Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል የኩፍኝ መከላከያ ክትባት እየተሰጠ ነው በትግራይ ክልል የተቀናጀ የኩፍኝ መከላከ | የዛሬ መረጃ ®

በትግራይ ክልል የኩፍኝ መከላከያ ክትባት እየተሰጠ ነው

በትግራይ ክልል የተቀናጀ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት እየተሰጠ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡በሚኒስቴሩ የእናቶችና ህጻናት ክትባት ዴስክ ሃላፊ መልካሙ አያሌው እንደገለጹት፥ ለትግራይ ክልል ለኩፍኝ ክትባት ዘመቻ የተመደበው በቂ ክትባት ወደ ክልሉ ተልኳል፡፡

ክትባቱ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ካለፈው መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፥ የክትባት አገልግሎቱ በዓለም ጤና ድርጅት እና ዩኒሴፍ አስተባባሪነት እየተካሄደ መሆኑንም ነው ሃላፊው የተናገሩት፡፡የመከላከያ ክትባቱ እስከ አምስት ዓመት እድሜ ለሆናቸው ህጻናት የሚሰጥ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ለ12 ቀናት በሚካሄደው የክትባት ዘመቻ ከ831 ሺህ በላይ ህጻናትን ለመድረስ መታቀዱም ነው የተገለጸው፡፡በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ከታህሳስ 13 እስከ ታህሳስ 22 ቀን 2015 ዓ.ም መካሄዱ ይታወሳል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።