቆጠረ እና በሁለትዮሽ የጋራ ትብብር ማዕቀፍ ላይ የተመሰረተ ወዳጅነት አላቸው።

ሁለቱ ተቋማት በBRTE ፕሮጀክት ላይ ባላቸው ስምምነት መሰረት በተማሪዎች እና ሰራተኞች ልውውጥ፣ በልምድና ተሞክሮ ልውውጥ፣ በአጭር ጊዜና በረዥም ጊዜ ስልጠና፣ በጋራ በሚተገበሩ ስርዓተ ትምህርት ቀረጻ እና የድህረ ምረቃ የትምህርት ዕድል በማመቻቸት፣ በጋራ በሚተገበሩ የምርምር ፕሮጀክት ትግበራና መሰል ተግባራት ላይ በአጋርነት የትብብር ማዕቀፍ በስፋት ሲሰሩ ቆይተዋል።

በተማሪዎች እና ሰራተኞች ልውውጥ ረገድ ተቋማቱ ልምድ እና ተሞክሯቸውን የተጋሩበት ሰፊ ዕድል በፕሮጀክቱ የተፈጠረ ሲሆን፤ 12 ያህል የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መምህራንም በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ዱብሊን በተለያዩ የትምህርት መስኮች የፒ.ኤች.ዲ ትምህርት ዕድል አግኝተዋል።

በዛሬው ዕለትም የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ከአየርላንድ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ዱብሊን ለይፋዊ ትምህርታዊ ጉብኝት ለመጡ የተማሪዎች ልዑክ አባላት ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

በአቀባበል መድረኩ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ የሰው ዘር መገኛ እና ጥንታዊት ታሪካዊ ሀገር ስለሆነችው ኢትዮጵያ እንዲሁም «ዕውቀትን በተግባር» በሚል መሪ ቃል ስለሚታወቀው እና አረንጓዴ፣ ጽዱ፣ ሰላምዊና ሕብረብሔራዊ ተቋም ስለሆነው ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ገለፃ አድርገዋል።

በዩሲዲ የፕሮጀክቱ ዋና ኃላፊ ፕሮፌሰር ፓት፡ በፕሮጀክቱ የመጨረሻ አምስት ዓመታት ውስጥ ስለተመዘገቡ ቁልፍ ስኬቶች ገለፃ ያደረጉ ሲሆን፤ የተማሪዎቹ ይፋዊ ትምህርታዊ ጉብኝት ሁለቱ ተቋማት በተማሪዎች ልውውጥ ረገድ በቀጣይ የሚያስጀምሩት የሁለተኛ ዘር ፕሮጀክት የልምድ ልውውጥ አካል በመሆን ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

ለአስር ቀናት ለሚቆይ ይፋዊ ትምህርታዊ ጉብኝት ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የመጡት እነዚህ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ዱብሊን በሂዩማኒቴርያን አክሽን/MSc in Humanitarian Action/የትምህርት መስክ የማስተርስ ተማሪዎች መሆናቸው በመድረኩ ተጠቁሟል።

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የBRTE ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ኩማ በበኩላቸው፡ ተማሪዎቹ በቆይታቸው ከወላይታ ማህበረሰብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማት ጋር በመተዋወቅ የሰብአዊ ተግባር ፖሊሲዎችንና መርሃ ግብሮችን ከአካባቢያዊ ሁኔታዎች እና ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ጋር በማስተሳሰር ግንዛቤ እንዲያገኙ የትምህርታዊ ጉብኝቱ መርሃ ግብር አስቻይ መሆኑን ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ በቆይታቸው የወላይታን ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ተቋማት የሚጎበኙ መሆኑ በመድረኩ የተገለጸ ሲሆን፤ ትምህርታዊ ጉብኝቱ የግብረ ሰናይ ስራዎች እና ፖሊሲዎች እንዴት የማህበረሰቡን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ መቀረፅ እንዳለባቸው ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ አላማውን ያደረገ እንደሆነ ተመላክቷል።

የትምህርታዊ ጉብኝቱ ልዑካን አባላት በማኔጅመንቱ ከተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል በኋላ በዋናው ግቢ የተገነባውን የወላይታ ባህል ሙዚየምን ጨምሮ የተለያዩ ልማታዊ ስራዎችን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።


➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!

➤ ግንቦት 09/2015 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክWolaita Sodo University4/

ቴሌግራም፡https://t.me/WolaitaSUniversity

ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos

ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/

ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09

ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/

ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን
2.4K views15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 16:25:58
2.0K views13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 18:39:39 በዩኒቨርሲቲው 2ኛው ዙር ብሔራዊ የቦክስ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ።

ከኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በተዘጋጀው የቦክስ ሻምፒዮና ውድድር ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ 7 ክለቦች የተሳተፉ መሆኑም ተጠቁሟል።

=========================

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር 2ኛ ዙር ብሔራዊ የቦክስ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር እያካሄደ መሆኑን የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል አሳውቋል።

በጨዋታው የማስጀመሪያ ስነስርዓት የተገኙት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ዴአ አረንጓዴ፥ ጽዱ፥ ሠለማዊ እና ሕብረብሔራዊ ወደ ሆነው ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በሠላም መጣችሁ በማለት ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዩኒቨርስቲው ከመማር ማስተማር፣ ከጥናትና ምርምር እንዲሁም ከማህበረሰብ አገልግሎት ሥራዎች ጉን ለጎን በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች በስፋት እየሰራ እንደሆነ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ገልጸው፤ የቦክስ ስፖርትም በአከባቢው ተሰጥኦ ያላቸው የበርካታ ተጨዋቾች መፍለቂያ ስለሆነም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተገበረ ይገኛል ብለዋል።

ዩኒቨርስቲው ለወደፊቱም ከኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ዘርፉ በተለያዩ ስልጠና በማበልጸግ በታዳጊ ፕሮጀክት እና መሰል ተግባሮችን በትብብር የሚሰራ ይሆናል ሲሉም ዶ/ር ሙላቱ ጠቁመዋል።

ውድድሩን ላዘጋጁት ለፌዴሬሽኑ እና ለስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ምስጋና ያቀረቡት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ ለሁሉም ክለቦች መልካም ቆይታ እና በውጤት የታጀበ ውድድር እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ የሆኑት መ/ር አፈወርቅ አሳሌ በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር እየተካሄደ ያለው 2ኛው ዙር ብሔራዊ ቦክስ ክለቦች ሻምፒዮና ባማረ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን አሳውቀዋል።

የቦክስ ስፖርት የካርዲዮቫስኩላር ጤናን ለማሻሻል፣ በጡንቻ ላይ ጥንካሬን እንዲኖር ለማድረግ፣ ጽናትን ለማዳበር፣ ለጤናማ ክብደት፣ የሰውነት ሚዛንን እና ቅንጅትን ለማሻሻል፣ የአካል ብቃትን ለማዳበር ብሎም ለወጣቶች እንደ ገቢ ማስገኛ እየሆ መጥቷል ሲሉ ኃላፊው ገልጸዋል።

በውድድሩ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ቦክስ ክለብ፣ ድሬዳዋ ቦክስ ክለብ፣ ፋስል ከተማ ቦክስ ክለብ፣ ፌደራል ፖሊስ ቦክስ ክለብ፣ ፌደራል ማረሚያ ቦክስ ክለብ፣ አዲስ አበባ ቦክስ ክለብ እንዲሁም ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ቦክስ ክለብ ተሳታፊ መሆናቸው ተመላክቷል።

«እውቀትን በተግባር!!»

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
1.4K views15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 18:39:34
1.3K views15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 18:37:07 «የሌማት ትሩፋት» አካል የሆነው “የንብ ማነብ እና የማር ምርት” ፕሮጀክት በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ!!

ዩኒቨርሲቲው በአካባቢው ያሉ ጸጋዎች ላይ በማተኮር እየተገበረ ካለው ዘርፈ ብዙ የሌማት ትሩፋት ሥራዎች የንብ ማነብ እና የማር ምርትና ምርታማነትን ማሻሻል አንዱ ሲሆን፤ ይህን ወደ እያንዳንዱ አርሶ አደር ቤተሰብ ተደራሽ ለማድረግ ሰፊ ዕቅድ በማዘጋጀት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው በማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክት በመታገዝ በንብ ማነብ እና የማር ምርት እና ምርታማነትን ለማሻሻል የጥናትና ምርምር ስራዎችን ተግባራዊ ከማድረግ ባሻገር ተገቢውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ የአርሶ አደሩ ህይወት በሚለወጥበት አግባብ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራም ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው የተልዕኮ አቅጣጫዎች እና የትኩረት መስኮች ላይ በማተኮር በሚበሉ የፍራፍሬ ዝርያዎች፣ በወተት ሀብት ልማት፣ በእንስሳት ማድለብ፣ በማሞከት፣ በዓሳ ስጋ አቅርቦት፣ በዶሮ እርባታ እና በሌሎች ተዛማጅ መስኮች ላይ በማተኮር ሰፊ ዕቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ተመላክቷል

«እውቀትን በተግባር!!»

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
1.3K views15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 18:37:00
1.3K views15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ