Get Mystery Box with random crypto!

የዛሬ መረጃ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የሰርጥ አድራሻ: @todaynewsethiopia
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.26K
የሰርጥ መግለጫ

#መረጃ_አይናቅም ‼️
ትኩስ ና አዳዲስ የሀገር ውስጥ ና የአለም ዜናዎችን በፍጥነት ሰብስበን ወደናንተ እናደርሳለን Today News Ethiopia።
መረጃዎች ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ አብሮነታችሁ ያሳዩ
#ለእውነት ና #ለትክክለኛ #መረጃ ብቻ እንሰራለን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-07 19:39:11
አጭር ባል እና ረጅም ሚስት ሪከርድ

ሌንሣ ጩሎ እና በራቆ ሙዳ በአጭር ባል እና ረጅም ሚስት ዘርፍ ተይዞ የነበረውን የዓለም ሪከርድ ሰብረውታል፡፡ ሌንሳ ጩሎ 165 ሴ.ሜትር ስትሆን በራቆ ሙዳ ደግሞ 89 ሴ.ሜትር ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የአፍሪካ ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

http://t.me/TodayNewsEthiopia
6.9K views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 21:56:38 የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት  በሸገር ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ የሚገኘው የመሰጂዶች ፈረሳ በአሰቸኳይ እንዲቆም አሳሰበ

በኦሮሚያ ክልል "በሸገር ሲቲ" እየፈረሱ ያሉት መሰጂዶች በአሰቸኳይ እንዲያስቆም ለኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ደብዳቤ   መጻፉን አስታውቋል።በጠቅላይ ምክር ቤቱ በደብዳቤ፤ በኦሮሚያ ብሔራዊ  ክልላዊ መንግሥት እየፈረሱ ያሉ መስጂዶች በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ ጠይቋል።

የፈረሱ መስጂዶች በሸገር ከተማ አስተዳደር በፍጥነት እንዲሰሩና ሕዝበ ሙስሊሙን አስተዳደሩ በይፋ ይቅርታ መጠየቅ እንዳለበት በፃፈው ደብዳቤ አሳስቧል።የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለጠቅላይ ምክር ቤቱ በተፃፈው ደብዳቤ መሠረት:-

1.በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ዉንዴሳ ወረዳ ልዩ ሥፍራ ቀርሳ በቀን 14/07/15

2. በሸገር ከተማ ሰበታ ክፍለ ከተማ መጉላ ቶውፊቅ መስጂድ 19/08/15

3. በሸገር ከተማ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ወረዳ ልዩ ስሙ አን ኢ ሳይት ሰላም መስጂድ  በቀን 24/08/25

4. በሸገር  ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ አሸዋ ሜዳ በቀን 25/08/15 መፍረሳቸውና ጉዳዩ ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ደብዳቤ መጻፉም ተገልጿል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
7.2K views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 13:22:50
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በ27ኛ ዙር ያሠለጠናቸውን የመደበኛ እና አድማ ብተና የፖሊስ አባላትን አስመረቀ

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ለፖሊስ አባላቱ የሥራ መመሪያ በመስጠት ወደ ሥራ አሰማርተዋል።

“መጪው ጊዜ ሕዝባችሁን በቅንነት እና በታማኝነት የላቀ አገልግሎት የምትሰጡበት እንደሚሆን እምነት አለኝ” ያሉት ከንቲባ አዳነች፣ ፖሊሶቹ ወደ ተግባር ሲገቡ ሕዝባቸውን በእኩልነት በማገልገል የማይለካ ክብር እንደሚያገኙም ጠቁመዋል።

የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በበኩላቸው፣ ከራስ በላይ ሕዝብን በማስቀደም በማንኛወም ቦታ እና ሁኔታ በቅንነት፣ ሁሉንም በፍቅር በእኩልነት በማገልገል ከፖለቲካ፣ ከሃይማኖት፣ ከብሔር ወገንተኝኘት በመጠበቅ በታማኝነት ማገልገል ሁሌም መዘንጋት የሌለባቸው ተቀዳሚ ተግባራቸው እንዲሆን አሳስበዋል።

ተመራቂ የፖሊስ አባላቱ በከተማዋ የሚፈፀሙ ውስብስብ ወንጀሎችን በመረዳት ቀድመው ለማክሸፍ በአካልም ሆነ በሥነ ልቦና ጠንካራ እንዲሆኑ አዳዲስ ፖሊሳዊ ሥልጠናዎችን መውሰዳቸው ተጠቁሟል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል መላኩ ፋንታ፣ የከተማ አስተዳደሩ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች፣ የፖሊስ አካዳሚ ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር መኮንን አሻግሬ እንዲሁም በኮሚሽኑ ከፍተኛ የፖሊስ አመራሮች ተገኝተዋል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
7.3K views10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 23:12:54
መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በአማራ ክልል ላሉ ውጥረቶች በቂ ትኩረት ይስጡ

የኢሰመጉ አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ-ሚያዚያ 27/2015 ዓ.ም
6.9K views20:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 23:59:33
አእምሮን በመቀየር ህይወቶን ይቀይሩ።

ለውጥን ከልባቸው ለሚፈልጉ ሰዎች የቀረበ እራሳችሁን ከማይፈልጓቸው ልምዶች፤በገቢ፤በአመለካከት ሊያድጉበት የሚችሉት ትልቅ እድል


ለውጥን ከልቡ የሚፈልግ ብቻ
ለመጠቀም ወደሚቀጥለው ገፅ ይቀላቀሉ።


https://t.me/+RbSAK0r6u8ZhNTRk
https://t.me/+RbSAK0r6u8ZhNTRk
1.4K views20:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 10:19:26 ሰበር ዜና

ግብረ ኃይሉ “በአማራ ክልል ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ኃይሎች ላይ እርምጃ እየወሰደኩ ነው” አለ!!

የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል “በአማራ ክልል ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ እርምጃ እየወሰድኩ ነው” አለ።

የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ባወጣው መግለጫ፤ ለአማራ ሕዝብ እንታገላለን በሚል በውስጥም በውጭም በመቀናጀት የራሳቸውን ህቡዕ አደረጃጀት የፈጠሩ አካላት ከመሰል ቡድኖች ጋር በመቀናጀት የሕዝቡን የቁርጥ ቀን ልጆች መልሰው እየበሉ ይገኛሉ። “እነዚህ ኃይሎች በትናንትናው ዕለትም የአማራ ክልል ብልፅግና ጽሕት ቤት ኃላፊ የሆነውን ግርማ የሺጥላን በመግደል አስነዋሪ ድርጊታቸውን አስመስክረዋል” ብሏል ግብረ ኃይሉ።

“በአማራ ክልል ሕገመንግስታዊ ሥርዓቱን በማፍረስም ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠርም ሲጥሩ መቆየታቸውን” መግለጫው አመላክቷል።

የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይልም ይህን ተከትሎ አስፈላጊና ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ነው የገለጸው።

ይሄ ጽንፈኛ ኃይል በአማራ ክልል ሳይገደብ እንደ ሀገርም መንግስትን በኃይል ከስልጣን ለማስወገድ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም ያለው የጋራ ግብረ ኃይሉ መግለጫ÷ ከዚህ የጥፋት መንገዳቸው እንዲመለሱ በተደጋጋሚ የተሰጣቸውን ዕድል ከመጠቀም ይልቅ አሁንም በሕ ገወጥ ተግባራቸው መቀጠላቸውን አመልክቷል፡፡

በዚህ ህገ ወጥ ተግባራቸውም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በሕግ እየታየ የሚገኙ በርካታ የቡድኑ አባላት መኖራቸውንም ግብረ ኃይሉ አስታውቋል፡፡ መንግስት በሀገሪቱ ብሎም በክልሉ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ በሌሎቸም የሕገ ወጥ ቡድኑና ቡድኑን በገንዘብና በሐሳብ በህቡእ በሚደግፉ አካላትና ግለሰቦች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ነው ያስታወቀው፡፡

በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ የፅንፈኛ ቡድኖቹ ደጋፊዎች በዚህ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጅ ላይ የተፈፀመውን ግድያ ከመኮነን ይልቅ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ገዳይ ቡድኖቹን ሲደግፉ ተስተውለዋል ብሏል መግለጫው፡፡ሐሳብን በሐሳብ ከማሸነፍ ይልቅ ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት ባፈነገጠ መልኩ በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ የፈጸሙትን ፅንፈኛ ቡድኖች ሕዝቡ በአንድነት በማውገዝ ኢትዮጵያዊ ጨዋነቱን ሊያስመሰክር ይገባልም ብሏል፡፡

በአቶ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ የፅንፈኛ ኃይሎቹን ትክክለኛ መልክና ገፅታ ለሕዝቡ በይፋ ያጋለጠ ነው ብሏል የደኅንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ኃይል፡፡ መንግስት ለሕዝቡ ሰላምና ደኅንነት መረጋገጥ ግዴታውን ለመወጣት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ የጀመረ በመሆኑ÷ ሕዝቡም ይሄንን ተገንዝቦ የፌደራል እና የክልል የፀጥታ አካላት ተጠያቂነትን ለማስፈን የጀመሩትን እንቅስቃሴ ጥቆማና መረጃ በመስጠት እንዲደግፍ ጥሪ አቅርቧል፡፡ የፅንፈኛ ኃይሎቹን አስነዋሪ ተግባር በመሸፋፈን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች መሰረተ ቢስ ወሬዎችን ከሚያሰራጩ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ሕብረተሰቡ ራሱን እንዲጠብቅ ግብረ ኃይሉ አሳስቧል፡፡

http://t.me/TodayNewsEthiopia
4.5K views07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 22:26:28 በሱዳን የተኩስ አቁም ስምምነቱ ቢራዘምም ውጊያው ቀጥሏል!

የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ተኩስ አቁሙን ለማራዘም የተስማሙ ቢሆንም ትናንት ተዋጊ ጄቶች ዋና ከተማዋ ካርቱም ያሉ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ይዞታዎች ደብድበዋል።

የጦር ሰራዊቱ እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በተደጋጋሚ ሲጣስ የነበረውን የተኩስ አቁም እንዲያራዝሙ ሳውዲ አረቢያ እና ዩናይትድ ስቴትስ ግፊት ማድረጋቸውን ተከትሎ ጥቂት ሰዐት ሲቀረው በተጨማሪ 72 ሰዐት ለማራዘም መስማማታቸውን ይፋ አድርገዋል።

ውጊያው እንዲቆም ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ የውጭ አካላት ተወካዮች በተኩስ አቁሙ መራዘም መደሰታቸውን ገልጸዋል።የአፍሪካ ህብረት፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፥ ሳውዲ አረቢያ፥ የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች፥ ብሪታኒያ እና ዩናይትድ ስቴትስ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

"ሁለቱ ወገኖች ይበልጡን ዘላቂ በሆነ መንገድ ግጭቱ እንዲቆም ወደሚያስችል ንግግር ለማምራት ብሎም የሰብዐዊ ረድዔት ያለእንቅፋት መግባት ለማስቻል ዝግጁ መሆናቸው አስደስቶናል" ብለዋል።በተያያዘ ዜና ትናንት ተዋጊ አውሮፕላኖች በዋና ከተማዋ ሰሜናዊ ጠርዝ አካባቢ ሲበሩ እንደነበር የመድፍ እና የከባድ አውቶማቲክ መሳሪያ ተኩስም ይሰማ እንደነበር ዕማኞች ገልጸዋል።

ነገ ቅዳሜ ሁለት ሳምንት በሚደፍነው የሱዳን ውጊያ ቢያንስ 512 ሰዎች ሲገደሉ 4193 መቁሰላቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚንስቴር መረጃ ያሳያል።ዳርፉር ውስጥም ውጊያው ማገርሸቱን ዘገባዎች አመልክተዋል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
4.9K views19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 11:20:23
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች መሪዎች ጋር በስልክ ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ጦር ኃይሎች መሪ ጄኔራል አብደልፈታህ አልቡርሃን እና ከሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መሪ ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ደጋሎ ጋር በስልክ መወያየታቸውን ገለጹ።

ታላቁ የሱዳን ሕዝብ ሰላም ያስፈልገዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሁለቱ መሪዎች ልዩነቶቻቸውን በመግባባት እንዲፈቱ እና ለሀገራቸው መረጋጋትን ማምጣት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
5.9K viewsedited  08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 11:57:09 ሰበር ዜና
በታንዛኒያ ዛንዚባር ደሴት በኢትዮጵያ መንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የሰላም ውይይት ዛሬ ተጀመረ።

በታንዛኒያ የሰላም ድርድር ዛሬ ማለዳ መጀመሩን በስፍራው የነበሩ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በውይይቱ ላይ የሁለቱም ወገኖች ተወካዮች ስድስት ሰዎች እየተሳተፉ መሆናቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በመንግስት በኩል ወደ ታንዛኒያ የተጓዘው የልዑካን ቡድን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ እንደሚገኙበት ቢቢሲ ዘግበዋል።

በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በኩል አንጋፋው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር መሃመድ ሃሰን እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ዋና አዛዥ አማካሪ ሚስተር ጂሬኛ ጉዳታ እና አቶ አብዲ ጠሃ እና ሌሎችም መገኘታቸውን ፋስት መረጃ ከቢቢሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ሁለቱም ተደራዳሪ አካላት ንግግር ስለመጀመሩ ማረጋገጫ ቢሰጡም ዝርዝር መረጃ ይፋ አላደረጉም ፤ የታንዛኒያ ባለስልጣናትም ስለድርድሩ የተለየ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

 
4.4K views08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 14:41:53
ደስተኛ ናችሁ?

ለመሆን ምንድን ነው የጎደለባችሁ?

ኑ የህይወት አላማችሁን እወቁ ዋጋ ያላችሁ ሰው ሆናችሁ መኖር ጀምሩ ባላችሁ Time ጥሩ ገቢ የሚያመጣ ቢዝነስ አብረን እንስራ።

ፍላጎት ብቻ ያላችሁ ኑ በቴሌግራም ያዋሩኝ

T.me//MyDream51
5.4K views11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ