#Remedial_Exam የሪሜዲያል ሀገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና የሦስተኛ ቀን ውሎ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች እየተሰጠ ያለው ሀገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና ሦስተኛ ቀኑን ይዟል። ዛሬ ሰኔ 28/2015 ዓ.ም ዕለተ ረቡዕ በሁለቱም የተፈጥሮ እና ማሕበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎቹ የኬሚስትሪ እና የጄኦግራፊ ፈተና ተፈትነዋል። _________ በዩኒቨርሲቲው ሦስተኛ ቀኑን በያዘው የሪሜድያል ሀገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና በሁለቱም የተፈጥሮ እና ማሕበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች የኬሚስትሪ እና የጄኦግራፊ ፈተና ተፈትነዋል። ዛሬ በተሰጠው የኬሚስትሪ እና የጄኦግራፊ ፈተና በአጠቃላይ 5 ሺሕ 625 ተማሪዎች የተፈተኑ ሲሆን፤ ከጠቅላላ ተፈታኝ ተማሪዎች 3 ሺሕ 282 የተፈጥሮ እና 2 ሺሕ 374 የማሕበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ናቸው። የፈተናው ሂደት ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ ያሳወቁ ሲሆን፤ የፕሮግራሙ ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ የፈተና ሂደት እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በዩኒቨርሲቲው የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም፤ ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተናውን ህጎች በማክበር እና ሥነ-ምግባር ተላብሰው እንዲፈተኑ ያሳሰቡ ሲሆን፤ በቀጣይ አመት መደበኛ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን መቀጠል የሚያስችላቸውን ማለፊያ ውጤት እንዲያስመዘግቡ መልካም ምኞታቸውንም ገልጸዋል። የፈተናው ሂደት ሰኔ 28/2015 ዓ.ም ዕለተ ሐሙስ ከቀኑ 9 ሰዓት ሲቀጥል ለሁለቱም የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ፈተና የሚሰጥ መሆኑ ተመላክቷል። ➭ «ዕውቀትን በተግባር!!» የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!! ➤ ሰኔ 28/2015 ዓ.ም ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063820159424 ቴሌግራም፡ https://t.me/WolaitaSUniversity ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/ ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09 ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/ ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y= አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን 1.9K views14:19