Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ በሚገኙ 153ቱም ነዳጅ ማደያዎች የነዳጅ ሽያጭ በዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እየተከናወነ | የዛሬ መረጃ ®

በአዲስ አበባ በሚገኙ 153ቱም ነዳጅ ማደያዎች የነዳጅ ሽያጭ በዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እየተከናወነ ነው

ኢትዮ ቴሌኮም

በአዲስ አበባ በሚገኙ 153ቱም ነዳጅ ማደያዎች የነዳጅ ሽያጭ በዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እየተከናወነ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።

በአዲስ አበባ በሚገኙ ሁሉም ነዳጅ ማደያዎች ባለሙያዎች እና የቴሌብር ወኪሎች ተሰማርተው አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ኢትዮ ቴሌኮም ገልጿል።

በአዲስ አበባ ነዳጅ ማደያዎች ዛሬ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በሆነው የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ደንበኞች በቀላሉ ክፍያቸውን በቴሌብር እየፈጸሙ እንደሆነም ተገልጿል።

ደንበኞች ነዳጅ ለመቅዳት ሲሄዱ በቅድሚያ የቴሌብር አካውንት ከሌላቸው ቴሌብር ሱፐርአፕን http://xn--onelink-om4a.to/75zfa5 በማውረድ ወይም *127# በመደወል በቀላሉ ሂደቱን በመከተል እንዲመዘገቡ ከቴሌብር ጋር በተሳሰሩ 20 ባንኮች፣ በአገልግሎት ማዕከሎች ወይም በቴሌብር ወኪሎች በኩል በቂ ገንዘብ ወደ ቴሌብር አካውንት እንዲያስተለልፉ እና በየነዳጅ ማደያዎቹም በሚገኙ ወኪሎች በኩል ገንዘብ ገቢ በማድረግ የነዳጅ ክፍያን በቀላሉ በቴሌብር መፈጸምም እንደሚችሉ ኢትዮ ቴሌኮም በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ አስታውቋል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia