Get Mystery Box with random crypto!

የዛሬ መረጃ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የሰርጥ አድራሻ: @todaynewsethiopia
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.26K
የሰርጥ መግለጫ

#መረጃ_አይናቅም ‼️
ትኩስ ና አዳዲስ የሀገር ውስጥ ና የአለም ዜናዎችን በፍጥነት ሰብስበን ወደናንተ እናደርሳለን Today News Ethiopia።
መረጃዎች ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ አብሮነታችሁ ያሳዩ
#ለእውነት ና #ለትክክለኛ #መረጃ ብቻ እንሰራለን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-25 14:12:46
በአዲስ አበባ በሚገኙ 153ቱም ነዳጅ ማደያዎች የነዳጅ ሽያጭ በዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እየተከናወነ ነው

ኢትዮ ቴሌኮም

በአዲስ አበባ በሚገኙ 153ቱም ነዳጅ ማደያዎች የነዳጅ ሽያጭ በዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እየተከናወነ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።

በአዲስ አበባ በሚገኙ ሁሉም ነዳጅ ማደያዎች ባለሙያዎች እና የቴሌብር ወኪሎች ተሰማርተው አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ኢትዮ ቴሌኮም ገልጿል።

በአዲስ አበባ ነዳጅ ማደያዎች ዛሬ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በሆነው የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ደንበኞች በቀላሉ ክፍያቸውን በቴሌብር እየፈጸሙ እንደሆነም ተገልጿል።

ደንበኞች ነዳጅ ለመቅዳት ሲሄዱ በቅድሚያ የቴሌብር አካውንት ከሌላቸው ቴሌብር ሱፐርአፕን http://xn--onelink-om4a.to/75zfa5 በማውረድ ወይም *127# በመደወል በቀላሉ ሂደቱን በመከተል እንዲመዘገቡ ከቴሌብር ጋር በተሳሰሩ 20 ባንኮች፣ በአገልግሎት ማዕከሎች ወይም በቴሌብር ወኪሎች በኩል በቂ ገንዘብ ወደ ቴሌብር አካውንት እንዲያስተለልፉ እና በየነዳጅ ማደያዎቹም በሚገኙ ወኪሎች በኩል ገንዘብ ገቢ በማድረግ የነዳጅ ክፍያን በቀላሉ በቴሌብር መፈጸምም እንደሚችሉ ኢትዮ ቴሌኮም በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ አስታውቋል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
5.2K viewsedited  11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 06:52:42 ከሸኔ ጋር የሚደረገው ድርድር ከነገ ወዲያ ይጀመራል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ከሸኔ ጋር የሚደረገው ድርድር ከነገ ወዲያ በታንዛኒያ እንደሚጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
የወለጋ ሕዝብ እፎይ እንዲል ሁሉም ወገን የበኩሉን እንዲያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ወዳጅነት አደባባይ 'ጦርነት ይብቃ፤ ሰላም እናጽና’ በሚል መሪ ሐሳብ የምስጋና እና የዕውቅና ሥነ ስርዓት ተካሂዷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዚሁ ሥነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ሁለት ዓመት ከመዋጋት 20 ዓመት መወያየት ይሻላል ሲሉም ተናግረዋል።

ይህንን ቀንን እንድናይ ያደረገንን ፈጣሪ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያመሰግን ከአደራ ጭምር አሳስባለሁ ብለዋል።

በሌላ በኩል በቀጣዩ ሣምንት በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት የተመራ ልዑክ ወደ መቀሌ እንደሚያቀና ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የገለጹት።

ልዑኩ የሁሉንም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ያካተተ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
3.1K views03:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 10:55:26
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀኔራል ሰዓረ መኮንን ያስገነባውን ሐውልት እና በስማቸው የሰየመውን ፓርክ አስመረቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቀድሞው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል ሰዓረ መኮንን ያስገነባውን የመታሰቢያ ሐውልት እና በስማቸው የሰየመውን ፓርክ ዛሬ አስመርቋል፡፡የመታሰቢያ ሐውልቱ እና ፓርኩ ግንባታ የተከናወነው በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ርዋንዳ አካባቢ ነው፡፡
4.5K views07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 20:01:51
#BREAKING

የዒድ አልፈጥር በዓል #ነገ መሆኑ ታውቋል።

የሸዋል ወር ጨረቃ  በሳኡዲ አረቢያ በቱሚናር እና ሱዳይር ዛሬ ሀሙስ በመታየቷ የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ ጁምዓ / አርብ ይውላል።

እንኳን ለ1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ምንጭ፦ Haramain Sharifain

http://t.me/TodayNewsEthiopia
2.8K viewsedited  17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 14:42:43
በኬንያ የታገተው ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ክስ መሰረቱ!

ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በፊት ኬንያ ውስጥ “የፖሊስ ደንብ ልብስ” በለብሱ ሰዎች ተወስዶ እስካሁን ያለበት አልታወቀም የተባለው የአቶ ሳምሶን ተክለሚካኤል ቤተሰቦች የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ላይ ክስ መሰረቱ።

የመንግስት አካላቱ ላይ የተከፈተውን ክስ በተመለከተ በዛሬው እለት የአቶ ሳምሶን ባለቤት ወ/ሮ ሚለን ሀለፎም እንዲሁም በፌደራል እና በኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች ጠበቃ የሆኑት አቶ ዳባ ጩፋ (ዶ/ር) በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

ወ/ሮ ሚለን ሀለፎም እንደተናገሩት ከባለቤታቸው መሰወር በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት የተወሰኑ ጥረቶች ቢያደርግም አንድ ዜጋ በውጭ ሀገር መብቱ ሲጣስ ማድረግ ከሚገባውው አንፃር በቂ ባለመሆኑ ክስ መክፈቱ አስፈላጊ ሆኗል ብለዋል።

ጉዳዩን የያዙት የህግ ባለሞያ አቶ ዳባ ጩፋ በበኩላቸው “ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የመጣበት ምክንያት እነዚህ የተከሰሱ አካላት ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ነው። ፍርድ ቤት በህግ አግባብ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማስገደድ የሚችል በመሆኑ እንደሚያስገድዳቸው እንጠብቃለን” ሲሉ ተናግረዋል።

[Addis Zeybe]
4.0K views11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 23:01:04
ትላንት የቱርኳ ኢስታንቡል በድንገት እስከ አስር ኪሎ ሜትር በሚሸፍን ግዙፍ ጥቁር ደመና ተሸፍና ነበር ። ፀሐይ ለ5 ደቂቃ ያህል አልታየችም ። ከተማዋ እንደ ሌሊት ጨለማ ሆና ነበር።

ቪዲዮው ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ ነው።
3.1K views20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 22:40:29
ለቅርጫ ካረዱት በሬ ሆድ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ ያገኙት ዕድለኞች

በአርሲ ዞን ጢዮ ወረዳ ዶሻ በምትባል ቀበሌ በጋራ ሆነው ለበዓል የቅርጫ በሬ ያረዱት ሰዎች ከበሬው ሆድ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ አግኝተዋል። በሬውን በ40 ሺህ ብር የገዙት ተቃራጮቹ፣ ከበሬው ሆድ ውስጥ ያገኙትን ወርቅ በ53 ሺህ ብር በመሸጥ የበሬውን ሥጋ በነፃ በልተው 13 ሺህ ብር ማትረፍ ችለዋል።

ነገር ግን ተቃራጮቹ ሌላ በሬ ለመግዛት ወስነዋል፤ የተቃራጮቹ አስተባባሪ የሆኑት አቶ በቀለ ቀነኒ እንዳሉት፣ ከወርቁ ሽያጭ በተገኘው ገንዘብ ሌላ በሬ ለመግዛት ቀጠሮ ይዘዋል።

ከበሬው ሆድ ውስጥ እንዴት ወርቅ ተገኘ? ሳይንሱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላል? ለሚለው ጥያቄ መልስ የሰጡት በኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የአሰላ የእንስሳት ጤና ማዕከል የላቦራቶሪ ባለሙያ ዶ/ር አብዲሳ ለማ፣ በበረሃማ አካባቢ የሚኖሩ ከብቶች ጥቃቅን ማዕድናት ያላቸውን ተክሎች እየተመገቡ በጊዜ ሂደት ማዕድናቱ በሐሞት ውስጥ እየተጣሩ ወደ ወርቅነት (በተለምዶ ‘የሐሞት ወርቅ’ ወደሚባለው) እንደሚቀየሩ ተናግረዋል ሲል ኦቢኤን ዘግቧል።

ንጥረ ነገሩ በከብቶቹ ሆድ ውስጥ እየቆየ ሲሄድ የሐሞት ፍሳሽን ስለሚመጥጥ ከብቶቹ እንዳይደልቡ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
http://t.me/TodayNewsEthiopia
6.2K views19:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 09:47:49
የጎዳና ላይ ኢፍጣር በሰሜናዊት ኮኮብ መቐለ ከተማ
http://t.me/TodayNewsEthiopia
7.2K views06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 22:10:56 የሱዳን ሕዝብ አሁን ካጋጠመው ሁኔታ ለመውጣት የሚያስችለው ጥበብና ችሎታ ያለው ሕዝብ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

የሱዳን ሕዝብ አሁን ካጋጠመው ሁኔታ ለመውጣት የሚያስችለው ጥበብና ችሎታ ያለው ሕዝብ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው በአረብኛ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የጎረቤት አገር ሱዳን ህዝቦች ከጥንትም ጀምረው ነፃነታቸውን የሚወዱ እና ብሄራዊ ክብራቸውን አስጠብቀው የቆዩ ህዝቦች መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን የሱዳን ህዝብ ከሚወሳባቸው አያሌ መልካም ባህሪያት መሀከል ለጋስነት እና እንግዳ ተቀባይነታቸው ከምንም በላይ ጎልቶ ይጠቀሳል።

እነዚህ እሴቶች ደግሞ ከማህበራዊ ትስስሩ በላይ የኢትዮጵያን እና የሱዳንን ህዝብ የሚያመሳስሉ እና ይበልጥ የሚያቆራኙ ብለውም ከሌላው እንዲለዩ ከሚያረጓቸው እውነታዎች ሁነው እናገኛቸዋለን ብለዋል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
6.3K views19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 13:52:40 በካርቱም በሚሊሻ አባላቱ እና በአገሪቱ ጦር መካከል የሚደረገው ውጊያ ለሦስተኛ ቀን ተጠናክሮ ቀጠለ!

ካርቱምን ጨምሮ በበርካታ የሱዳን ከተሞች በአገሪቱ ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ልዩ የሚሊሻ አባላት መካከል የሚደረገው ውጊያ ለሦስተኛ ቀን ተጠናክሮ ቀጥሏል።በውጊያው ከ100 ያላነሱ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን እና ከ1ሺህ 100 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን የዶክተሮች ስብስብ የሆነ ኮሚቴ ተናግሯል።የዓለም ጤና ድርጅት ደግሞ 83 ሰዎች መሞታቸውን አረጋገጫለሁ ብሏል። ከሟቾቹ መካከል ሦስቱ የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሠራተኞች ናቸው።

ግድያውን ተከትሎ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሱዳን ያለኝን ስራ አቋርጫለሁ ብሏል።ሁለቱም ተዋጊ ኃይሎች በካርቱም እንደ አየር ማረፊያ፣ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያዎችን፣ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ እና ቤተ-መንግሥትን ተቆጣጥረናል ሲሉ እርስ በእርሱ የሚጣረስ መረጃ ሲያወጡ ነበር።

ተዋጊዎቹ ኃይሎች ትናንት እሁድ ረፋድ ላይ ለሰብዓዊነት ሲባል ለጥቂት ሰዓታት የዘለቀ የተኩስ አቁም ስምምነት አድርገው ነበር።በዚህ የተኩስ አቁም ጊዜ ውስጥ የቆሰሉ ወደ ሕክምና ተጓጉዘዋል።ሀኪሞች በካርቱም ሆስፒታሎች ያለው ሁኔታ እጅግ ከባድ መሆኑን እና ውጊያው ባለሙያዎች እና የህክምና ግብዓቶች ወደ ጤና ተቋማት እንዳይደርሱ እክል መሆኑን እየተናገሩ ነው።

[BBC]

http://t.me/TodayNewsEthiopia
6.6K views10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ