Get Mystery Box with random crypto!

ድሬዳዋ : የተረሳ 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ #Ethiopia | በድ | የዛሬ መረጃ ®

ድሬዳዋ :
የተረሳ 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ

#Ethiopia | በድሬዳዋ ከተማ ከሚያሽከረከረው ባጃጅ ላይ የተረሳ 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል።

መኮንን ግርማ ኑሮን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ ባጃጅ ላይ ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው።

ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም እንደተለመደው ለስራ በድሬዳዋ ጎዳና ላይ ከምሽቱ ሶስት ሰአት ላይ ባጃጁን እያሽከረከረ ሳለ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ መሀመድ ዑስማን ከሳቢያን ወደ ኦርቢት ለመሄድ በሱ ባጃጅ ተሳፍረው ወደተባለው ቦታ ማድረሱን ተናግራል።

ይህ ከሆነ ከአንድ ሰአት በኋላ ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እና እንድመለከት ተነገረኝ የሚለው ወጣቱ፤ ከተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሬ ስመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ በርካታ ብር ተቀምጦ ማግኘቱን እና ወዲያው ገንዘቡን ይዞ ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳሬክቶሬት በመምጣት 150ሺህ ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ተናግሯል።

ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፣ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ዑስማን በበኩላቸው፤ ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የምሽት ባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልፀው፣ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።