Get Mystery Box with random crypto!

የዛሬ መረጃ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የሰርጥ አድራሻ: @todaynewsethiopia
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.26K
የሰርጥ መግለጫ

#መረጃ_አይናቅም ‼️
ትኩስ ና አዳዲስ የሀገር ውስጥ ና የአለም ዜናዎችን በፍጥነት ሰብስበን ወደናንተ እናደርሳለን Today News Ethiopia።
መረጃዎች ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ አብሮነታችሁ ያሳዩ
#ለእውነት ና #ለትክክለኛ #መረጃ ብቻ እንሰራለን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-04-16 19:51:10 በካርቱም የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 56 ከፍ ማለቱ ተገለጸ

ትናንት በሱዳን በሀገሪቱ ጦር እና አርሴስኤፍ ሀይሎች መካከል የተጀመረው ውጊያ አዳሩንም ቀጥሏል።

ይህን ተከትሎም የሀገሪቱ ዶክተሮች ኮሚቴ እንደገለጸው በጦርነቱ ምክንያት እስካሁን በካርቱም የሟቾች ቁጥር ወደ 56 ከፍ ብሏል።

የሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል በትናትናው እለት የተከሰተውን ግጭት ትክተሎ በሁለቱም ወገኖች በርካታ የሰራዊት አባላትም ሞተዋ የተባለ ሲሆን፤ ከ600 ገደማ ሰዎች መቁሰላቸውን የሱዳን ዶክተሮች ማእከላዊ ኮሚቴን አስታውቋል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
2.4K views16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 10:03:07 ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለፋሲካ በአል በሰላም አደረሳችሁ!
3.4K views07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 22:21:01 የ1 GB የኢንተርኔት ዳታ ስጦታ ከኢትዮ ቴሌኮም

ኢትዮ ቴሌኮም የስቅለት በአልን ምክንያት በማድረግ የ1 GB የኢንተርኔት ዳታ አገልግሎት ስጦታ ለደንበኞቹ አበርክቷል።

የትንሳኤን ጥቅል ገዝታችሁ ስትጠቀሙ 1GB ነፃ ታገኛላችሁ

እንደ ወግ ልማዳችን እንኳን አደረሰን የምንባባልበትን ልዩ የትንሳኤ የሞባይል ጥቅል እስከ 50% በሚደርስ ቅናሽ ከ1ጊ.ባ ዳታ ስጦታ ጋር ማቅረባችንን በደስታ እንገልጻለን!

ልዩ የትንሳኤ ጥቅሎቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር እንዲሁም በማይ ኢትዮቴል እና *999# ለራስዎ በመግዛት እና ለወዳጅ ዘመድ በስጦታ በማበርከት በዓሉን በደስታ ያሳልፉ!

http://t.me/TodayNewsEthiopia
3.2K views19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 16:34:57
የትንሳዔ እና የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከ256 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የሀገር ባለውለታዎች፣ አቅመ ደካሞች እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች ማዕድ ማጋራት ተከናውኗል። በተጨማሪም 555 የአቅመ ደካማ ቤቶችንም ታደሶ ተሰጥቷል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
1.8K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 15:55:03 የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ለ1 ሺህ 364 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ÷በክልሉ በ6 የማረሚያ7 ሺህ 7 00 ታራሚዎች እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡

የክልሉ ይቅርታ ቦርድ በዓመት ሁለት ጊዜ ለታራሚዎች ይቅርታ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው÷ አሁን ደግሞ በቴክኒክ ኮሚቴ ተጣርቶ የቀረበውን መነሻ በማድረግ ለክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ ለ1 ሺ 364 ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን አቶ ተክሌ ተናግረዋል፡፡

ታራሚዎችም በታነጹትና በታረሙት መሠረት ወደ ማህበረሰቡ ሲገቡ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

http://t.me/TodayNewsEthiopia
2.1K views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 09:54:44
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዲሱ “የመደመር ትውልድ” መጽሐፍ በኦንላይን ገበያ ለሽያጭ ቀረበ

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጻፈውና በቅርቡ የተመረቀው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በተለያዩ አካባቢዎች ለገበያ መቅረቡ ይታወቃል።

አሁን ላይም "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በኢትዮ ፖስት (Ethio Post shop) በኩል በኦንላይን ገበያ ለሽያጭ ቀርቧል።

ስለሆነም በቀጣዩ ሊንክ በመግባት ethio.post/product/genera በዓለም አቀፍ እና በመደበኛ የመገበያያ ዘዴዎች ክፍያ በመፈጸም መጽሐፉን መግዛት እንደሚቻል ተገልጿ።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
3.2K viewsedited  06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 10:42:40 በተቃውሞ ሳቢያ ተዘግቶ የነበረው የደጀን መንገድ፤ ትናንት ለሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት አገልግሎት ክፍት ሆነ

በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ምክንያት ለሶስት ቀናት ተዘግቶ የነበረው የደጀን መንገድ፤ ትናንት ጠዋት ላይ መከፈቱን አንድ የከተማይቱ አስተዳደር ኃላፊ እና ነዋሪዎች ተናገሩ። ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች፤ ከአዲስ አበባ በደጀን ከተማ በኩል ወደ ባህር ዳር ለሚደረግ ጉዞ ገና ትኬት መቁረጥ አለመጀመራቸውን ገልጸዋል።

ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ከተማ የሚወስደው አውራ ጎዳና፤ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን በምትገኘው ደጀን ከተማ የተዘጋው፤ ባለፈው ሳምንት አርብ መጋቢት 29፤ 2015 ዓ.ም ነበር። የአማራ ክልል “ልዩ ኃይል መበተንን የሚቃወሙ” የተባሉ ነዋሪዎች፤ በከተማዋ መግቢያ እና ውስጥ ባሉ ቦታዎች መንገዱን ከዘጉ በኋላ በደጀን በኩል የሚያልፉ የህዝብ እና የጭነት ሀገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎች መተላለፍ አቁመው ቆይተዋል።

ትናንት ማክሰኞ ሚያዝያ 3፤ 2015 ጠዋት ከሁለት ሰዓት ገደማ ጀምሮ ግን፤ ለቀናት ተዘግቶ የነበረው መንገድ ተከፍቶ ቆመው የነበሩ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ እንደጀመሩ የከተማዋ ኮሚዩኒኬሽን ቡድን መሪ አቶ ሞኙ ሆዴ አሳየ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
3.3K views07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 12:56:46 ጎንደር

የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ክልከላዎችን አስቀመጠ።

ኮማንድ ፖስቱ ፤ ክልከላው " የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል " የተቀመጠ መሆኑን ገልጿል።

የተቀመጡ ክልከላዎች ምንድናቸው ?

1. በከተማው ያሉ ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች እስከ ምሽቱ 3:00 ሰዓት ዉጭ አገልግሎት መስጠት ተከልክለዋል።

2. በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 3 እግር ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ዉጭ መንቀሳቀስ ተከልክለዋል።

3. ከተፈቀደለት የመንግስት የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

4. ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ ፣ ገጀራ ፣ አንካሴ ፣ ጦርና ፌሮ ብረት ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

5. በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ ፣ የደበቀ ፣ የሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያሰመለጠ ፣ የፀጥታ ሀይሎችን የህግ ማስከበር ተልዕኮ ማደናቀፍ ማወክ በህግ ተከልክሏል።

6. በማንኛውም ቦታና ስዓት ጥይትም ሆነ ሮኬት ርችት መተኮስ በጥብቅ ተከልክሏል።

7. በተከለከሉ ቦታዎች በእምነት ተቋማት፣ በገቢያዎች፣ ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ፣ በሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶችና ግሮሰሪዎች፣ ልዩ ልዩ መዝናኛ ቦታዎች ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘትና መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

8. የሠራዊቱን ሚሊተሪ (አልባሳት) ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ የተከለከለ ነው ፦ የልዩ ኃይል ፣ የፓሊስ ፣ የመከላከያ ሠራዊት ፣ የፌዴራል ፓሊስ ልብስ መልበስ በጥብቅ ተከልክሏል።

9. ያልተፈቀዱ ስብሰባዎችን ማለትም ያለ መንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ ፣ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት ተከልክሏል።

10. አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ስራን ማስተጓጎል በጥብቅ ተከልክሏል።

11. የአማራን ህዝብ ከጥቃትና ከውርደት ለመታደግ መስዋትነት የከፈሉ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ከተለያየ አካባቢ ተነስተው ወደ ከተማው የመጡ በከተማው በተዘጋጀው ማረፊያዎች እንዲሰባሰቡ ማሳሰቢያ ተለልፏል። ከዚህ ውጭ በተናጠልም ሆነ በቡድን መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ጥይት መተኮስ ተከልክሏል።

12. ፀጉረ ልዉጥ/አጠራጣሪ ሰው ከቤቱ ያሳደረ ፣ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዙ እንዲሁም ለሚመለከተዉ የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በህግ  ይጠየቃል።

መረጃው የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ነው።
 
http://t.me/TodayNewsEthiopia
6.1K viewsedited  09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 20:49:05
አዎን!! ልክ እንደዚህ ነው። በሌሎች የሰዎች ዓላማ ማሳኪያ ሆነህ ለዓመታት ከሰራህ በኋላ በባዶ እጅህ ጡረታ አትጨርስ። ደሞዝ ስለሚያገኝ ብቻ የሕይወት ዓላማህን ችላ እንዳትል እና #ደሞዝ ህልምህን እንድትተው ሲፈለጉ የሚሰጡህ ማስታገሻ መድሃኒት እንደሆነ እንድታውቅ ነው። አሁን ተነስና ቀስ በቀስ ለግል ግቦች እና ራዕይ እሴት ጨምር፣ ደሞዝ በሚከፈልህ ስራህ ላይ ሆነህ እንኳን በትርፍ ሰዓትህ እራስህ ላይ ሥራ። ራስህን ለመስራት ኢንቨስት አድርግ።

መልካሙ ዜና የዕለት ተዕለት ስራችን ላይ ሆነን መለወጥ ከቻላችን ነው።

እንዴት ነው እራሴ ላይ ሰርቼ የምለወጠው?
@Tesfish85
+251985158551 call
2.9K views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 18:00:21 ​​የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ፤ የአማራ ልዩ ኃይልን በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የተወሰነ ውሳኔ የለም አሉ

ይህን ያሉት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው።

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ምን አሉ ?

- በሀገር ደረጃ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ ልዩ ኃይሎችን በፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ለማደራጀት ተወስኖ ወደ ትግበራ ተገብቷል።

- ውሳኔው በፌዴራል መንግሥት እና በክልል መንግሥታት ስምምነት የተወሰነ ሲሆን በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ ይደረጋል።

- በአማራ ክልል ውሳኔውን ለመተግበር እየተሠራ ነው። ይህንን በተመለከተ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር ተወይይተናል።

- በአፈጻጸም ላይ በታየ ክፍተት እና በተነዛው ፕሮፖጋንዳ ችግሮች ተከስተዋል። ችግር እንኳን ቢኖር ተወያይቶ መፍታት ይቻላል።

- አብዛኛው የልዩ ኃይል አባል ውይይቱን አጠናቆ ውሳኔውን  በካምፕ ሆኖ እየተጠባበቀ ነው።

- ልዩ ኃይዩ ትጥቅ የሚፈታና የሚበተን አይደለም ፤ በላቀ አደረጃጃት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የሚያስችል ነው።

- ልዩ ኃይሉ ዓላማውን ተገንዝቦ ለበለጠ ተልእኮ ሊዘጋጅ ይገባል።

- የአማራ ሕዝብ በሁኔታው ቅሬታ ውስጥ ገብቷል።ቅሬታው የመነጨው በተሟላ መንገድ ለሕዝቡ መረጃ ባለመድረሱ ነው።

- አደረጃጀቱ የሚደገፍ፣ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው የሀገርን አንድነት የሚያረጋግጥ ነው።

- አደረጃጀቱ የአማራን ክልል በተለየ መንገድ የሚጎዳ አይደለም።

- የአማራ ክልልን ልዩ ኃይል በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የታለመ ዓላማ የለም።

- በተፈጠረ የመረጃ ክፍተት በአንዳንድ ከተሞች የሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴ፣ የአድማ ጥሪ እና የሰዎች እና የተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴን የመገደብ አዝማሚያዎች እያታዩ ናቸው። አላስፈላጊ አካሄዶች አውዳሚ እና አክሳሪ እንጂ አትራፊ አይደሉም።

- የአማራ ክልል በጦርነት የከረመ ክልል ነው ፤ በጦርነቱ ምክንያት ሕዝቡ ተጎሳቁሏል፣ በጦርነቱ ምክንያት የተጎዳው ኅብረተሰብ እና መሠረተ ልማት ገና ማገገም አልቻለም ፤ ከአንደኛው ችግር ሳናገግም ወደ ሌላ ችግር መሸጋገር ሕዝቡን መጉዳት ነው።

- በመወያየት አላስፈላጊ ጉዳዮችን ማስቆም ይቻላል ፤ ሁሉም አውዳሚ የሆነውን ጉዳይ መከላከል ይገባዋል።

- ግጭት እንዳይፈጠር ወጣቶች እና የሃይማኖት አባቶች የሚመሰገን ሥራ እየሠሩ ናቸው።

- የአማራ ክልል ሕዝብ ጉዳዩን በውል በማጤን፣ በመመካከር እና ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት አስቀድሞ በማሰብ ማስከን ይገባል።

- የአማራ ልዩ ኃይል በተለየ መንገድ የሚጎዳ ውሳኔ አልተወሰነም፣ ወጥና ሀገራዊ ውሳኔ ነው የተደረገው፣ በሁሉም ክልል የሚፈጸም ነው፣ ውሳኔው ለሀገር ግንባታ ታላቅ አስተዋጽዖ አለው።

- ከወቅታዊ ጉዳይ አንጻር የሚነሳው ጥያቄ ትክክል ቢሆንም አፈጻጸሙ ለሀገር የሚጠቅም መሆኑን መገንዘብ ይገባል።

- ከካምፕ የወጡ የልዩ ኃይል አባላት እንዲመለሱ ማድረግ ይገባል።

- የአማራ ሕዝብ ጉዳዩን በሰከነ መንገድ ማየት አለበት ፤ ችግሩ ዳር ወጥቶ ግጭት እንዳይከሰት እያደረጉ ላሉ አካላት ምስጋና ይገባል።

- የልዩ ኃይል አባላት ትጥቅ አትፈቱም፣ የምትበተኑበት ነገር የለም፣ ወደ ላቀ ተልእኮ ነው የምትሸጋገሩት።

- በመደማመጥ ችግሮቻችን እንፈታለን፣ የአማራን ጥያቄዎች እናስመልሳለን።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
3.7K views15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ