Get Mystery Box with random crypto!

በዩኒቨርሲቲው የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አስፈጻሚ መምህራን ከፈተና አሰጣጥ ሂደት | Wolaita Sodo University

በዩኒቨርሲቲው የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አስፈጻሚ መምህራን ከፈተና አሰጣጥ ሂደት ጋር የተያያዙ ሕገ-ደንቦችን በተመለከተ ገለጻ (Orientation) ተሰጠ።
_____________
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከሐምሌ 19 እስከ 28/2015 ዓ.ም በሚካሄደው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በአስፈጻሚነት ለተመደቡ ፈታኝ መምህራን ገለጻ (Orientation) ተሰጥቷል።

በመድረኩ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ፈተናውን ለማስፈጸም ወደ ዩኒቨርሲቲው ለተመደቡ ፈታኝ መምህራን አረንጓዴ፣ ጽዱ፣ ሠላማዊ፣ ሕብረ-ብሔራዊ እና ተወዳዳሪ ወደሆነው ተቋም እንኳን በደህና መጣችሁ ብለዋል።

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ መንግስት እየወሰደ ያለውን ቁርጠኛ አቋም እውን ለማድረግ መምህራን የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱ መሆኑን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ የፈተናው ሂደት ፍጹም ሠላማዊ፣ ከደንብ ጥሰት እና ከኩረጃ የጸዳ እንዲሆን ፈታኝ መምህራን ትልቅ ሀላፊነት እንዳለባቸው አሳውቀዋል።

እንደ ሀገር ከገባንበት የትምህርት ጥራት አዘቅት ለመውጣት ፈታኝ መምህራን የተጣለባቸውን ታላቅ ሀገራዊ ሀደራ በሚገባ በመወጣት ትውልድን ከኩረጃ እንዲሁም ከሥነ-ምግባር ዝቅጠት የመታደግ ተልዕኮን ኃላፊነት ወስደው እንዲያስፈጽሙ ፕሮፌሰር ታከለ ጥሪ አቅርበዋል።

በመድረኩ የፈታኝ መምህራን መብትና ግዴታ ምን እንደሆን እንዲሁም ለፈታኝ መምህራን የተከለከሉና የተፈቀዱ ነገሮችን በተመለከተ ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በመጡ የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ ተሰጥቷል።

ፈታኝ መምህራን ወደ መፈተኛ ክፍል እና አካባቢ ስልክ፣ ስማርት ስዓት፣ ማጂክ ብዕር፣ እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት እና ሌሎች ማንኛውንም ፎቶ፥ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን መያዝና መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ በገለጻው ተብራርቷል።

በተጨማሪም ፈታኝ መምህራን ማንኛውንም ዓይነት መጽሐፍት፣ መጽሔት እና ጋዜጣ በመፈተኛ ክፍል ይዞ መገኘት ሆነ መጠቀም የተከለከለ መሆኑ በመድረኩ ተጠቁሟል።

ፈታኝ መምህራን የፈተና ደንብ ጥሰትን የመከላከል ተግባር ላይ በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ጭምር ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

«የፈተና ኩረጃና ስርቆትን በጋራ እንከላከል! ትውልድ ይዳን!»

➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!

➤ ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063820159424

ቴሌግራም፡ https://t.me/WolaitaSUniversity

ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos

ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/

ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09

ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/

ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን