Get Mystery Box with random crypto!

የማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች–የ2ኛ ቀን ቅበላ!! በጥብቅ የ | Wolaita Sodo University

የማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች–የ2ኛ ቀን ቅበላ!!

በጥብቅ የፍተሻ ሥርዓት ማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች አሁንም በመግባት ላይ ይገኛሉ።

በዩኒቨርሲቲው ከሐምሌ 19 እስከ 21/2015 ዓ.ም በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 19 ሺሕ 324 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ይፈተናሉ።

ሐምሌ 18/2015 ዓ.ም ለተፈታኞች ፈተናውን በትመለከተ አጠቃላይ የሥነ ምግባር ደንብ ላይ ያተኮረ ገለጸ ይሰጣቸዋል።

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን በሚውስዱበት ጊዜ የፈተናውን ህግና ስርዓት እንዲያከብሩ በጥብቅ አሳስቧል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተናው ግልጋሎት ከሚሰጡ የፅህፈት መሳሪያዎች እርሳስ፣ ላጲስ፣ መቅረጫ እና ስክቢቶ ውጭ ወደ ፈተና ክፍል ይዞ መግባት ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን እንዲያውቁትም አሳስቧል።

ውድ የ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች እንኳን አረንጓዴ፣ ጽዱ፣ ሠላማዊ፣ ተወዳዳሪ እና ሕብረብሔራዊ ወደሆነው ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በደህና መጣችሁ።

የ12 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ቆይታችሁ ወደሚያበቃበትና አዲስ ሌላ የሕይወት ምዕራፍ ወደሚጀመርበት ጊዜ እንኳን አደረሳችሁ በማለት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

መልካም ፈተና

«የፈተና ኩረጃና ስርቆትን በጋራ እንከላከል! ትውልድ ይዳን!»

➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!

➤ ሐምሌ 16/2015 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063820159424

ቴሌግራም፡ https://t.me/WolaitaSUniversity

ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos

ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/

ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity?t=w_VzjrOWj3D3Mc8BKlQFXA&s=09

ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/wolaita-sodo-university/

ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን