Get Mystery Box with random crypto!

የዛሬ መረጃ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የሰርጥ አድራሻ: @todaynewsethiopia
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.26K
የሰርጥ መግለጫ

#መረጃ_አይናቅም ‼️
ትኩስ ና አዳዲስ የሀገር ውስጥ ና የአለም ዜናዎችን በፍጥነት ሰብስበን ወደናንተ እናደርሳለን Today News Ethiopia።
መረጃዎች ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ አብሮነታችሁ ያሳዩ
#ለእውነት ና #ለትክክለኛ #መረጃ ብቻ እንሰራለን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 41

2022-08-26 08:25:49 በአዲስአበባ የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለቀጣይ ስድስት ወራት ተራዘመ!!

የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የኑሮ ጫናን ለመቀነስ በመኖርያ ቤት ተከራዮች ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራይን ማስለቀቅን የሚከለክል ደንብ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ይህም ደንብ በተለያየ ጊዜ እየተራዘመ ላለፈው አንድ አመት ተግባራዊ ተደርጎ ቆይቷል፡፡

ስለሆነም የከተማ አስተዳደሩ አሁን ያለውን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ እና የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ከግምት ባስገባ ወቅቱን በአብሮነትና በመተሳሰብ ለማለፍ ይረዳ ዘንድ ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት እንዲራዘም ወስኗል፡፡በመሆኑም ይህንን ክለከላ በመተላለፍ ተከራዮችን የሚያስወጡ እና የኪራይ ዋጋን የሚጨምሩ አካላት ላይ ማህበረሰቡ በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች ጥቆማውን ለከተማ አስተዳደሩ ማድረስ እንደሚችል ያስታውቃል፡፡
አጭር ቁጥር ፡- 9977

የሞባይል ስልኮች

09-00640830 / 09-00640789

https://t.me/TodayNewsEthiopia
9.9K views05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 22:30:19 ለ 3 ሰዎች ብቻ

በጣም በህይወቴ የጎደሎነት ስሜት ይሰማኛል የሆነ በህይወቴ ደስተኛ መሆን አልቻልኩም አንገብጋቢ መቀየር የምፈልገው አለ ለሚል ለዛሬ 3 ሰዎች Online ነኝ ያማክሩኝ።

@life_of_tesfshi
8.9K views19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 21:38:53
አሸባሪው ህወሓት ቡድን ወደ ትግራይ ክልል ሊያስገባ የነበረው አደገኛ ዕፅ ተያዘ

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ከአዲስ አበባ እስከ ሚሌ ኔትወርክ በመዘርጋት በአፋር ክልል በኩል ወደ ትግራይ ክልል ሊያስገባው የነበረ በርካታ ኩንታል አደገኛ ዕፅ በህብረተሰቡ ጥቆማ እና በፖሊስ ብርቱ ክትትል ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም መያዙን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

https://t.me/TodayNewsEthiopia
9.3K views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 15:59:01 ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተገነቡ ሕንፃዎችን ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች አስተላለፉ

የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ለሚኖሩ አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የተገነባውን “80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፕሮጀክት” ለአካባቢው አቅመ ደካማ ነዋሪዎች በዕጣ አስተላልፈዋል፡፡
ሕንፃዎቹ ለነዋሪዎቹ የተላለፉት ነዋሪዎቹ ቀደም ሲል እንደ ነበራቸው የመኖሪያ ቤት ሥፋትና መጠን መሠረት ነውም ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ከንቲባዋ በልቤ ፋና ትምህርት ቤት በመገኘት ያስገነቧቸውን ሁለት ተጨማሪ ሕንጻዎች ማስረከባቸውን ከከንቲባ ጽኅፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡

https://t.me/TodayNewsEthiopia
4.3K views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 15:39:22
የብዙ ሰዋች የትዳር (የፍቅር) መፍረስ የሆነው የስንፈተ ወሲብ ችግር ዘላቂ መፍትሄ በሀገራችን አስመጥተናል።

ዶ/ር ዮናስ አጠቃላይ የስንፈተ ወሲብ አማካሪ

ፍቱን የተመሰከረላቸው ኦርጅናል የስንፈተ ወሲብ መድሀኒቶችን ከኛጋ ያገኛሉ።

በሰዎች ላይ ተሞክረው ፈጣን ና ዘላቂ መፍትሄ ያመጡ ኦርጂናል የስንፈተ ወሲብ መድሀኒቶችን በክሬም ና በታብሌት አማራጭ በተመጣጣኝ ዋጋ በመሸጥ ላይ እንገኛለን።

ይደውሉ +251903970404

በወሲብ ወቅት ቶሎ የመጨረስ ችግር በዘላቂነት የሚቀርፍ።

የብልት መጠን ማነስ ችግር በዘላቂነት መጠንን የሚጨምር።

በወሲብ ወቅት የብልት አለመቆም (ጥንካሬ) የማጣጥ ችግርን በዘላቂነት የሚቀርፉ ።

ዋና ማከፋፋያችን አ.አ በተለያዩ ክልል ከተሞች ሰዋች አዘጋጅተናል ይዘዙን ባሉበት ቦታ ሆነው ያገኛሉ።

ተጨማሪ ይመልከቱ
https://t.me/TY_ShopCenter
1.1K views12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:58:14 በቀጣይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ የሕዝብ ተሳትፎና የጥራት ማረጋገጫ መንገዶችን በተከተለ መንገድ ይፈጸማል ተባለ

በቀጣይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ሂደት የኅብረተሰቡን ተሳትፎ ባገናዘበና ተገቢነት ባለው እንዲሁም የጥራት ማረጋገጫ መንገዶችን በተከተለ መንገድ እንደሚፈፀም ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ ገለጹ፡፡

ኃላፊው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ እንዳስታወቁት በ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሐምሌ 01 ቀን 2014 እጣ አወጣጥ ላይ የተገኘውን ግኝት ተከትሎ ከተማ አስተዳደሩ የወሰደው ፈጣን እርምጃ ፍትሕን ከማስፈን አኳያ ተገቢነት ያለው ውሳኔ ነው፡፡

የማጣራት ሥራው በሚመለከታቸው ተቋማት እና ከፍተኛ እውቀት ባላቸው ባለሙያዎች የተከናወነ ሥራ መሆኑም የግኝቶቹን ተአማኒነት ከፍ እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ ለሚከናወኑ የእጣ አወጣጥ ሥራዎች የኅብረተሰቡን ተሳትፎ ባገናዘበና ተገቢነት ባለው እንዲሁም የጥራት ማረጋገጫ መንገዶችን በተከተለ መንገድ እንደሚፈፀም ሁሉም ሊገነዘበው እንደሚገባ ገልጸው ለተግባራዊነቱም እንተጋለን ብለዋል፡፡

https://t.me/TodayNewsEthiopia
5.1K views09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 20:31:18 አይቀርም ምሽት 3 ሰአት ላይ
በታዎቂው የአርቲስቶች መንደር የ Telegram ገፅ
የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልሶች ይደረጋሉ የተለያዩ የሞባይ ካርድ ሽልማቶችም አሉ።

እርሶስ ምን ይጠብቃሉ ሊንኩን ጠቅ አድርገው ይሳተፉ።
https://t.me/instagrame_pictures
7.0K views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 20:03:53 አስተዳደሩ ባወጣው የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ በማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አመራሮችና ሰራተኞችን ዝርዝር ይፋ አደረገ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ እና ከቤቶች ቢሮ በማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አመራሮችና ሰራተኞችን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡

የተጠረጠሩ አመራሮችና ሰራተኞች ስም ዝርዝርም እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

1. ዶ/ር ሙሉቀን ሃብቱ- የቢሮ ሃላፊ፣ ከሃላፊነቱ የተነሳ

2. አብርሀም ሰርሞሎ -የዘርፉ ምክትል ቢሮ ሃላፊ

3.መብራቱ ወልደኪዳን -ዳይሬክተር

4. ሀብታሙ ከበደ -ሶፍትዌር ባለሙያ

5. ዬሴፍ ሙላት-ሶፍትዌር ባለሙያ

6. ጌታቸው በሪሁን -ሶፍትዌር ባለሙያ

7. ቃሲም ከድር- ሶፍትዌር ባለሙያ

8. ስጦታው ግዛቸው- ሶፍትዌሩን ያለማ

9. ባየልኝ እረታ - ሶፍትዌር ተቆጣጣሪ

10. ሚኪያስ ቶሌራ- የቤቶች ኢንፎሜሽን ና ቴክኖሎጂ ባለሙያ

11.ኩምሳ ቶላ የቤቶች ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳሬክተር

https://t.me/TodayNewsEthiopia
7.0K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 14:04:23 የባልደራስ ፕሬዚዳንት እስክንድር ነጋ የአሜሪካ ጉብኝታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ

በአሜሪካ ለሁለት ወራት ቆይታ ያደረጉት የባልደራስ ፕሬዚዳንት እስክንድር ነጋ፣ ዛሬ፣ ሐምሌ 6 2014 ወደ ኢትዮጰያ ተመልሰዋል።ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ሲደርሱ የድርጅቱ አመራር አባላት አቶ ነብዩ ውብሸት እና ቀለብ ስዩም(አስቴር) እንደተቀበሏቸው ፓርቲው በትስስር ገፁ አጋርቷል፡፡

በአሜሪካ የነበራቸው ቆይታ በእጅጉ ሰኬት እንደነበር የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ ፣ ነገ ሐምሌ 7 2014 ሥራ እንደሚጀምሩ ማስታወቃቸውን ባልደራስ ገልጿል፡፡"እንደ ሀገርም ፣ እንደ ድርጅትም ብዙ ስራ አለብን። የምናጠፋው ግዜ የለም"ብለዋል።

ከሳምንታት በፊት ባልደራስ ፓርቲውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ፕሬዝዳንቱ የእረፍት ጊዜያቸውን ስላጠናቀቁ በአፋጣኝ ወደ ስራ ገበታቸው ሊመለሱ ይገባል ሲል ጥሪ አስተላልፎ ነበር፡፡

https://t.me/TodayNewsEthiopia
7.7K views11:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 11:47:01
የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኮሚሽነሩ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነው ዛሬ በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት።

በፌዴራል ፖሊስ በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው ለኢቲቪ እንዳሉት፣ ኮሚሽነሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት "ኤልሻዳይ" ከተሰኘ በጎ አድራጎት ማህበር ባለቤት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በመጠርጠራቸው ነው።

ይህ ኤልሻዳይ የተሰኘ ድርጅት በአዋሽ፣ በአዳማ፣ በሀዋሳ፣ በእንጅባራ እና በሌሎችም አካባቢዎች ተፈናቃዮች በሌሉበት ተፈናቃዮች አሉ በማለት በተደጋጋሚ ጊዜ የእርዳታ እህልና አልባሳት በመረከብ ሽጦ ለተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት መግዛቱ በምርምራ መረጋገጡን ነው ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ የተናገሩት።ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ሰፊ ክትትል ሲያደርግ እንደነበረም ረዳት ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

https://t.me/TodayNewsEthiopia
7.4K viewsedited  08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ