Get Mystery Box with random crypto!

በዩኒቨርሲቲው ለተመደቡ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አስፈጻሚዎች ተቢው ገለጻ (Orientation) | Wolaita Sodo University

በዩኒቨርሲቲው ለተመደቡ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አስፈጻሚዎች ተቢው ገለጻ (Orientation) ተሰጠ።

በፈተና ወቅት የፈተና የስፈጻሚዎች መብትና ግዴታ እንዲሁም የተከለከሉና የተፈቀዱ ነገሮችን በተመለከተ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
_________
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከሐምሌ 19 እስከ 28/2015 ዓ.ም በሚካሄደው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በአስፈጻሚነት ለተመደቡ የፈተና ማዕከል ኃላፊ፣ የፈተና የጉድኝነት ማዕከል አአስተባባሪ፣ የፈተና ጣቢያ ኃላፊ እና ሱፐርቫይዘሮ ገለጻ (Orientation) ተሰጥቷል።

በመድረኩ የተፈታኞችና የፈተና አስፈጻሚዎች መብትና ግዴታ እንዲሁም አጠቃላይ የተከለከሉና የተፈቀዱ ነገሮችን በተመለከተ ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በመጡ የሥራ ኃላፊዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ማዕከል ኃላፊ፣ የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ፣ ጣቢያ ኃላፊ፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ ፈታኝ፣ የዓይነ ስውር ተፈታኝ አንባቢ፤ የፊተና ግብአቶች ቆጣሪ እና ሌሎች የፈተና ግበረ ኃይል አባላት ወደ መፈተኛ ክፍል እና አካባቢ ስልክ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር፣ እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት እና ሌሎች ማንኛውንም ፎቶ፥ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን መያዝና መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ በመድረኩ ተብራርቷል።

በፈተና አስፈጻሚነት የተመደበ ማንኛውም ፈታኝ፤ ሱፐርቫይዘርና የፈተና ግብአቶች አደራጅ ማንኛውንም ዓይነት መጽሐፍት፣ መጽሔት እና ጋዜጣ በመፈተኛ ክፍል ይዞ መገኘት ሆነ መጠቀም የተከለከለ መሆኑም ተመላክቷል።

ለፈተና ደህንነት መረጋጥጥ አጋዥ በሆኑ አካሄዶች እንዲሁም የደንብ ጥሰት መከላከልን በተመለከት ሠፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፤ ፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና ደንብ ጥሰትን የመከላከል ተግባር ላይ በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል፡፡

➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!

➤ ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063820159424

ቴሌግራም፡ https://t.me/WolaitaSUniversity

ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos

ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/

ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09

ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/

ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን