Get Mystery Box with random crypto!

#Exit_Exam # የ3ኛ_ቀን ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ሙከራ ፈተና/National Mock Ex | Wolaita Sodo University

#Exit_Exam

# የ3ኛ_ቀን ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ሙከራ ፈተና/National Mock Exit Exam/ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ!!

በዩኒቨርሲቲው በትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በኦንላይን እየተሰጠ ያለው ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ሙከራ ፈተና ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።

ዛሬ ሰኔ 28/2015 ዓ.ም ዕለተ ረዕቡ ጠዋት እና ከሰዓት በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የሙከራ መልቀቂያ ፈተና 826 ተመራቂ ተማሪዎች ተፈትነዋል።

የሙከራ ፈተናው ዓላማ፦ ተፈታኝ ተማሪዎች የኮምፒውተር አጠቃቀም ክዕሎታቸውን እንዲያዳብሩ በማድረግ ከፈተና መተግበሪያ ሶፍትዌሩ ጋር እንዲለማመዱ ማድረግ፤ ለፈተናው ያላቸውን የዕውቀት እና የሥነ-ልቦና ዝግጁነት ማላቅ፤ ዋናውን የመውጫ ፈተና ስርዓት ቀድመው እንዲረዱት ማስቻል እንዲሁም የተቋሙን የኢንተርኔት አቅርቦት እና አማራጭ በጄኔሬተር የታገዘ የኤሌክትሪክ አቅም ለገምገም እንደሆነ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር አሳውቋል።

እስከ ሰኔ 29/ 2015 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በሚሰጠው ሀገር አቀፍ የሙከራ መልቀቂያ ፈተና (National Mock Exit Exam) በዩኒቨርሲቲው በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 3 ሺሕ 26 ተመራቂ ተማሪዎች እንዲሁም 7 ሺሕ 800 ያህል ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡ የ2015 ዓም ተመራቂ ተማሪዎች የሙከራ ፈተናውን የሚፈተኑ መሆኑን አስተዳደሩ ጠቁሟል።

የ3ኛ ቀን ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ሙከራ ፈተና በሚፈለገው ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ የፈተናው ሂደት በታቀደው አግባብ እንዲሳካ የድርሻቸውን ሚና ለተወጡ ፈተኞች፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ የአይ.ሲ.ቲ እና የኤሌክትሪክ ባለሙያዎች ላደረጉት አስተዋጽኦ አስተዳደሩ ልባዊ ምስጋና አቅርቧል።

ሰኔ 29/2015 ዓ.ም ጠዋት እና ከሰዓት የሙከራ ፈተና መርሃ ግብሩ ሲቀጥል በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞ 699 ያህል ተመራቂ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ የሚሰጠውን ብሔራዊ የሙከራ መልቀቂያ ፈተና ሚወስዱ መሆኑ ተመላክቷል።

➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!

➤ ሰኔ 28/2015 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063820159424

ቴሌግራም፡ https://t.me/WolaitaSUniversity

ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos

ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/

ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09

ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/

ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን