2023-04-24 20:27:25
ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በሁለትዮሽ የአጋርነትና ትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በመፍጠር ከፍተኛ ሀብት ላስገኙ ከፍተኛ ተመራማሪዎችና መምህራን ዕውቅና ተሰጣቸው።
_______በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከመደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ጎን ለጎን ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር በሁለትዮሽ የአጋርነት ትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በመፍጠር ሀብት አፈላልገው ላገኙና በዘርፉ የድርሻቸውን ተቋማዊ ሚና ለተወጡ ተመራማሪዎች እና መምህራን ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
የዩኒቨርሲቲው አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት መምህር ፍሰሀ ሰለሞን፡ ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር አጋርነትና ትብብር በመመስረት ሀብት በማፈላለግ የድርሻቸውን ተቋማዊ ሚና የተወጡና እየተወጡ ያሉ ከፍተኛ ተመራማሪዎችንና ባለሙያዎችን እንደ ተቋም ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።
ለዚህም ዳይሬክቶሬቱ ለ2ኛ ጊዜ ባካሄደው የዕውቅና ሥነ ስርዓት ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች እና ተቋማት ጋር ሳይሰላቹ በመጻጻፍ ሀብት በማፈላለግ ረገድ ህጋዊ አካሄድን ተከትለው የሁለትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ እንዲፈረ ያደረጉ እንዲሁም ወደ ሥራ በመግባት ዓለም አቀፍ ልምዶችን እና ተጨማሪ ሀብት ወደ ዩኒቨርሲቲው እንዲመጣ ላደረጉ አካላት ዕውቅናው የተሰጠ መሆኑንም ዳይሬክተሩ አሳውቀዋል።
ዕውቅናው የተሰጣቸው ከፍተኛ ተመራማሪዎች ባለሙያዎች ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በጋራ የምርምር እና ፕሮጀክቶች በመስራት፤ በአጫጭር እና የረዥም ጊዜ ስልጠናዎችን በማመቻቸት፤ የድህረ ምረቃ የትምህርት ዕድል በማመቻቸት፤ የተማሪና የሠራተኞችን ተቋማዊ ልውውጥ በማሳደግ እንዲሁም የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲገኝ ያደረጉና የድርሻቸውን ሚና የተወጡ ናቸው ሲሉም መምህር ፍሰሀ ጠቁመዋል።
ዩኒቨርሲቲው በሁለትዮሽ አጋርነት ለሚተገበሩ የአለም ዓቀፋዊነት ሥራዎች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በተቀናጀ መልኩ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ገልጸው፤ እንደ ተቋም በዓለም አቀፋዊነት የትብብርና የአጋርነት ማዕቀፍ ከ 47 በላይ የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙን እና ይህም ለተቋም የዕድገት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።
መምህር ፍሰሃ አክለውም፤ ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የስራ መስኮች ከተቋማቱ ጋር በትብብርና አጋርነት ለመስራት ከተፈራረማቸው አጠቃላይ የመግባቢያ ሰነዶች መካከል 24 ያህሉ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ የገቡ እንደሆኑና 23 ያህሉ ደግሞ የትግበራ ሂደት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመጻጻፍ አጋርነትን መስርተው ሀብት በማፈላለግ ረገድ የድርሻቸውን ሚና የተወጡ እንዲሁም በትጋት እየሰሩ ያሉ የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎችና መምህራን ምስጋና ይገባቸዋል ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ግራንት በማፈላለግ ተጨማሪ ሀብት እንዲገኝ ያደረጉ አካላትን በማመስገን እውቅና መስጠቱ የላቀ ተነሳሽነትን የሚፈጥር መሆኑንም ገልጸዋል።
ዕውቅናው የተሰጣቸው ከፍተኛ ተመራማሪዎች እና ባለሙያዎች ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ለተቋሙ እድገት ላበረከቱት አስተዋፅዖ ሁሌም ሊመሰገኑ ይገባል ያሉት መምህር ፍሰሃ፤ የዩኒቨርሲቲውን አመራር በመወከል ለዘርፉ ቁልፍ ተዋናዮች፣ ለተመራማሪዎች እና ባለሙያዎች «የምስጋና ወረቀት» በታላቅ ክብር የተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።
ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎችና ባለሙያዎች ይህንን አርሃያነት በመከተል የተቋሙን ተልዕኮ እና የትኩረት መስክ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር አጋርነት በመመስረት ሀብት የማፈላለግ ስራ ላይ ትኩረት ሰጥተው የድርሻቸውን ሚና እንዲወጡ ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ዕውቅና የተበረከተላቸው ከፍተኛ ተመራማሪዎች እና ኤክስፐርቶች እንደ ተቋም የተሰጣቸው እውቅና ለበለጠ ስራ እንደሚያነሳሳቸው በመግለጽ የተቋሙን አመራሮች አመስግነዋል።
➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!
➤ ሚያዝያ 16/2015 ዓ.ም
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክWolaita Sodo University4/
ቴሌግራም፡https://t.me/WolaitaSUniversity
ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos
ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/
ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09
ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/
ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን
2.2K views17:27