Get Mystery Box with random crypto!

የዛሬ መረጃ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የሰርጥ አድራሻ: @todaynewsethiopia
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.26K
የሰርጥ መግለጫ

#መረጃ_አይናቅም ‼️
ትኩስ ና አዳዲስ የሀገር ውስጥ ና የአለም ዜናዎችን በፍጥነት ሰብስበን ወደናንተ እናደርሳለን Today News Ethiopia።
መረጃዎች ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ አብሮነታችሁ ያሳዩ
#ለእውነት ና #ለትክክለኛ #መረጃ ብቻ እንሰራለን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-12 18:11:12
አንጋፋዋ ድምጻዊት ሂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

ሕይወት እንደሸክላን ጨምሮ በርካታ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን እንካችሁ ያለችው ድምጻዊት ሂሩት በቀለ፣ በአደረባት ህመም በሃገር ውስጥና በውጭ በህክምና ስትረዳ ቆይታ በዛሬው እለት ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም ህልፈተ-ሕይወቷ ተሰምቷል፡፡

ከ1950 መጀመሪያ እስከ 1980ዎቹ መጨረሻ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን ያስደመጠችን ሂሩት በቀለ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘማሪነት/አገልጋይነት ስራዎችን ስትስራ እንደነበር ይታወሳል፡፡

የቀድሞ ድምጻዊት ከዛም ዘማሪት ሂሩት በቀለ በተወለደች በ80 ዓመቷ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው፡፡

ሂሩት በቀለ የ7 ልጆች እናት፣የ10 ልጆች አያት እና የ7 ልጆች ቅድመ አያት ነበረች።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
3.0K views15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 15:26:53 በመዲናዋ ሲሚንቶ ከታሪፍ በላይ ሲሸጡ የተገኙ 89 የንግድ ሱቆች ታሸጉ

የከተማ አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ መንግሥት ያወጣው የሲሚንቶ የማከፋፈያና የችርቻሮ ተመን ዋጋ እንዲከበር እንደሚሰራ ገልጾ፤ የተሰጡ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያዎችን በተላለፋ 89 የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።

እርምጃው የተወሰደባቸው በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በለሚኩራ ክፍለ ከተማ የሚገኙና አለአግባብ ከተተመነው የሲሚንቶ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በላይ በመሸጥ፣ ምርት በመደበቅ መሸጫ ቦታቸውን ዘግተው በመጥፋት የተገኙ ሲሚንቶ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች መሆናቸውን ቢሮው አስታውቋል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
4.6K views12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 14:17:37
ብሔራዊ ባንክ ለሳፋሪ ኮም የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድ ሰጠ

የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ እንደገለጹት፣ ባንኩ  የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድ ለሳፋሪ ኮም ሰጥቷል።

ይህም ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድ ያገኘ የመጀመሪያው የውጭ ሀገር ኩባንያ እንደሚያደርገው የብሔራዊ ባንክ መረጃ ያመለክታል።
4.6K views11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 07:20:39 አፋር የፍቅር ሀገር

የሀገሬ ልጆች እንዴት ናችሁ ተስፍሽ ነኝ ወደ ሀገሬ ተመልሻለሁ በአፋር ለምትኖሩ የሀገሬ ልጆች ጥሩ የቢዝነስ እድል ይዤ ብቅ ብያለሁ።

በውስጥ መስመር ያናግሩኝ @Tesfish85
4.6K views04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 23:28:20 ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር ስምምነት ሳይደረስ የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል ተገለጸ

ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ላይ ሳይደርሱ የ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የክፍያ ላይ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

ባለሥልጣኑ ዛሬ ለግልና መንግስተዊ ላልሆኑ ትምህርት ቤቶች ባስተላለፈው ሰርኩላር ደብዳቤ ከወላጆች ጋር ስምምነት ላይ ሳይደረስ የ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ምንም ዓይነት የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል አስታውቋል፡፡

ባለሥልጣኑ በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ የግል ትምህርት ተቋማት የክፍያ ጭማሪውን በተመለከተ ከወላጆች ጋር በነበረ ውይይት ስምምነት ላይ መድረስ ያልተቻሉባቸው መድረኮችን በአካል ተገኝቶ ማረጋገጡን አመልክቷል፡፡

የክፍያ ጭማሪውን በተመለከተ ከተማሪ ወላጅ ተወካዮች እና ከባለሥልጣኑ ጋር ውይይት በማድረግ በሚቀመጥ አቅጣጫ ብቻ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
4.9K views20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 11:56:02
የፈረንሳይ መንግሥት የአብአላ ሆስፒታልን መልሶ ለመገንባት የሚያስችል የ2.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ የመግባቢያ ስምምነት ፈረመ

የፈረንሳይ መንግሥት በአፋር ክልል የሚገኘውን የአብአላ ሆስፒታል መልሶ ለመገንባት የሚያስችል የ2.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ ከጤና ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

ሆስፒታሉ ከ300 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ተገልጿል።

የፈረንሳይ መንግሥት የሚያደርገው ድጋፍ ሆስፒታሉን መልሶ ከመገንባት ባለፈ አገልግሎቱን ለማሻሻል እንደሚያግዘው የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል።

ስምምነቱን ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር የተፈራረሙት በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማርሾው በበኩላቸው፣ በትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት እና በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎችን ለመደገፍ ረገድ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱ ከዚህ በፊት ቃል በተገባው መሠረት እንደሚፈፀም እና የመልሶ የማቋቋም ሥራውም በ2 ዓመት ውስጥ የሚተገበር መሆኑንም ተናግረዋል።
5.3K views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 21:55:59 ሰላም ፎዚ ነኝ Happy life ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁ ዛሬን አንድ ትልቅ እድል ይዤላችሁ መጥቻለሁ።

እራሱ ላይ ለመስራት እና ከራሱ አልፎ በሌሎች ላይ በመስራት በፍጥነት ሳይሆን በርግጠኝነት ስኬታማ ለመሆን ቁርጠኛ የሆኑ 3 ሰዎች ብቻ።

ቀድመው ለመጡ በውስጥ ያናግሩኝ
@HopeActionSuccess
5.4K views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 21:55:19 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ቀናት ይፋ አደረገ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የ 8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 19 እና 20 እንዲሁም የ 6ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 26 እና 27 እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

አያይዘውም ቢሮው ከተማ አቀፍ ፈተናዎቹን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመስጠት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የተናገሩ ሲሆን ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹን የበለጠ ማዘጋጀት እንዲችሉ ከከተማና ክፍለ ከተሞች ጋር በጋራ በመሆን የሞዴል ፈተናዎችን እንዲሰጡ አሳስበዋል።

በ2015 ዓ.ም 75ሺህ 100 የ8ኛ እንዲሁም 75ሺህ 78 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተናውን እንደሚወስዱ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
5.4K views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 11:18:02
በክልሎች ከዛሬ ጀምሮ ነዳጅ በኤሌክትሮኒክ ግብይት እንደሚፈፀም የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ገለፀ

በአዲስ አበባ ከተማ ከሚያዝያ 16፣ 2015 ጀምሮ ነዳጅ በኤሌክትሮኒክ ግብይት እንዲፈፀም በማድረግ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች በሌሎች ክልሎች እንዳይከሰቱ የሚመለከታቸው አካላት ዝግጅት እንዲያደርጉ መደረጉን በባለስልጣኑ የነዳጅ ስርጭት ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ዴሬሳ ኮቱ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ገልጸዋል ።

በአዲስ አበባ ነዳጅን በኤሌክትሮኒክ መገበያየት ሲጀመር የነበረው ሰልፍ አሁን መስተካከሉንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
5.9K viewsedited  08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 14:58:47 የብልፅግና ፓርቲ የወረዳ አመራር ተገደሉ

ከትላንት በስቲያ ከአዳማ ወደ አዋሽ በሚወስደው መንገድ ላይ በተከፈተ ተኩስ በአፋር ክልል በገቢ ረሱ የሓንሩካ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡመር ለማ መገደላቸውን የአፋር ክልል የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት አሳውቋል።

ጥቃቱን " አሸባሪዎች " ናቸው የፈፀሙት ያለው የአፋር ብልፅግና " በፈፀሙት ድንገተኛ ጥቃት የአቶ ኡመር ለማን ህይወት ቀጥፈዋል ብሏል።

ፅ/ቤቱ ባሰራጨው መረጃ ጥቃት አድራሾቹ ላይ የተወሰደ እርምጃ ይኖር እንደሆነ እና ጥቃቱ በተፈፀመበት ወቅት በሌሎች ላይ ጉዳት ደርሶ እንደሆነ በዝርዝር ያሳወቀው ነገር የለም።

ከዚህ ቀደም በዚሁ ቀጠና እጅግ የለየለት የወንጀል ተግባር በታጠቁ አካላት እንደሚፈፀም ሲገለፅ እንደነበር ይታወሳል።

በዚሁ መስመር ታጣቂዎች እንደሚንቀሳቀሱና እንደ ከተማዎች ውስጥ በመግባት ጭምር ሰላማዊ ሰዎችን መግደል፣ በየመንገዱ ሰላማዊ ሰዎችን እያገቱ ከፍተኛ ገንዘብ የመጠየቅ ፤ በአጠቃላይ በቀጠናው ወጥቶ ለመግባት ከፍተኛ ስጋት የመፍጠር እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ የአካባቢው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በተደጋጋሚ መግለፃቸው ይታወሳል።

መንግሥት ይህንን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነና ዜጎች ቀንም ማታም ያለስጋት ሲንቀሳቀሱበት የነበረውን ቀጠና ይህን ያህል ጊዜ ሙሉ በሙሉ ከታጣቂዎች እንቅስቃሴና የወንጀል ተግባር ነፃ ማድረግ ለምን እንዳልቻለ የብዙሀኑ ጥያቄ ነው።

እስከ ዛሬ ድረስ በንፁሃን ላይ ሲፈፀሙት ለነበሩት ጥቃቶች ፣ ዝርፊያዎች ወንጀለኞቹ መቼ ነው ወደ ፍርድ አደባባይ የሚቀርቡት ? መቼስ ነው ፍትህ የሚሰጠው ? የሚለውም ጉዳይ መልስ ይፈልጋል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
6.5K views11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ