Get Mystery Box with random crypto!

Wolaita Sodo University

የቴሌግራም ቻናል አርማ wolaitasuniversity — Wolaita Sodo University W
የቴሌግራም ቻናል አርማ wolaitasuniversity — Wolaita Sodo University
የሰርጥ አድራሻ: @wolaitasuniversity
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.46K
የሰርጥ መግለጫ

This is the official telegram channel of Wolaita Sodo University
Our Official Website :
http://www.wsu.edu.et/
Our Official Facebook page :
https://m.facebook.com/Wolaita-Sodo-University-246568056057804

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-04-20 19:20:24
1.2K views16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:19:16 የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ አካል ከሆነው ጃፓይጎ ድርጅት ጋር በመተባበር በጤናው ዘርፍ የሚተገበረው ፕሮጀክት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ።

የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት የፕሮጀክቱን የእስካሁን አፈጻጸም እና የቀጣይ ዕቅድ በተመለከተ ከድርጅቱ ከመጡ አመራሮች ጋር መክረዋል።
_
የጆን ሆፕኪንስ
ዩኒቨርሲቲ አካል ከሆነው ጃፓይጎ ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር የጤናውን ዘርፍ የሚያግዙ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የኮሌጁ ቺፍ ኤክስክዩቲቩ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ወኪል ወልዴ ባቀረቡት ሪፖርት ተገልጿል።

ከድርጅቱ ጋር በሁለትዮሽ የአጋርነት የትብብር ማዕቀፍ በጋራ ለመስራት በተካሄደ ስምምነት መሰረት ለ 5 ዓመት የሚቆይ "የጤና ሰራተኞችን የሙያ ብቃት የማሻሻያ ፕሮግራም" የስምምነት ሰነድ ከዚህ ቀደም መፈራረማቸውን ኤክስክዩቲቩ ዳይሬክተሩ አሳውቀዋል።

ፕሮግራሙ የተሻለና ብቁ የጤና ባለሙያን በማፍራት ጥራት ያለውን የጤና ክብካቤ አገልግሎት መስጠትን ዓላማ በማድረግ ባለፉት ሶስት ዓመታት ለጤና ዘርፍ ዕድገት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ተግባር ሲከናወን መቆየቱንም አሳውቀዋል።

ጃፓይጎ በሕክምና እና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ለስልጠናና የተግባር ልምምድ የሚያገለግሉ የህክምና መሣሪያዎችን እንዲሁም ግብአቶችን ድጋፍ በማድረግ፤ የጤና ፕሮግራም የጥራት ማረጋገጫ እንቅስቃሴዎች ላይ በመሳተፍ፤ ለጤና ባለሙያዎች ተከታታይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት፤ በብቃት ላይ የተመሰረተ ስርዓተ ትምህርት ትግበራ ላይ በመሳተፍ፤ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በመስጠት፤ በስርዓተ ጾታ ትግበራ ላይ በመሳተፍ፤ ቀጣይነት ያለው የሙያ እድገት አስተዳደር ስርዓትን በማጠናከር እንዲሁም በሰው ኃይል አስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች እና መሪዎችን በማሰልጠን ከፍተኛ እገዘ ማድረጉን ዶ/ር ወኪል ጠቁመዋል።

ፕሮግራሙን በማስመልከት ከጃፓይጎ ከመጡ ልዑካን ጋር በተደረገ ውይይት የጤናውን ዘርፍ የሚያግዙ ስራዎች የበለጠ ተጠናክረው መቀጠል በሚችሉበት አግባብ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፤ በዋናነት በቀጣይ ግዜ ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የምዘና ሂደትን ማጠናከር በሚያስችል አግባብ በትብብር ለመስራት ሁለቱ ተቋማት የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በጤናው ዘርፍ ያለውን ውስን ሀብት በአግባቡ አለመጠቀምና የአመራርነት ክህሎት ክፍተት አለማቀፋዊ ቸግሮች መሆኑን ከጃፓይጎ የመጡ ልዑካን ያሳወቁ ሲሆን፤ እነዚህን ክህሎቶች በመሙላት የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት የተጀመሩ ተግባራት በቀሪ ጊዜያት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ በውይይቱ ተመላክቷል።

በመድረኩ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ ባደረጉት ንግግር፡ የጤና ባለሙያዎች ሚናቸውን ለይተው የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት በወቅቱ፣ በሚፈለገው ደረጃ እና ጥራት እንዲወጡ ከማድረግ አንጻር ከጃፓይጎ ጋር በትብብር የተሰሩ ስራዎች ጉልህ ፋይዳ እንዳላቸው ጠቁመዋል።

መልካም የጤና አስተዳደር ስርዓትን መገንባት ለአንድ ሀገር ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት ወሳኝ እንደሆነ ፕሬዝዳንቱ ገልጸው፤ በፕሮግራሙ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የጤና ስርዓትን፣ አመራር ክህሎትን እና አስተዳደርን ከማሻሻል ረገድ የተጀመሩ ስራዎች የበለጠ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።

እውቀትን በተግባር!!

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
1.5K viewsedited  16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:19:15
1.4K views16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 02:57:48 ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
___

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ የ2015 ዓ.ም የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ድህነት ሲል መከራና ስቃይን ለተቀበለበት እና ሞትን ድል አድርጎ ለተነሳበት የትንሳኤ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ፕሬዝዳንቱ የተሰማቸውን ጥልቅ ደስታ ገልጸዋል።

“ስቅለቱ እና ትንሳኤው” ፍቅርን፣ ይቅርታን እና በፅናት ማሸነፍን ያስተምራል ያሉት ፕ/ር ታከለ፤ ክርስቶስ በስቅለቱና በትንሳኤው ካሳየን በጎነት፥ ፍቅርና ርህራሄ አልፎም ድል አድራጊነት በመማር “ለሰው ልጆች ሁሉ ፍቅርን፣ መሰጠትና ፍፁማዊ ደግነትን ልናሳይ ይገባል” ብለዋል።

የክርስትና አስተምህሮት እንደሚያስረዳን “ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ህይወቱን የሰጠው ስለ ሰው ልጅ ፍፁም ፍቅር ነዉ” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ እኛም ይህን አርዓያነት በመከተል በፍጹም ፍቅር እንድንኖር እና መስጠትን የህይወታችን አካል ልናደርግ ይገባል ብለዋል።

የትንሳኤ በዓል "ከፈተና ማዶ አስገራሚ የድል አድራጊነት ብስራት መኖሩን የሚያውጅ መሆኑን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ የሰው ልጅ በማንኛውም ምድራዊ ፈተና መካከል ቢሆን እንኳ ነገ ትልቅ ተስፋ መኖሩን እንዳይዘነጋ የሚያመላክት የእውነት መሰረት መሆኑንም ጠቁመዋል።

እርስ በርስ በክፋትና በተንኮል ከመጠማመድ ተለይተን፣ የተንኮል አስተሳሰብን በፍጹም ቀብረን በምትኩ የትህትና፣ የመተሳሰብ፣ የአብሮነት እና የአንድነት በጎ አስተሳሰብ እንድናጎለብት ጽኑ መሠረት የሚጥል ኃይማኖታዊ ክብረ በዓል እንደሆነ ስለትንሳኤ በዓል ፕ/ር ታከለ አብራርተዋል።

እንደ እምነቱ አስተምህሮ "ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በከፈለው ዋጋ የይቅርታ ህይወትን ተምረን በይቅርታ ልንሻገር ይገባል" ሲሉ የተናገሩት ፕ/ር ታከለ፤ ትንሳኤ የይቅርታና የፍቅር ምልክት መሆኑን በመገንዘብ፥ በዓሉን ስናስብ የበደሉንን ይቅር በማለት፣ዕርቅ በማድረግና ሠላም በማውረድ በፍጹም ፍቅር በመመላለስ ሊሆን ይገባል ሲሉም ጠቁመዋል፡፡

የተወለደው እንዲያድግ፣ ወጣት አገር እንዲረከብ፣ ጎልማሳው ለአገሩ በርትቶ እንዲሰራ፣ አረጋውያን በክብር እንዲጦሩ የሚያስፈልገው እርቅ፣ ሰላምና ፍቅር ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የትንሳኤ በዓልን ስናከብር ቂም እና ጥላቻን በይቅርታ በማለፍ የተቸገሩ ወገኖቻችንን በመደገፍ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ተቋም በሚያጋጥሙን ጊዜያዊ ፈተናዎች ሳንሸበር፣ ለዘላቂ ህዝባዊ ጥቅም መረጋገጥ ተግተን መስራትና መጓዝ ይጠበቅብናል ያሉት ፕ/ር ታከለ፤ የክርስቶስን አርዓያነት በመከተልና እውነት ላይ በመቆም እንዲሁም የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በጽናት በመቋቋም በፍቅር እንድንኖር እና መስጠትን የህይወታችን አካል ልናደርግ ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንቱ አሳውቀዋል።

የዘንድሮውን የትንሳዔ በዓል ስናከብር እንደ ሀገርም ሆነ፥ እንደ ተቋም ባላፉት ጥቂት የለውጥ አመታት የታዩ ውጤቶች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን በመውሰድ፤ በቀጣይ ጊዜያት አዲስ ነገር በምንሰራበት ሁኔታ ላይ በማተኮር መሆን አለበት ያሉት ፕ/ር ታከለ ፤ በሚቀጥሉት ጊዜያትም ለሚያጋጥሙን ፈታኝ ሁኔታዎች እጅ ሳንሰጥ ለውጤታማነት የበለጠ ተቀናጅተን በትብብር ልንሰራ ይገባል በማለት ተናግረዋል።

ትንሳኤን ስናስብ ከችግር በኋላ ደስታ፤ ከሞት በኋላ ትንሳኤ፤ ከጨለማ በኋላ ብርሃን መኖሩን በማስታወስ መላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ባለድርሻ አካላት ከመቼውም ጊዜ በላይ በመግባባት፣ በመደማመጥ እና አንድነትን ይበልጥ በማጠናከር በሁሉም የሥራ መስኮች የተጀመሩ የልማት ተግባራት ከግብ እንዲደርሱ የዘወትር ድጋፍ በመስጠት የድርሻውን እንዲወጣ ፕሬዝዳንቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲያችን በመማር ማስተማር፣ በችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር፣ በአሳታፊ የማህበረሰብ አገልግሎት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና ስርጸት እንዲሁም በሌሎች አስተዳደራዊ እና ልማታዊ መስኮች የጀመራቸውን የለውጥ ተግባራት ከዳር በማድረስ ለተቋማችን ራዕይ መሳካት በትብብር መስራት ተገቢ እንደሆነም ፕ/ር ታከለ አሳስበዋል።

የትንሳኤን በዓል ስናከብር በተለመደው የመተጋገዝና የአብሮነት መንፈስ ሆነን በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ የተጎዱ እና ለአደጋ የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን በላቀ ተነሳሽነት በመርዳት፥ አረጋዊያንን በመደገፍ፣ የወደቁትን በማንሳት፣ የታረዙትን በማልበስ እና የተራቡትን በመመገብ እንዲሁም ያላችሁ ለሌላቸው በማካፈል የተለመደው በጎ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ባስተላለፉት መልዕክት።

በድጋሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ በማለት በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ የመቻቻል፣ የአብሮነትና የወንድማማችነት እንዲሆን ፕሬዝዳንቱ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ዕውቀትን በተግባር!!

https://t.me/WolaitaSUniversity/1659
1.2K viewsedited  23:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 02:57:35
1.2K views23:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 18:47:56 To find the MSc./MA. Application form & ENSP Learning Agenda and proposal format clik the link below
http://www.wsu.edu.et/call-for-msc-ma-research-fund-opportunity-for-female-applicants/
429 views15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 18:47:55 WAGENINGEN UNIVERSITY & RESEARCH

(Stichting Wageningen Research Ethiopia)

To: WOLAITA SODO UNIVERSITY

#Subject: Call for MSc/MA. Research Fund Opportunity for Female Applicants

Stichting Wageningen Research (SWR) Ethiopia is an international NGO based in Ethiopia. SWR Ethiopia is affiliated to Wageningen University & Research of the Netherlands. Its mission is to leverage transformation in Ethiopian food systems. One of the projects implemented by SWR is the Ethiopia Netherlands Seed Partnership (ENSP). ENSP is a project that evolved from the Integrated Seed Sector Development (ISSD) that has been implemented in Ethiopia for more than a decade.

One of the major intervention areas of ENSP is capacity development of seed sector
actors and engaging more professionals in the sector. In this regard, SWR Ethiopia, ENSP project has a plan to award MSc./MA. Students of higher institutes with research fund grant.

@Applicants of the MSc. /MA. Research fund are expected to fulfill the following criteria፡

1. MSc. /MA. Students of Higher Institutes

2. Ready to prepare their proposal

3. A student with higher academic and research competency

4. Interested and ready to work and answer ENSP learning agenda (thematic areas stated in the attached document)

5. An applicant who is ready to prepare a brief the research proposal, according
the attached ENSP application format

6. Ready to govern by the rules, regulation and agreement of SWR Ethiopia

@The SWR Ethiopia, ENSP learning questions, to be answered through research are:

#1. Conflict, disaster and seed insecurity

1. What is the impact of conflict and disaster on the Ethiopian seed system and what are the ways to mitigate and support seed system resilience in such areas of
Ethiopia?

2. How private, public intermediary and informal seed businesses contribute to
improved access to quality seed for small scale farmers in conflict/disaster affected
areas?

3. How can private sector and public sector; formal, intermediary and informal seed systems; private seed companies or local seed businesses, and different actors work towards creating sustainable access to quality seed for small scale farmers in conflict/disaster affected areas?

#2.Competition in the seed sector

1. What are future scenarios for the position, roles, and markets of local, national and international seed companies in the seed sector of Ethiopia?

@What should local seed companies do to be prepared for the future competition?

2. What are important requirements for the Ethiopian seed sector where both national and international seed companies can be active, building on their respective areas of competence?

#3. Seed sector governance

1. What evidence is required to be able to 'right-size' public policies to Ethiopia's demand for seed?

2. What are barriers and enablers to enforcement of available seed related laws and regulations across Ethiopia?

3. How the seed sector of Ethiopia is currently governed and how it should be governed better (which elements of existing governance indices would be useful to include in a quality of seed sector governance index tool? Is quality data available for Ethiopian seed sector governance, if not, what are missing and how can it be (easily) collected? How to translate this into a comprehensive seed sector dashboard?)

4. What is the progress of transformation of the seed sector in terms of the main functions of the seed sector,their interaction with socio-economic and environmental drivers, and effect on food system outcomes?

#Application_procedure

1. An applicant should fill the application form

2. An applicant should submit a brief proposal (based on ENSP format), attached

3. The application form should be signed and stamped by the respective departments of students

4. All the documents should be scanned and send (in PDF format) to:

hermine.tenhove@wur.nl copy to

ansha.yesufe.swr@gmail.com

5. The deadline for application is May 6, 2023

#Enclosure:
438 viewsedited  15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 18:47:52
416 views15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 19:34:53
1.0K views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 19:34:31 የዩኒቨርሲቲው «የሠላምና ልማት አማካሪ ምክር ቤት» በ2015 አጋማሽ አመት በተከናወኑ አንኳር የስራ አፈጻጸሞች እና ተያያዥነት ባላቸው ተቋማዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄደ።
_______________

ሠላማዊ መማር ማስተማርን ለማረጋገጥና ለማዝለቅ በ2015 አጋማሽ አመት በተከናወኑ አንኳር የስራ አፈጻጸሞች እና ተያያዥነት ባላቸውን ተቋማዊ ጉዳዮች ላይ አማካሪ ምክር ቤቱ ውይይት አካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ በ2015 አጋማሽ አመት የተከናወኑ ዋና ዋና የስራ አፈጻጸሞች እና ተያያዥነት ያላቸውን ተቋማዊ ጉዳዮች በተመለከተ ለምክር ቤቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዩኒቨርሲቲው ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ አበክሮ የሚሰራ፥ ገለልተኛና ሁሉን በእኩል የሚያስተናግድ ሕብረ ብሔራዊ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አሳውቀዋል።

“በአሉባልታና እና በሀሰተኛ መረጃ ” ለውጥ ፈጽሞ ሊመጣ አይችልም ያሉት ፕሬዝዳንቱ ፤ “ዕውቀትን በተግባር በመግለጽ” በሀገሪቱ አዎንታዊ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ለውጥ ለማምጣት በዕውቀት መመራት ግድ ይላል ብለዋል።

ተቋምን ለማጠልሸት በሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች ዩኒቨርሲቲውንና የተቋሙን አመራሮች ፈጽሞ አይገልጻቸውም ሲሉ በመጠቆም።

“ለውጥ በቆሞ ቀር አስተሳሰብ አይመጣም” ያሉት ፕ/ር ታከለ ፤ “ተራማጅና ዘመናዊ አስተሳሰቦችን በእውቀት በመተግበር ተቋማዊ እና ሀገራዊ የልማት እምርታ እንዲመጣ ከዓለም ዓቀፍ ተቋማት ጋር በአጋርነት እና ትብብር መስክ የጀመርናቸውን ተግባራት አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

ሠላም ሁለንተናዊ ተነሳሽነትን፣ መሰጠትንና፣ አብሮ መስራትን እንደሚጠይቅ የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፤ ዩኒቨርሲቲው ለሰላም ጉዳይ የቅድምያ ቅድምያ ሰጥቶ እንደሚሰራም አሳውቀዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ለሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደት መረጋገጥ በስፋት ሲሰራ ቆይቷል፥ የተሻለ ውጤትም ተመዝግቧል ያሉት ፕ/ር ታከለ፤ ከአካባቢው ማህበረሰብና ከባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመረው የሁለትዮሽ ቅንጅታዊ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የተረጋጋ እና ሰላም የሰፈነበት ምቹ አካባቢን በመፍጠር በመማር ማስተማር፣ በችግር ፈቺ ምርምር፥ በማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግርና ስርጸት መስክ ዩኒቨርሲቲው የጀመራቸውን ተግባራት አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ምክር ቤቱ ጉልህ ሚናውን እንዲወጣ ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል።

ፕ/ር ታከለ ባቀረቡት የ2015 በጀት አመት የ6 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት፦ አመራርና አስተዳደርን ከማጠናከር እንዲሁም ተቋማዊ የማስፈፀም አቅምን ከማጎልበት ረገድ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት የበለጠ ተጠንክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

አዲሱ የሰው ሀይል አደረጃጀት መዋቅር ተሰርቶ እና በሲቭል ሰርቪስ ኮሚሽን ፀድቆ ለዩኒቨርሲቲው የተላከ መሆኑን ፕ/ር ታከለ ጠቁመው፤ በአፈጻጸም መመሪያው መሠረት የአደረጃጀት መዋቅሩ ስራ ላይ እንዲውል ተገቢው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

በ2013 በጀት ዓመት በኦዲት ውጤቶች ላይ የድርጊት መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ ተገቢው የማስተካከያ እና የእርምት እርምጃ እየተወሰደ ነው ያሉት ፕ/ር ታከለ፤ የኦዲትና የህግ የበላይነትን ከማስከበር ረገድ የተጀመሩ ተግባራት በቀጣይ ጊዜያት የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አሳውቀዋል።

ሰላማዊ መማር መስተማርን ከማስፈን እና ከማዝለቅ ረገድ ባለፉት 6 ወራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ዘርፈ ብዙ ተግባራት የተከናወነ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ገልጸው፤ የውስጥ ተጋላጭነትን የመቀነስ፤ የህግ የበላይነትን የማስፈንና የማረጋገጥ እንዲሁም የተደራጀ ችግር ፈቺ የክትትል እና ድጋፍ ተግባራት በተቀናጀ አግባብ የተሰራ መሆኑንም አመላክተዋል።

አደረጃጀቶችን በማጠናከር ሰላማዊ መማር ማስተማር መቀጠሉ፤ የውስጥ አቅምን በመጠቀም ከፍተኛ ወጪዎች መቀነሱ፤ ከሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር ሀብት ማመንጨት መቻሉ፤ የድጋፍ፥ ክትትልና ግምገማ ሥርዓትን በማጠናከር የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፈታት መቻሉ በአፈጻጸም ደረጃ ባለፉት 6 ወራት በጥንካሬ የታየ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

ከዩኒቨርሲቲው "የሰላምና ልማት አማካሪ ምክር ቤት" አባላት ጋር በተካሄደው ምክክር በሠላምና ልማት ጉዳዮች ላይ በማተኮር ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፥ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ የዕለቱ መርሃ ግብር ተጠናቋል።

የዩኒቨርሲቲው "የሰላምና ልማት አማካሪ ምክር ቤት" በትምህርትና ስልጠና ተቋማት የአማካሪ ምክር ቤት የአሠራር ማዕቀፍ የተቋቋመ ሲሆን፤ በተቋሙ ውስጥና በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖ ዩኒቨርሲቲው የተሰጠውን ጉልህ ተልዕኮ በተገቢው ማሳካት እንዲችል በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።

ዕውቀትን በተግባር!!

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!
1.0K views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ