Get Mystery Box with random crypto!

የዛሬ መረጃ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የሰርጥ አድራሻ: @todaynewsethiopia
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.26K
የሰርጥ መግለጫ

#መረጃ_አይናቅም ‼️
ትኩስ ና አዳዲስ የሀገር ውስጥ ና የአለም ዜናዎችን በፍጥነት ሰብስበን ወደናንተ እናደርሳለን Today News Ethiopia።
መረጃዎች ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ አብሮነታችሁ ያሳዩ
#ለእውነት ና #ለትክክለኛ #መረጃ ብቻ እንሰራለን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-05-20 16:09:21
15 የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው አለፈ

15 የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ዛሬ ማለዳ ለማስተማር ወደ ሻሸመኔ ካምፓስ በመጓዝ ላይ እያሉ በደረሰባቸው የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው አልፏል።

ተሸከርካሪው መንገድ በመሳት በተፈጠረው አደጋ እስካሁን 15 የዩኒቨርሲቲው መምህራን ሕይወት ማለፉን የሮቤ ከተማ ከንቲባ አቶ ንጋቱ ሞቱማ ገልጸዋል ሲል ኦቢኤን ዘግቧል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
2.6K viewsedited  13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 23:27:21 Stop wishing, start working.

ምኞትን አቁም - መስራት ጀምር

በዚህ ሀሳብ ብቻ የሚስማማ ቤተሰብ ብቻ ይህን የቴሌግራም ገፅ ይቀላቀል በፍጥነት ሳይሆን በርግጠኝነት ግባችን ላይ እንደርሳለን።

ለኔ ምርጫ አይደለም ሀብታም መሆን

Join Telegram Page

https://t.me/+RFm03EsorweXe1Pg
3.7K viewsedited  20:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 21:33:04 ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ተፃፈ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ደብዳቤ ፃፈ።

" በቅርቡ በአዲስ መልኩ ' ሸገር ከተማ ተብሎ ' በተመሠረተው ከተማ ህገወጥ በሚል በርካታ መስጂዶች በከተማ አስተዳደሩ አማካኝነት እየፈረሱብን ይገኛል " ያለው ምክር ቤቱ  " በመስጅዶች ፈረሳ ጉዳይ ላይ ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጋር በስልክ በመነጋገር መፍትሄ ላይ እንደደረስን ብናምንም የከተማ አስተዳደሩ ግን በረመዳን ወር ለጊዜው የመስጂዶች ፈረሳውን እንዲቆም በማድረግ ከረመዳን በኋላ የመስጂዶች ፈረሳ በአዲስ መልክ በብዛት ቀጥሏል " ሲል ለጠ/ሚኒስትሩ በፃፈው ደብዳቤ አመልክቷል።

በመሆኑም የመስጂዶች ፈረሳ ጉዳይ በከተማ አስተዳደሩ " ህገ-ወጥ " ስለተባለ ብቻ በቀላሉ የሚታይ ሳይሆን የህዝበ ሙስሊሙ የኃይማኖት ዋነኛ ህልውና በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም ለኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ደብዳቤ ብንፅፍም እስካሁን ምላሽ አላገኘም ብሏል።

" በስልክም በጉዳዩ ላይ ለመነጋጋር ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም " ሲል አክሏል።

" ተጨማሪ መስጅዶች የማፍረስ ተግበሩ ለክልሉ ፕሬዜዳንት ደብዳቤ ከፃፍንና በጉዳዩ ላይ በአካል በመገናኘት ለመነጋገር ቀጠሮ እየጠየቅን ባለንበት ወቅት መስጅዶች እየፈረሱ መሆኑ የጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮችን እንዲሁም ሕዝበ ሙስሊሙም በእጅጉ አሳዝኗል " ብሏል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ በደብዳቤው ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እንደ ጠቅላይ ሚኒስተርና እንደ የብልጽግና ፓርቲ መሪ ለመስጂዶች ፈረሳ ጉዳይ አስቸኳይ መፍትሄ የመስጠት ሙሉ ስልጣኑ እንዳላቸው በማመን ለችግሩ የማያዳግም መፍትሄ እንዲሰጡ ጠይቋል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
5.6K views18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 11:37:02
#ዘይገርም

ኤለን መስክ በ2023 ሴብቴምበር ወር የሮቦት ሚስት መሸጥ እንደሚጀምር አስታውቋል

ቱጃሩ ሰው ራሱም ከሮቦት ጋር እንደሚሞሸር ታውቋል። ኤለን መስክ የሮቦት ሚስቱን ካታኔላ ሲል ጠርቷታል።

የሮቦት ሚስቶች ጋር ወሲብ ለመፈፀም ፓስዋርድ፤ ፓተርን ወይም በኣሻራ መክፈት ግድ ይላል። ይህም ሮቦቷ እንዳትደፈር ወይም ቺት እንዳታረግብህ ይጠቅማል ተብሏል።

አንድ የሮቦት ሚስት ቻርጅ ለመደረግ 3 ቀን ይፈጅባታል። አፍሪካ ላይ በ2023 ኖቬምበር ወር ሽያጩ ይጀመራል።

የሰው ልጅ ኣደጋ ውስጥ ነው። አሊታ ሚለው አኒሜሽን ፊልም የእውነት ሆኗል።

Via - Erimias belayineh

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችችን ይቀላቀሉ።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
6.0K viewsedited  08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 17:15:13
በአዲስ አበባ ቦሌ የሚገነባው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቤተ መንግስት ዲዛይን።

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

http://t.me/TodayNewsEthiopia
6.3K views14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 21:55:21
ሰርጉ ወደ ሀዘን ተቀየረ

በሰርግ ላይ በተተኮሰ ጥይት ሙሽራው እና አባትየው ህይወታቸው አለፈ!!

በምዕራብ ጎጃም አስተዳደር ዞን በቋሪት ወረዳ ወይበኝ ቀበሌ ልዩ ቦታው በተለምዶ አነሳት እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ በባህሉ በወጉ መሰረት ልጃችንን ለልጃችሁ ተባብለው ሙሽሪትና ሙሽራው ሊጣመሩ የሙሽራው ቤተሰብና የሙሽሪት ቤተሰብ በስጋ ዝምድና ሊጣመሩ ቤት ባፈራው እንደአቅም ድግስ በመደገስ የሩቁና የቅርቡ ወዳጅ ዘመድ ልጃችንን ስለምንድር ልጃችንን መርቁልን ማለት የተለመደ ስርዓትና ወግ ነው፡፡

ታዲያ በዕለተ እሁድ ከሩቁ ከቅርብ የተጠራው ቤተዘመዱ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሙሽራው መምጫ ሰዓት ደረሰ ሙሽራው ከነሚዜወቹ ደረሱ የሙሽሪት ቤተሰቦች በጣም ደስ አላቸው እልልታውን አቀለጡት ሙሽራው ሙሽሪትን በቤተሰብ አስመርቆ ወደቤቱ ሊመለስ ሲል ሞቅ ያለ ጭፈራ ሆታ ተነሳ በጭፈራው መሃል ቅልጥ ያለ የጥይት ተኩስም ተተኮሰ በድንገት ጭፈራ ሲጨፈር የነበረው ሰው ፀጥ አለ በጭፈራው መሃል በተተኮስ ጥይት ሙሽራው እና የሙሽራው አባት ወዲያውኑ ህይታቸው ያልፋል፣ አንድ የሴት ሚዜ አና ሰርጉን ለማድመቅ የተገኙ 4 ሰወች በድምሩ አምስት ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን በተደረገላቸው ህክምና ህይወታቸው መትረፉን የወረዳው የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ረ/ኢ/ር ተመስገን ሙሉነህ ተናግረዋለወ።

የወንጀል ድርጊት የተሳተፉትን በቁጥጥር ስር አድርገው ምርመራ እያጣሩ መሆኑን ገልፀዋል።

መረጃው የምዕ/ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ነው።
http://t.me/TodayNewsEthiopia
7.9K viewsedited  18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 19:05:42
#እንድረስላት

ይህች የ15ዓመት ህፃን #ኢክራም_አብራር ትባላለች!የሚጥል ህመም አለባት!ትላንት ግንቦት5 ጠዋት ቁርስ በልታ መድሀኒቷን ሳትወስድ ድንገት መሿለኪያ ከሚገኘው ቤታቸው እንደወጣች እስካሁን የት እንዳለች ምን እንደገጠማት አልታወቀም! እናትና አባት ተጨንቀዋል!እባካችሁን #ሼር በማድረግ አፋልጉን
                        "ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
                                  #ባይሽ_ኮልፌ_በጎ_አድራጎት
0911690582-አብራር(አባት)
0920038529-ሙባረክ(ወንድም)
6.6K views16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 13:58:37 የ22 ዓመቱ ማሌዥያዊ የ48 ዓመቷን የቀድሞ መምህሩን አግብቷል

የቋንቋ መምህሩ ለተማሪዎች የምታሳየው ፍቅር የማረከው ወጣት “እድሜ ቁጥር ብቻ ነው” ብሎ ከብዙ ድካም በኋላ ምኞቱን ማሳካቱን ገልጿል። የ26 ዓመት የእድሜ ልዩነት ያልገደባቸው ተማሪና የቀድሞ መምህሩ በቅርቡ ተሞሽረዋል።

ሙሃመድ ዳኔል አህመድ አሊ በፈረንጆቹ 2016 የማሌዥያ ቋንቋ አስተማሪውን ጀሚላህ ሞህድ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመለከት የ15 አመት ታዳጊ ነበር።
በወቅቱ ምንም የተለየ የፍቅር ስሜት እንዳልተሰማው የሚያነሳው ሙሀመድ ዳኔል፥ ታዳጊም ቢሆን ጀሚላ ለተማሪዎች የምታሳየው ፍቅርና እንክብካቤ እየረሳኝም ይላል።

ከክፍል ክፍል ሲዛወር የቋንቋ አስተማሪውን ያጣው ሙሃመድ፥ በ2017 በአጋጣሚ ወደ መምህራን ቢሮ ሲያመራ ጀሚላን ያገኛትና ሰላምታ ሰጥቶ ያልፋል።

ከዚህ በኋላ ስለጀሚላ ማሰብ ማንሰላሰል ጀመርኩ የሚለው ሙሀመድ፥ የልደት መልካም ምኞት ከጀሚላ ሲደርሰው ነገሮች ሁሉ በፍጥነት መልካቸውን መቀየራቸውን ያስታውሳል።

በአጭር የጽሁፍ መልዕክቱ የተጀመረው ንግግርም እያደገ ሄዶ የታዳጊነት ስሜቱን ሳይደብቅ በ26 አመት ለምትበልጠው የቀድሞ መምህሩ የፍቅር ጥያቄ ማቅረቡን ለማሌዥያው ኒው ስትሬት ታይምስ ይናገራል።
ጀሚላም የእድሜ ልዩነታቸውን በመጥቀስ በፍጹም የማይሆን ነገር ነው የሚል ምላሽ ትሰጣለች።

“አድራሻዋን አላውቅም ነበር፤ እድል ቤቷ ድረስ ወሰደኝ” የሚለው ሙሀመድ፥ ቤት ውስጥ ሁሉንም ነገር በግልጽነት እንዳወሩም ነው የሚገልጸው።
ያም ሆኖ ጀሚላ በአቋሟ መጽናቷን ተከትሎ ወጣቱ ሙሀመድ ለረጅም ጊዜ መወትወቱንና ለማሳመን መጣሩን ይገፋበታል።

መምህርት ጀሚላ የቀድሞ ተማሪዋ ወይ ፍንክች የአባ ቢለዋ ልጅ ማለቱን ስትመለከት ከሁሉ ነገር ቀድሞ የሚመጣው የእድሜ ልዩነታቸው ጉዳይ እየደበዘዘ ይሄዳል።

“ወደኔ ሲመጣ በሙሉ መተማመን ነው፤ ለቤተሰቦቹም ሲያሳውቅ አላፈረም፤ ይህ ይበልጥ እንድተማመንበት አድርጎኛል” የምትለው ጀሚላ፥ ለጉዳዩ የሰጠው ትኩረት አቋሟን እንድለውጥ እንዳደረጋትም ትናገራለች።
እናም ለቤተሰቦቻቸው አሳውቀው ጋብቻቸውን ለመፈጸም መስማማታቸውን ታስታውሳለች።

በ2021 በጋብቻ ለመጣመር የያዙት እቅድም በኮሮና ምክንያት ተራዝሞ ከሰሞኑ ቤተሰቦቻቸው እና ጓደኞቻቸው በተገኙበት በመጠነኛ ሰርግ ተሞሽረው የማሌዥያ መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስበው ሰንብተዋል።
“እድሜ ቁጥር ብቻ ነው፤ እንደ ባል የሚጣልብኝን ሃላፊነት ለመወጣት ተዘጋጅቻለሁ” ብሏል የ22 አመቱ ወጣት።

በፈረንጆቹ 2007 የመጀመሪያ ባሏን የፈታችው ጀሚላም ስራዋ ላይ ትኩረት አድርጋ ለወንዶች ሁሉ ዘግታው የነበረውን ልቧን ለባለቤቷ ሙሀመድ ዳኔል ክፍት ማድረጓን መናገሯ ተዘግቧል።

ዘገባው የዐል ዐይን ነው።

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
http://t.me/TodayNewsEthiopia
7.6K viewsedited  10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 13:58:05
6.3K views10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 22:07:11
ለበሬ መግዛ የተቀመጠ ከ263ሺ ብር በላይ በሻማ ምክንያት ከጥቅም ውጪ ሆነ


ክስተቱ ግንቦት 2 2015 ዓ/ም ነው ያጋጠመው፣ አቶ ግዛቸው ወርቅነህ እና ጓደኛቸው አዲሱ ሳላስብ የተባሉት የቻግኒ እና የጨረቃ ነዋሪዎች በሬ ለመግዛት በሚል ወደ ግልገል በለስ ከተማ ይሄዳሉ፣ ግልገለ በለስ ደርሰው በዋጋ ባለመግባባት የበሬ ግዢው ሳይፈፀም በመቅረቱ ግሪን ላንድ ከሚባለው ሆቴል በመሄድ አልጋ ይዘው ከቆዩ በሁዋላ ማታ ላይ መብራት ባለመኖሩ ምክንያት የተለኮሰውን ሻማ ሳያጠፉ ሻይ ቡና እንበል በሚል ከምሽቱ 4:00 ሰዓት አካባቢ ወጣ እንዳሉ ለፋስት መረጃ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ሻማው የተቀመጠበትን እቃ በእሳት መያዝ ይጀምራል በእሱ ብቻ አላበቃም ከስር ያለውን የአቶ ግዛቸውን ሻንጣ የእሳቱ ሰለባ ይሆናል። የቃጠሎ ሽታ መኖሩን እና ጭሱን ያየው የሆቴሉ ባለቤት እና በቦታው የነበሩ ሰዎች በሩን ገንጥለው በመግባት እሳቱን ለማጥፋት የቻሉ ሲሆን ሁለቱ ጓደኛሞች የሰውን መሯሯጥ አይተው ወደ አልጋቸው ሮጠው ቢደርሱም የአቶ ግዛቸው ሻንጣ በውስጡ ከያዘው የበሬ መግዣ ብር 280,000 ጋር በእሳቱ የተቃጠለ ሲሆን ከተቃጠለው ብር ውስጥ በተደረገው የመለየት ስራ አገልግሎት ላይ ሊውል የሚችል 16,200 ብር የተለየ ሲሆን ቀሪው 253,800 ያህሉ በእሳቱ ተቃጥሎ ከጥቅም ውጩ መሆኑን ከግ/በለስ ፖሊስ ፋስት መረጃ ሰምቷል።

የጓደኛው የአዲሱ ሳላስብ ሻንጣ ከሻማው ራቅ ብሎ የነበረ በመሆኑ በውስጡ ከነያዘው 220,000 ብር ጋር ምንም ጉዳት ሳይደርሰበት ሊተርፍ ችሏል::

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
http://t.me/TodayNewsEthiopia
7.2K views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ