Get Mystery Box with random crypto!

የዛሬ መረጃ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የሰርጥ አድራሻ: @todaynewsethiopia
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.26K
የሰርጥ መግለጫ

#መረጃ_አይናቅም ‼️
ትኩስ ና አዳዲስ የሀገር ውስጥ ና የአለም ዜናዎችን በፍጥነት ሰብስበን ወደናንተ እናደርሳለን Today News Ethiopia።
መረጃዎች ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ አብሮነታችሁ ያሳዩ
#ለእውነት ና #ለትክክለኛ #መረጃ ብቻ እንሰራለን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-03-24 16:08:21
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በክልሉ ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል

በዚህም መግለጫቸው ፤ " የትግራይ ህዝብ እራሱን ከጥፋትና ውድመት ለማዳን ሁሉንም አይነት መስዋዕትነት ከፍሏል። " ያሉ ሲሆን " ጊዜያዊ አስተዳደሩም የትግራይ ህዝብ የታገለለትንና መስዋእትነት የከፈለበትን ዓላማ ለማሳካት ይሰራል " ብለዋል።

አቶ ጌታቸው አስተዳደራቸው የትግራይን ግዛታዊ አንድነትን ማረጋገጥ፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቄያቸው መመለስ እና የህዝቡን ሁለንተናዊ ችግሮች በፍጥነት መፍታት ዋነኛው አላማው አድርጎ እንደሚሰራ በሰጡት መግለጫ መናገራቸውን ከክልሉ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
1.1K views13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 14:41:34
በሐረር ከተማ ማብቂያ ያጣው የባጃጅ ላይ ዘረፋ ባለ ተስፋዋን ወጣት ሕይወት ቀጥፏል።

ረቡዕ መጋቢት 13/2015 አመሻሽ 1:30 አካባቢ ወጣት የኔወርቅ አበበ ከማታ የትምህርት ገበታዋ ከጓደኞቿ ጋር በመመለስ ላይ ሳለች በተለምዶ ሞቢል ተብሎ በሚጠራው ሰፈር በሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) የዝርፊያ ተግባር በሚፈፅሙ ሌቦች አማካኝነት የእጅ ስልኳንና ቦርሳዋን ተነጥቃ፣ ወደ አስፓልት በመገፍተሯ በተቃራኒ መንገድ በሚመጣ መኪና ይሁን በዘራፊዎቹ ባጃጅ ተሽከርካሪ ባልታወቀ ሁኔታ ክፉኛ ተገጭታ የሞት ሰለባ ሆናለች።

በአቅራቢያ ወደሚገኘው ሐረር ጠቅላላ ሆስፒታል በፍጥነት ቢደረስም ከደረሰባት ጉዳት አንፃር ሕይወቷን ማትረፍ አልተቻለም።

ወጣት የኔወርቅ አበበ በ2014 ዓ.ም ከሐረር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአካውንቲንግና ፋይናንስ በዲፕሎማ ተመርቃ በቅርቡ በሐረር መምህራን ማሠልጠኛ ተቋም ትምህርቷን ለማሻሻል በዲግሪ መማር ከጀመረች 3 ቀናት ብቻ እንደተቆጠሩ በሚያሳዝን ሁኔታ ይህችን ዓለም ተሰናብታለች።

ስርዓተ ቀብሯም መጋቢት 14/2015 ዓ.ም በትውልድ ሐገሯ ጉርሱም ከተማ ይፈፀማል።

ፈጣሪ አምላክ ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጅ ዘመዶቿ በእጅጉ መፅናናትን እንዲሰጥልን እመኛለው

#ነፍስሽ_በሠላም_ትረፍ
ሙላው ገ/ሕይወት
ሐረር/ኢትዮጵያ

http://t.me/TodayNewsEthiopia
2.9K views11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 18:59:20 ረመዳን ሙባረክ

በሳውዲ አረቢያ የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ ባለመታየቷ የረመዳን ወር ሐሙስ መጋቢት 14 አንድ ብሎ እንደሚጀምር ታውቋል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
3.0K views15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 18:09:33 የረመዷን ፆም ዛሬ ጨረቃ ከታየች ነገ፣ ካልሆነ ግን ከነገ በስቲያ ይጀምራል

የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት

የ1444ኛው ዓመተ ሒጅራ የረመዷን ፆም ማክሰኞ (ዛሬ) ጨረቃ ከታየች ረቡዕ (ነገ)፣ ካልሆነ ግን ሐሙስ (ከነገ በስቲያ) እንደሚጀምር የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አስታወቀ። 

ፍርድ ቤቱ የ1444ኛው ዓመተ ሒጅራ የረመዷን ፆምን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል። 

"ለመላው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እንኳን ለ1444ኛው ዓመተ ሒጅራ የረመዷን ጾም በሰላም አደረሳችሁ፤ ለዚህ የተከበረ ታላቅ ወር ረመዷን በሰላም ላደረሰን አላህ ምስጋና እናቀርባለን" ብሏል ፍርድ ቤቱ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ። 

ሕዝበ ሙስሊሙ የተለመደ የእርስ በርስ መደጋገፍ እና መረዳዳት ተግባሩን በፆሙ ወቅት ይበልጥ አጠናክሮ እንዲቀጥልበት ፍርድ ቤቱ ጥሪ አቅርቧል። 

ለመላው ኢትዮጵያውያን እና የዓለም ሙስሊሞች ወሩ የጤና፤ የሰላምና የፍቅር እንዲሆን ፍርድ ቤቱ መልካም ምኞቱን ገልጿል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
3.4K views15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 15:17:55 የኢትዮጵያ መንግሥት በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የቀረበበትን የሰብአዊ መብት ጥሰት ክስ በፍፁም አይቀበልም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተከስቷል ሲል የደረሰበትን ድምዳሜ የኢትዮጵያ መንግሥት በፍፁም እንደማይቀበለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ጉዳዩን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር በጋራ ካደረጉት ምርመራ አንፃር ሲታይ ምንም አዲስ ግኝት ያልተካተተበት ነው ብሏል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያቀረበበትን ባዶ ውግዘት በፍፁም እንደማይቀበለው ገልጿል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ያወጣው መግለጫ አንድን ወገን ብቻ መወንጀል ላይ ያነጣጠረ መሆኑንም ነው ሚኒስቴሩ በመግለጫ የጠቆመው።
3.8K views12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 20:32:25 Good News
በማንኛውም እድሜና ፆታ ላሉ የሚሆን እድል።

በይበልጥ 12ተኛ ክፍል ውጤት ላልመጣላችሁ እራሳችሁ ላይ እየሰራችሁ በሙሉ ጊዜአችሁም ሆነ በትርፍ ጊዜአችሁ ቢዝነስ መስራት ለምትፈልጉ በማንኛውም ሀገር ለምትኖሩ ሰዎች የቀረበ ድንቅ እድል።


ይህን እድል ተጠቃሚ ለመሆን ይመዝገቡ
ሙሉ ስም
ስልክ ቁጥር
የመኖሪያ አድራሻ
@MyDream51 ይላኩልን።
4.9K views17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 13:23:07
አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ በህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ አብላጫ ድምፅ ማግኘታቸው ተነገረ።

የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አድርጎ ነበር። በዚህም አቶ ጌታቸው ረዳን በትግራይ ክልል ለሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንታዊ እጩ አድርጎ አብላጫ ድምጽ መስጠቱን ቅርበት ያላቸው የፓርቲው ምንጮች እንደገለፁለት የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ (ቪኦኤ) የትግርኛው አገልግሎት ክፍል ዘግቧል።

የአቶ ጌታቸው ረዳና ሌሎች የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ኣባላት ሹመት፣ የክልሉ አመራሮች ከፌደራሉ መንግሥት ጋር በጊዜያዊ አስተዳደሩ አወቃቀር ጉዳይ ተወያይተው ካፀደቁት በኋላ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥራ እንደሚጀምር ነው ' ቪኦኤ ትግርኛ ' ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ በዘገባው ያመለከተው።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
3.9K viewsedited  10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 19:46:40 ከብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

ኢትዮጵያ ሀገራችን ወደ ታላቅ ምእራፍ በምትሻገርበት ድልድይ ላይ ትገኛለች፡፡ አንዳንዶች ከድልድዩ ወደኋላ ሊመልሷት ይታገላሉ፡፡ ሌሎቹ ድልድዩን ሰብረው ገደል ሊከቷት ይለፋሉ፡፡

ታጋይ ልጆቿ ደግሞ በድልድዩ ላይ ብዙ ሳትቆይ ወደፊት እንድትራመድ ለማድረግ ይታገላሉ፡፡ ብልጽግና ሦስተኛውን መርጧል፡፡

ድልድይ ያለፈውን መንገድ ያህል ጠንካራ አይሆንም፡፡ ገደሉን ለመሻገር ግን የግድ ነው፡፡ ረዥም ጊዜ በድልድዩ ላይ መቆየትም አደጋ አለው፡፡ በቶሎ መሻገርና ወደጸናው መሬት መድረስ አስፈላጊ ነው፡፡ ያለንበት የሽግግር ጊዜም የሚነግረን ይሄንን ነው፡፡ የሽግግሩ ወቅት ዓላማው በዚያው መቆየት ሳይሆን ወደ በለጸገች ኢትዮጵያ መሸጋገሪያ ነው፡፡ እየገጠሙን ያሉትም የሽግግር ጊዜ ፈተናዎች ናቸው፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከመጋቢት 7- 8 ባደረገው ስብሰባ ኢትዮጵያ ካለፈው መንገድ የመጣችበትን፣ ወደ ብልጽግና ለመሻገር በድልድዩ ላይ የቆየችበትን፣ በድልድዩ ላይ በቆየችባቸው ወቅቶች የገጠሟትን ፈተናዎች፤ ከድልድዩ ወደኋላ ለመመለስ የሚታገሏትን ኃይሎች፣ ድልድዩን ተሻግራ ወደ ብልጽግና እንዳትሸጋገር ያጋጠሟትን ተግዳሮቶች በዝርዝር መርምሯል፡፡

አሁን እያጋጠሙን ያሉ ፈተናዎች በዋናነት ከአምስት ነገሮች የመጡ መሆናቸውን የፓርቲያችን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አምኗል፡፡ ለእነዚህም ተገቢ ነው ያለውን የትግል ስልት ቀይሷል፡፡
2.2K views16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 06:37:02
Today is not just another day. It's a new opportunity, another chance, a new beginning. Embrace it.

Have a good day

Join us and become a family

T.me//TesfamichaelAsefa
3.7K views03:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 15:22:27 አሜሪካ የሰላም ስምምነቱ ሙሉ ተግባራዊነትን ተከትሎ ኢትዮጵያን ወደ አጎዋ ለመመለስ ቁርጠኛ መሆኗን አንቶኑ ብሊንከን ገለጹ

አንቶኒ ብሊንከን በአዲስ አበባ ቆይታቸው በተለይም ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በቃለመጠይቁም ዩናይትድ ስቴትስ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅንጅት እየሰራች መሆኑን ነው የገለፁት።

ይህም አሜሪካ፥ ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚ እና በሌሎች ዘርፎች ላይ ያላትን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚያበረታታ ተናግረዋል።

የሰላም ስምምነቱ በሚመለከታቸው አካላት ሙሉ በሙሉና ዘላቂነት ባለው መልኩ ተግባራዊ ሲደረግም አሜሪካ ኢትዮጵያን ምርቶቿን ከኮታና ቀረጥ ነፃ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንድታስገባ ወደ ሚፈቅደው የአጎዋ ተጠቃሚነት ዳግም ለመመለስ ቁርጠኛ ናት ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕን ለመተግበር የጀመረችውን ጥረት ያደነቁት አንቶኒ ብሊንከን፥ የሰላም ስምምነቱ ትግበራ ሒደት በጥሩ ሁኔታ እየተፈጸመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
4.7K views12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ