Get Mystery Box with random crypto!

የዛሬ መረጃ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የሰርጥ አድራሻ: @todaynewsethiopia
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.26K
የሰርጥ መግለጫ

#መረጃ_አይናቅም ‼️
ትኩስ ና አዳዲስ የሀገር ውስጥ ና የአለም ዜናዎችን በፍጥነት ሰብስበን ወደናንተ እናደርሳለን Today News Ethiopia።
መረጃዎች ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ አብሮነታችሁ ያሳዩ
#ለእውነት ና #ለትክክለኛ #መረጃ ብቻ እንሰራለን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 42

2022-07-12 21:48:52 ለትግራይ ክልል የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት የሶስተኛ ወገን የትግበራ ስምምነት ተፈረመ

 
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ለሚካሄደው የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፕሮጀክቶች አገልግሎት ቢሮ ጋር የሶስተኛ ወገን የትግበራ ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና የተመድ የፕሮጀክቶች አገልግሎት ቢሮ ተወካይ ወርቅነሽ መኮንን ተፈራርመውታል።ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ በጦርነት የተጎዱ ማኅበረሰቦችን መልሶ የማቋቋም ፕሮጀክት በሚል ዕቅድ የመንግስት ብሄራዊ ማገገሚያ ፕሮግራም አካል ሲሆን ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በተመድ የፕሮጀክቶች አገልግሎት ቢሮ አማካኝነት የሚተገበር መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ይህ ፕሮጀክት በግጭት ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች የመሠረታዊ አገልግሎቶችን እና ለአየር ፀባይ ለውጥ የማይበገር የማኅበረሰብ መሠረተ ልማትን መልሶ መገንባት እና የማሻሻል ውጥን ያለው ነው።ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ በጦርነት በተጎዱ አካባቢዎች የሚገኙ እና የፆታ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች የባለብዙ ዘርፍ ምላሽ አገልግሎቶት ተደራሽነትን የማሻሻል ግብን የያዘ ነው።

በስምምነቱ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፕሮጀክቶች አገልግሎት ቢሮ በትግራይ ክልል የመልሶ መገንባት፣ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ማሻሻል እና የአየር ንብረት መቋቋም የሚችል ማኅበረሰባዊ መሠረተ ልማት የመገንባት ተግባራትን ያከናውናል ተብሏል።በተጨማሪም ማኅበራዊ ተቋማትን በመደገፍ እና ከማኅበረሰቡ ጋር በመምከር ማኅበረሰቡ ለሚፈልጋቸው አገልግሎቶች ፈጣን ምላሽ የሚያገኝበትን ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ነው የተባለው።

በግጭት ምክንያት የተጎዱ መሠረታዊ አገልግሎት የሚሰጡ መሠረተ ልማቶች መልሰው አገልግሎት እንዲሰጡ መስራትም ቢሮው ከመንግስት ጋር የገባው ስምምነት አካል መሆኑ ተገልጿል።ቢሮው በትግራይ ክልል አሁን ያለው ሁኔታ እስከሚስተካከል እና መንግሥት በክልሉ መደበኛ አገልግሎት መስጠት እስከሚጀምር ድረስ ብቻ ቆይታ ይኖረዋል ተብሏል።

https://t.me/TodayNewsEthiopia
7.8K views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 16:50:59
የሷ ነው!

አለምነህ ዋሴ

#Ethiopia | ይህ ባል ሚስቱን ይወዳል፤ ያምናልም፡፡ ወልደዋል ከብደዋል፡፡

በኬንያ ሽልንግ 3500 በእኛ 1500 ብር እየከፈሉ ለ15 ዓመታት የኖሩበት የኪራይ ቤት በደስታና በፍቅር የተሞላ ነበር፡፡

ኪራይ ጨምሩ የለ፣ ውሀ በከንቱ አታፍስሱ፣ አምፖል አታቃጥሉ ወዘተ የቤት አከራይ ጭቅጭቅ ገጥሟቸው አያውቅም፡፡

አረ እንደውም ቤት አከራዮቹ ብቅ ብለውአያውቁም!

ከአሥራ አምስት ዓመት በኋላ ባልየው መልካሟን የቤት አከራይ እንደ ድንገት አወቀ!

ሚስቱ
ናት፤ ቤቱ የሷ ነው!

ራሱን ስቶ ወደቀ።

https://t.me/TodayNewsEthiopia
8.2K viewsedited  13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 15:03:18 " ዕጣው ሙሉ ለሙሉ ተሰርዟል ብሎ መናገር አይቻልም "

- የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ተሰርዟል ብሎ መናገር አይቻልም ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ገለፀ።

የኮርፖሬሽኑ የሥራ ሀላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት " ዳታው ገብቶ ዕጣው ከወጣ በኋላ ያሉ ስህተቶች መኖራቸው ይታያል በተባለው መሰረት የተወሰኑ ክፍተቶች አሉ " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሰረት የከተማ አስተዳደሩ ምን ሊወስን እንደሚችል አልታወቀም ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ሽመልስ ጉዳዩና ውሳኔው ዛሬ ሊታወቅ ይችላል ሲሉም ጠቁመዋል።

ባለፈው ሳምንት ዓርብ 25,491 ሰው ዕጣ ወጥቶለታል ያሉት አቶ ሽመልስ ፤ ስህተት የፈጠረው ሰው እንደተለየው ሁሉ በስህተቱ እድሉ የተፈጠረለት ማነው የሚለው ተለይቶ ወደ ሚቀጥለው ደረጃ የሚያሻግረው አማራጭ ይታያል ተብሎ እንደሚታመን አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበረው የተዝረከረከ አሰራር እንዳይኖር ቀድሞ ማጣራት ተደርጓል ያለው የቤቶች ኮርፖሬሽን ዳታው ከገባ እና ዕጣው ከወጣ በኋላ ያሉ ስህተቶች መኖራቸውን ገልጿል፤ ጉዳዩ እልባት ለማግኘት ተቃርቧል ሲልም አሳውቋል።

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

https://t.me/TodayNewsEthiopia
8.1K views12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 11:20:44 "ሸኔ እና ትሕነግ መጠነ ሰፊ ጥፋት እየፈፀሙብን ነው"

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ

አሸባሪዎቹ ሸኔ እና ትሕነግ በአማራ ሕዝብ ላይ መጠነ ሰፊ ጥፋት እየፈጸሙ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ይህንን ያሉት ከሰሜን ሸዋ ዞን የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር ዛሬ በደብረ ብርሃን ከተማ እየተወያዩ ባሉበት ወቅት ነው።

በውይይቱ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ በርካታ ጥቃቶች እየተፈፀመበት ነው ያሉ ሲሆን ጥቃቱን ማክሸፍ የሚቻለው በመደማመጥና በመተባበር ብቻ ነው ብለዋል።

የክልሉ መንግሥት ከውስጥም ከውጭም እየደረሱ ያሉ ጫናዎችን ለመቋቋም በሰከነ መንገድ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ያወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ "ሸኔ እና ትሕነግ መጠነ ሰፊ ጥፋት እየፈፀሙብን ነው" ብለዋል፡፡

ይህን መጠነ ሰፊ ጥቃትና ጥፋት የሚያቀናብሩትንና በክልሉ ውስጥም ከክልሉ ውጭም ባሉ አካባቢዎች እያደረሱት ያለውን የጥፋት አጀንዳ ለማክሸፍ ጠንካራ መንግሥታዊ መዋቅር መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ የክልሉ መንግሥት ይህንን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እየሠራን ነው ብለዋል።

በክልሉ ውስጥ ለአብነት ከሰሞኑ በአጣዬና አካባቢው የደረሰው ጥቃት በተደጋጋሚ ረፍት ለመንሳት የሽብር ቡድኖች የጠነሰሱልን ሴራ አካል ነው ተብለዋል።
አሚኮ

https://t.me/TodayNewsEthiopia
8.3K views08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 23:30:28 የመዲናዋ አስተዳደሩ ሰሞኑን በወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የዳታ ማጭበርበር መከሰቱን አስታወቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ሐምሌ 01 ቀን 2014 በወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ  የዳታ ማጭበርበር ድረጊት በመከሰቱ ሁኔታውን እያጣራ እንደሚገኝ እና በድርጊቱ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር  እያዋለ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ሲጀመር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነት ተገኝቶበታል፡፡ በጉዳዩ የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር በቁጥጥር ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገ ይገኛል ብሏል፡፡ በእስካሁኑ የማጠራት ስራም ላልቆጠቡ ሰዎች እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል ነው ያለው፡፡

ከዚህ በመነሳትም “የቤት ማስተላለፉን ሂደት ግልፅነት ለማስፈን ሲባል እና ውጤቱን የሚያዛባ ተግባር ሲያጋጥም መልሰን ኦዲት እንዲደረግ በገባነው ቃል መሰረት የተፈጠረውን ችግር ከጉዳዩ ገለልተኛ በሆኑ በሚመለከታቸው ተቋማት የማጣራት ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል” ብሏል፡፡

https://t.me/TodayNewsEthiopia
8.4K views20:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 22:21:17 ሰዎችን በመልካም ስልጠናዎች አመለካከታቸው ላይ እና አምሮቸው ላይ እንዲሰሩ በማድረግ ህይወታቸውን እየቀየረ ያለ አንድ ድንቅ ቻናል ልጠቁማችሁ ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ።

https://t.me/Happy_life44
8.2K views19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 20:26:45 የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ነገ ፍርድ ቤት እንደቀርቡ ቀጠሮ ተይዟል

ባሳለፍነው ሳምንት በነበረ የችሎት ቀጠሮ አቶ ሀይለማርያም በማንኛውም ሰዓት ወደ ኢትዮጲያ ሲመጡ ተወካያቸው ወይም የሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ጠበቃ ከ48 ሰዓት በፊት ለፍርድ ቤቱ እንዲያሳውቁ እና ምስክርነታቸው እንዲሰማ መታዘዙ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ተወካያቸው ዛሬ ቀርቦ ወደ ኢትዮጳያ መምጣታቸውን ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሪፖርት አድርጓል።

ፍርድ ቤቱም በነገው ቀጠሮ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በአካል ቀርበው ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በተከሰሱበት በመርከብ ግዢና በእርሻ መሳሪያ ግዢ ጉዳይ ላይ በተቆጠሩበት የመከላከያ ምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ቀጠሮ ይዟል።

በዚህ ቀጠሮ መሰረት አቶ ሀይለማርያም ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይታሰባል።

https://t.me/TodayNewsEthiopia
8.9K views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 14:10:20 በትግራይ ክልል ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ተሰማ


በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች በጦርነቱ ምክንያት በተከሰተው ርሃብ ከመሰቃየት ሞትን በመምረጥ ቀድመው ራሳቸውን እያጠፉ መሆኑን በሥፍራው ተዘዋውረው የተመለሱ ታማኝ ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ገለፁ።

ኹለት ዓመት ሊሞላው ወራት በቀሩት ጦርነት ሳቢያ ርሃብ መከሰቱን ተከትሎ በርካታ ሰዎች ራሳቸውን ለማጥፋት እንደተገደዱ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድርግ መቀሌ ከተማ ደርሰው የመጡ ሰዎች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

መረጃ ሰጪዎቹ እንደሚሉት ከሆነ፤ በክልሉ የሰብዓዊ ድጋፍ አነስተኛ በመሆኑ ነዋሪዎቹ በርሃብ እየተሰቃዩ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎም ግለሰቦች ራሳቸውን እያጠፉ ነው ተብሏል። ነዋሪዎቹ ራሳቸውን እያጠፉ ነው የተባለው ጎዳና ወጥተው ቢለምኑም ማግኘት እንደማይችሉ በመረዳታቸውና ከመለመን ሞትን በመምረጣቸው ነውም ተብሏል።

ምንጭ አዲስ ማለዳ

https://t.me/TodayNewsEthiopia
9.7K views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 11:56:15
"በስህተት ወደ አካውንቴ የገባልኝን 2.4 ሚሊዮን ብር ተመላሽ አድርጌያለሁ።"
ከቤሩት ሃገር ከስር በምስሉ ላይ እንደሚታየው፤ አንዴ 1.3 ሚሊዮን ብር፤ አንዴ ደግሞ 1.1 ሚሊዮን ብር በስህተት ወደ ጥላሁን አለሙ አካውንት ገቢ ይደረጋል።
ይሄኔ ጥላሁን የገባለት 2.4 ሚሊዮን ብር ሳያጓጓው ለባለቤቱ ተመላሽ አድርጓል።

ነዋሪነቱን በኤሌልቱ ከተማ ያደረገው ጥላሁን አለሙ
"ማንም ወደ እኔ የደወለ የለም፤ ራሴ ሄጄ ነው ብሩ በስህተት ወደ አካውንቴ እንደገባ ያመለከትኩት ፤ ለባለቤቱም በአካውንቱ ተመላሽ አድርጌያለሁ በዚህም ይህንን በማድረጌ ከፀፀት ድኛለሁ" ሲል ገልጿል።

እንደ ወጣት ጥላሁን አለሙ ያሉ ሠዎችን ያብዛልን!!

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ጌትነት ተመስገን

https://t.me/TodayNewsEthiopia
11.0K views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 13:18:59 ኤሎን መስክ ከ44 ቢሊዮን ዶላር የትዊተር ግዢ ስምምነት እራሱን አገለለ

የዓለማችን ቁጥር አንድ ቢሊየነር ኤሎን መስክ በርካታ የግዢ ስምምነቶች አለተከበሩም በማለት በ44 ቢሊዮን ዶላር ትዊተርን ለመግዛት ደርሶት ከነበረው ስምምነት እራሱን እያገለለ መሆኑ ተገለጸ።

ከሁለት ወራት በፊት የትዊተር ቦርድ የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መድረኩን በ44 ቢሊዮን ዶላር ለኤሎን መስክ ለመሸጥ ተስማምቶ ነበር።

መስክ ከትዊተር ግዢ ራሱን ያገለለው የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያው ሐሰተኛ የሆኑ የትዊተር አካውንቶች ምን ያህል እንደሆኑ በቂ መረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ ነው ብሏል።

ትዊተር በበኩሉ የግዢ ስምምነቱ ተፈጻሚ እንዲሆን ሕጋዊ እርምጃዎችን ለመውሰድ አማራጮችን እያጤንኩ ነው ብሏል።

“የትዊተር ቦርድ ከመስክ ጋር በተደረሰው ዋጋ እና ደንቦች መሠረት ስምምነቱ ተፈጻሚ እንዲሆን ጽኑ ፍላጎት አለው” ሲሉ የትዊተር ቦርድ ሰብሳቢ ብሬት ቴይለር በትዊተር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

በፎርብስ መጽሔት መረጃ መሠረት 273.6 ቢሊዮን የሚገመት የተጣራ ሃብት ያለው ኤሎን መስክ የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ ነው።

ይህም በዋነኝነት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራች በሆነው ቴስላ ውስጥ ባለው ድርሻ እና ስፔስ ኤክስ የተባለውን የህዋ በረራ ፕሮግራም ተቋም በኩል በሚያገኘው ገቢ ነው።

መስክ ትዊተርን ለመግዛት ከስምምነት መድረሱ በተገለጸበት ወቅት፤ የማኅበራዊ ትስስር መድረኩን ደንብ እና የአጠቃቀም መመሪያዎችን በማላለት ሰዎች በተሻለ ነጻነት እና አነስተኛ ገደብ ሃሳባቸውን መግለጽ እንዲችሉ ይፈቀዳሉ ግምቶች በስፋት ተነስተው ነበር።

“ነፃ ንግግር የዲሞክራሲ መሠረት ነው፤ ትዊተር ደግሞ ለሰው ልጅ የወደፊት ሕይወት ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ክርክር የሚደረግበት የዲጂታል አደባባይ ነው” ሲል ኤሎን መስክ ስምምነቱን ይፋ ባደረገበት መግለጫ ገልጾ ነበር።

ትዊትር የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ከማኅበራዊ መድረኩ ማገዱን መስክ አጥብቆ ተቃውሞ ነበር።

ሐሰተኛ አካውንቶች

መስክ ግንቦት ወር ላይ ‘ስፓም’ እና ሐሰተኛ የሆኑ አካውንቶችን በተመለከተ መረጃ እስኪገኝ ድረስ የግዢው ስምምነት “ባለበት እንዲቆም” ተደርጓል ብሎ ነበር።

ትዊተር ከአጠቃላይ ተጠቃሚዎቹ የሐተሰኛ አካውንቶች ቁጥር ከ5 በመቶ ያልዘለለ ነው ቢልም፣ መስክ ግን ማረጋገጫ እንዲሰጠው ሲጠይቅ ቆይቷል። መስክ ይህ ቁጥር ከ20 በመቶ ያለነሰ ነው ብሎ ያምናል።

የኤሎን መስክ ጠበቆች ትዊተር ይህን ማረጋገጫ ማቅረብ አልቻለም ይላሉ።

ስፓም አካውንቶች አንድ ተመሳሳይ የሆነ መረጃ ያለ ተቀባዩ ፍቃድ እና እውቅና ለበርካታ ሰዎች የሚልኩ አካውንቶች ሲሆኑ፣ ሐሰተኛ አካውንቶች ደግሞ ትክክለኛ ባለሆነ ማንነት የሚከፈቱ አካውንቶች ናቸው።

ሐሙስ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም. ትዊትር በየቀኑ መሰል 1 ሚሊዮን አካውንቶች አስወግዳለሁ ሲል መግለጫ አውጥቶ ነበር።

Via:- BBC

https://t.me/TodayNewsEthiopia
11.4K viewsedited  10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ