Get Mystery Box with random crypto!

የዛሬ መረጃ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የሰርጥ አድራሻ: @todaynewsethiopia
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.26K
የሰርጥ መግለጫ

#መረጃ_አይናቅም ‼️
ትኩስ ና አዳዲስ የሀገር ውስጥ ና የአለም ዜናዎችን በፍጥነት ሰብስበን ወደናንተ እናደርሳለን Today News Ethiopia።
መረጃዎች ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ አብሮነታችሁ ያሳዩ
#ለእውነት ና #ለትክክለኛ #መረጃ ብቻ እንሰራለን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-03 08:49:08
Always trust his plan

Join us @tesfamichaelAsefa
3.7K views05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 22:51:00 የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ ለተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ምስጋና አቀረበ

የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ÷ ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል በክልሉ ዛሬ የተካሄደውን የድጋፍ ሰልፍ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም÷በኦሮሚያ ክልል ሀሉም አካባቢዎች በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ለለውጡ ያላቸውን ድጋፍ መግለጻቸውን አንስተዋል፡፡

የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ለነጻነት፣ ለእኩልነትና ለፍትህ ለተካሄደው ትግል እንዲሁም ከለውጡ በኋላ ለተመዘገቡት ድሎች እና ስኬቶች እውቅና ሰጥተዋል ነው ያሉት፡፡

የሰልፉ ተሳታፊዎች በሰላማዊ መንገድ የመጣውን ለውጥ በሴራና በሃይል ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኞች ሃይሎችን እንደሚታገሉ ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋልም ብለዋል፡፡

http://t.me/TodayNewsEthiopia
4.5K views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 11:45:14
ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እና ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ ከእስር ተፈቱ

በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እና በሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ መዝገብ ተከስሰው በእስር ላይ የነበሩ የህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ትናንት ሐሙስ መጋቢት 21፤ 2015 አመሻሽ ላይ ከእስር መፈታታቸውን የተከሳሾቹ ጠበቆች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሃፍቶም ከሰተ ተናግረዋል።

በትናንቱ ዕለት ከእስር ተለቅቀው ወደ ቤታቸው መግባታቸው ከተረጋገጡ ተከሳሾች ውስጥ፤ የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እና ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ እንደሚገኙበት ጠበቃው አስታውቀዋል።

ተከሳሾቹ ትናንት አመሻሽ ላይ በእስር ላይ ከቆዩበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ወደ ሲ.ኤም.ሲ የመኖሪያ ግቢ፣ ፒያሳ እና ሳሪስ አካባቢዎች በማረሚያ ቤቱ አውቶብስ ከተወሰዱ በኋላ መፈታታቸውን ጠበቃው አስረድተዋል። እስረኞቹ ወደ እነዚህ ቦታዎች እንደተወሰዱ አስቀድሞ የተነገራቸው ቤተሰቦች፤ በስፍራው ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል ተብሏል።

ትናንት ከእስር የተፈቱት በዶ/ር ደብረጽዮን መዝገብ የተካተቱ 16 ተከሳሾች እና በሌተናል ጄነራል ታደሰ መዝገብ ስር ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ 20 ወታደራዊ መኮንኖች መሆናቸውን ጠበቃ ሃፍቶም ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። እነዚህ ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ከእስር የተለቀቁት፤ በዐቃቤ ሕግ ቀርቦባቸው የነበረው የወንጀል እና የሽብር ድርጊት ክስ መቋረጡን ፍትሕ ሚኒስቴር ባስታወቀ ሁለት ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
2.2K viewsedited  08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 15:17:09
የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ነርስ ከፎቅ ላይ ዘላ ጉዳት ደረሰባት

መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ሌሊት 10:30 ሲሆን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዉስጥ አዋላጅ ነርስ የሆነች ዕድሜዋ 40 የተገመተ አንዲት የሆስፒታሉ ሰራተኛ ከ6ኛ ፎቅ ላይ ዘላ ወደ ምድር በመዉደቋ ከባድ ጉዳት ደርሶባታል።

ከ6ኛ ፎቅ ወደ ታችኛዉ ወለል ወደ ቤዝመንት ዉስጥ የወደቀችዉን ተጎጂ ከወደቀችበት ለማንሳት ምቹ ሁኔታ ባለመኖሩ ለኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጥሪ ተደርጓል።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም በመሰላልና በገመድ በመጠቀም ተጎጂዋን በህይወት አዉጥተዋታል። ተጎጂዋ ከአደጋዉ በህይወት ብትተርፍም ከባድ ጉዳት ደርሷባታል።

ተጎጂዋ በሆስፒታሉ ተረኛ አዋላጅ ነርስ ሆና ምሽቱን የተለመደ ስራዋን ከባልደረቦቿ ጋር ስታከናዉን ነበር

መረጃው የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
4.3K views12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 17:16:20
በትግራይ ክልል የኩፍኝ መከላከያ ክትባት እየተሰጠ ነው

በትግራይ ክልል የተቀናጀ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት እየተሰጠ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡በሚኒስቴሩ የእናቶችና ህጻናት ክትባት ዴስክ ሃላፊ መልካሙ አያሌው እንደገለጹት፥ ለትግራይ ክልል ለኩፍኝ ክትባት ዘመቻ የተመደበው በቂ ክትባት ወደ ክልሉ ተልኳል፡፡

ክትባቱ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ካለፈው መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፥ የክትባት አገልግሎቱ በዓለም ጤና ድርጅት እና ዩኒሴፍ አስተባባሪነት እየተካሄደ መሆኑንም ነው ሃላፊው የተናገሩት፡፡የመከላከያ ክትባቱ እስከ አምስት ዓመት እድሜ ለሆናቸው ህጻናት የሚሰጥ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ለ12 ቀናት በሚካሄደው የክትባት ዘመቻ ከ831 ሺህ በላይ ህጻናትን ለመድረስ መታቀዱም ነው የተገለጸው፡፡በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ከታህሳስ 13 እስከ ታህሳስ 22 ቀን 2015 ዓ.ም መካሄዱ ይታወሳል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።
2.6K views14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 12:54:45
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስልጣን በጋራ ብንለቅ የተሻለ ነው ሲሉ ከምክር ቤቱ አባል ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጡ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ላቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል አንደኛው እና ቀዳሚው በኢትዮጲያ በተደጋጋሚ እየታየ የሚገኘውን የሰላም እጦት እና ሀገርን አደጋ ውስጥ ያስገባው በመንግስት ክፍተት ነውና እርስዎ ስልጣን በመልቀቅ የመፍትሔ አካል ለመሆን አላሰቡም ወይ የሚል ጥያቄ የአብን ተወካዩ የምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ አንስተዋል፡፡

ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ‹‹ ጥያቄው ስልጣን ቢለቁ ከሚለው ይልቅ ብንለቅ የሚለው የተሻለ ነው ›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህግ አውጪ ሆነ አስፈፃሚ እንዲሁም ደግሞ ህግ ተርጓሚ መንግስት እንደመሆኑ መጠን ለሚደርሰው ሁሉም ነገር ኃላፊነትን በጋራ በመውሰድ ስልጣን ብንለቅ የሚለው ሃሳብ የተሻለ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሁሉም ችግር እና ምንጭ እኔ ብቻ ልሆን አልችልምና ሁሉንም ነገር መጋራት የሚገባን በጋራ ነው ሲሉ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ መስጠታቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል ፡፡
3.7K views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 14:59:16
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ በትላንትናው ዕለት የተደረገውን ጥሪ በመቀበል የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የተደረሰውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመቀበል በዛሬው ዕለት ወደ እናት ቤተክርስቲያን መመለሳቸውን የሚገልዕ ደብዳቤ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በማቅረብ በይፋ መመለሳቸውን አሳወቀች

ቤተክርስቲያኗ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ፦

- ወደ ሥራ እንደምትመልሳቸው
- ደመወዛቸውን እንደምትከፍል
-  የታሸገውን ቤታቸውን በመክፈት እንደምታስረክባቸው ገልጻለች።
2.6K views11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 15:16:23
ድሬዳዋ :
የተረሳ 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ

#Ethiopia | በድሬዳዋ ከተማ ከሚያሽከረከረው ባጃጅ ላይ የተረሳ 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል።

መኮንን ግርማ ኑሮን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ ባጃጅ ላይ ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው።

ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም እንደተለመደው ለስራ በድሬዳዋ ጎዳና ላይ ከምሽቱ ሶስት ሰአት ላይ ባጃጁን እያሽከረከረ ሳለ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ መሀመድ ዑስማን ከሳቢያን ወደ ኦርቢት ለመሄድ በሱ ባጃጅ ተሳፍረው ወደተባለው ቦታ ማድረሱን ተናግራል።

ይህ ከሆነ ከአንድ ሰአት በኋላ ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እና እንድመለከት ተነገረኝ የሚለው ወጣቱ፤ ከተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሬ ስመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ በርካታ ብር ተቀምጦ ማግኘቱን እና ወዲያው ገንዘቡን ይዞ ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳሬክቶሬት በመምጣት 150ሺህ ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ተናግሯል።

ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፣ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ዑስማን በበኩላቸው፤ ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የምሽት ባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልፀው፣ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
2.8K views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 17:51:41
የጉራጌ ሕዝብ ችግሮችን ገንቢ በሆነ ተሳትፎና ውይይት የሚፈታ ሰላም ወዳድ ሕዝብ ነው

ጠ/ ሚ ዐቢይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  ከጉራጌ ዞን ከተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የጉራጌ ሕዝብ የሚነሡ ችግሮችን ገንቢ በሆነ ተሳትፎና ውይይት የሚፈታ ሰላም ወዳድ ሕዝብ ነው ብለዋል።

“ዛሬ ባደረግናቸው ውይይቶች ያነሧቸውን ሥጋቶች እና ተስፋዎች በመስማቴ ደስተኛ ነኝ” ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

በየደረጃው ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት እንሠራለንም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡
4.3K views14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 15:02:57
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከዞኑ ኅብረተሰብ ጋር ለመወያየት ጉራጌ ዞን ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ከዞኑ ኅብረተሰብ ጋር ለመወያየት ዛሬ ጠዋት ጉራጌ ዞን መግባታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
4.5K views12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ