Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስልጣን በጋራ ብንለቅ የተሻለ ነው ሲሉ ከምክር ቤቱ አባል ለቀረበላ | የዛሬ መረጃ ®

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስልጣን በጋራ ብንለቅ የተሻለ ነው ሲሉ ከምክር ቤቱ አባል ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጡ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ላቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል አንደኛው እና ቀዳሚው በኢትዮጲያ በተደጋጋሚ እየታየ የሚገኘውን የሰላም እጦት እና ሀገርን አደጋ ውስጥ ያስገባው በመንግስት ክፍተት ነውና እርስዎ ስልጣን በመልቀቅ የመፍትሔ አካል ለመሆን አላሰቡም ወይ የሚል ጥያቄ የአብን ተወካዩ የምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ አንስተዋል፡፡

ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ‹‹ ጥያቄው ስልጣን ቢለቁ ከሚለው ይልቅ ብንለቅ የሚለው የተሻለ ነው ›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህግ አውጪ ሆነ አስፈፃሚ እንዲሁም ደግሞ ህግ ተርጓሚ መንግስት እንደመሆኑ መጠን ለሚደርሰው ሁሉም ነገር ኃላፊነትን በጋራ በመውሰድ ስልጣን ብንለቅ የሚለው ሃሳብ የተሻለ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሁሉም ችግር እና ምንጭ እኔ ብቻ ልሆን አልችልምና ሁሉንም ነገር መጋራት የሚገባን በጋራ ነው ሲሉ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ መስጠታቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል ፡፡