Get Mystery Box with random crypto!

የዛሬ መረጃ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ todaynewsethiopia — የዛሬ መረጃ ®
የሰርጥ አድራሻ: @todaynewsethiopia
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.26K
የሰርጥ መግለጫ

#መረጃ_አይናቅም ‼️
ትኩስ ና አዳዲስ የሀገር ውስጥ ና የአለም ዜናዎችን በፍጥነት ሰብስበን ወደናንተ እናደርሳለን Today News Ethiopia።
መረጃዎች ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ አብሮነታችሁ ያሳዩ
#ለእውነት ና #ለትክክለኛ #መረጃ ብቻ እንሰራለን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-08 22:07:53
በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የጎዳና ኢፍጣር በደማቅ ሁኔታ ተከናወነ!!
ህሊና ታፈሰ


http://t.me/TodayNewsEthiopia
3.4K views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 10:34:57 በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል

በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገልጿል።

የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ተጠቁሟል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ ተነግሯል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
5.5K viewsedited  07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 18:56:10 በአማራ ክልል ልዩ ኃይልን እና በፌደራል የጸጥታ ኃይሎች መካከል ውጥረት መፈጠሩ ተገለጸ

የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን በግዴታ ትጥቅ ለማስፈታት እንቅስቃሴ በመጀመሩ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች፤ በክልሉ ልዩ ኃይል እና በፌዴራል የጸጥታ ተቋማት መካከል ከፍተኛ ውጥረት መፈጠሩን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አስታወቀ፡፡

የክልሉን ልዩ ኃይል ያለ በቂ ዝግጅት፣ ውይይት፣ የጋራ መግባባትና መተማመን ሳይደረስ በድንገት እና ያለበቂ የጸጥታ ዋስትና ለማፍረስ መንግሥት ያሳለፈው ውሳኔ እና ውሳኔውን ለማስፈጸም እየሄደበት ያለው መንገድ ኃላፊነት የጎደለው መሆኑን አብን አስታውቋል፡፡

ጉዳዩ በአማራ ክልል ብቻ ሳይወሰን በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አለመረጋጋት የሚፈጥር፣ ክልሉን እና ኢትዮጵያን ወደ ሌላ የቀውስ አዙሪት የሚከት አደገኛ አካሄድ መሆኑን አብን ለፌዴራሉ መንግሥትና ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አሳስቧል፡፡

በመሆኑም፣ የገዥው ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ውሳኔውን በአፋጣኝ እንዲቀለብስ እና ከአማራ ክልል መንግሥት እና ከክልሉ ሕዝብ ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት እና ምክክር እንዲደረግ አብን ጠይቋል፡፡

በካምፕ እና በግዳጅ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የአማራ ክልል የልዩ ኃይል ፖሊስ አመራሮች እና አባላት በሙሉ የተፈጠረው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ እንዳይወጣ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡ ልዩ ኃይሉ በጥንቃቄ እና መረጋጋት ራሱን እንዲጠብቅ እና የተፈጠረው ችግር በውይይት እና በመነጋገር እንዲፈታ አብን ጠይቋል፡፡

http://t.me/TodayNewsEthiopia
1.8K views15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 21:21:33
በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ እንሳሮ እና መራሐቤቴን የሚያገናኘው አገር አቋራጭ የጀማ ድልድይ በቀን 27/7/2015 ዓ.ም ሁለት ሲኖ ትራክ ተከታትለው ሲሆዱ አንዱ ሲኖ ትራክ የውሃ መያዣ ቦቴ የጫነ ሲሆን አደኛ በዶውን ሲጓዝ ባልታወቀ ምክንያት ድልድዩ ሊደረመስ ችሏል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
4.2K views18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 15:40:00 የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር 27 አባላት ያሉትን ካቢኔ ይፋ አደረገ

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው አዲሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር 27 አባላት ያሉትን ካቢኔ ይፋ አደረገ። በአዲሱ ካቢኔ ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የሰላም እና ጸጥታ ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊን ሆነው የተሾሙ ሲሆን፤ ሌተናል ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ ደግሞ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደር እና ዴሞክራታይዜሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ሆነዋል።

ከተቋቋመ ሁለት ሳምንት ያስቆጠረው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የካቢኔ አባላቱን በይፋ ያስተዋወቀው ዛሬ ረቡዕ መጋቢት 27፤ 2015 በመቐለ ከተማ ባካሄደው ስነስርዓት ነው። በዚህ ስነ ስርዓት ላይ የክልሉን መንግስት ሲመራ የነበረው የቀድሞ ካቢኔ፤ የአስፈጻሚነት ስልጣኑን በጊዜያዊ አስተዳደሩ ለተቋቋመው አዲሱ ካቢኔ አስረክቧል።

አዲሱ ካቢኔ የተዋቀረው ከህወሓት፣ ከትግራይ ኃይሎች፣ ከምሁራን እና ከብሔራዊ ባይቶ አባይ ትግራይ (ባይቶና) ፖለቲካ ፓርቲ የተውጣጡ አባላትን በማካተተት ነው። የካቢኔው 51 በመቶ ቦታ የተያዘው በህወሓት ሲሆን፤ ተቃዋሚው ባይቶና ፓርቲ ሁለት ቢሮዎችን በኃላፊነት የመምራት ዕድል አግኝቷል። ከትግራይ ኃይሎች በካቢኔው ውስጥ የኃላፊነት ቦታ ያገኙት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ ብርጋዴር ጄነራል ተኽላይ አሸብር፣ ሌተናን ጄነራል ፍሰሃ ኪዳኑ እና ሜጀር ጄነራል ዘውዱ ኪሮስ ናቸው።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
4.7K views12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 14:46:53
Formal education will make you a living; self-education will make you a fortune. Jim Rohn

ራስን ማስተማር፣ራስ ላይ መስራት ሁለንተናዊ እድገትና ሀብት እንድታመጣ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል።


አዲስ እድል ይዞ የመጣውን ገፅ ይቀላቀሉ።
https://t.me/+1Goa6-vNoKw2YThk
4.2K views11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 13:52:13
ዶ/ር ጫላ ዋታ ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ

ምክር ቤቱ የአንድ የምክር ቤት አባልን ያለመከሰስ መብት አነሳ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንድ ምክር ቤት አባልን ያለመከሰስ መብት አነሳ፡፡የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት 13ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው፡፡በጉባኤውም የፍትሕ ሚኒስቴር ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ነው የአንድ ምክር ቤት አባልን ያለመከሰስ መብት ያነሳው፡፡

ያለመከሰሰ መብታቸው የተነሳው የምክር ቤት አባልም የቀድሞው የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶክተር ጫላ ዋታ ናቸው፡፡

ዶክተር ጫላ ዋታ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ወቅት የመንግስት ግዢ ስርዓትን ሳይከተሉ የተለያዩ ግዢዎችን ፈጽመዋል በሚል በሙስና ወንጀል በመጠርጠራቸው ነው።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
3.2K viewsedited  10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 00:38:37
#update

ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ የቁርዓን ንባብ እና የአዛን ውድድር እየተካሄደ ይገኛል። በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያዊው ሙሐመድ ኑር ተሳታፊ ነው።

" መሐመድ ኑር ውድድሩን በማሸነፍ የ800,000 ዶላር አሸናፊ ሆኗል " የሚል ነው።

" ወንድማችን ሙሐመድ ኑር ወደ ቀጣዩ ዙር ወደ ተመረጡት 16 ተወዳዳሪዎች አልፏል እንጂ ገና አንደኛ እንዳልወጣ ታውቋል

" ለወንድማችን ሙሐመድ ኑር መልካም እድል እንመኝለታለን "ም ብለዋል።

በሳዑዲ መዝናኛ ሚኒስቴር የሚዘጋጀውን ውድድር ለመከታተል የምትፈልጉ የአዘጋጁ OtrElkalam የዩቲዩብ ቻናሉ https://youtube.com/@OtrElkalam

የውድድሩ አዘጋጅ መረጃ ለመከታተል የቲዊተር አካውንቱ https://twitter.com/otrelkalam?s=21&t=uFFM6cqH6cX8V_cWl-Un8w

ከዚህ በተጨማሪ ፦ የሳውዲ ጋዜጣ (Saudi Gazette) ሙሐመድን ኑርን በተመለከተ የሰራውን ዘገባ በዚህ አንብቡ : https://saudigazette.com.sa/article/631263
223 views21:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 21:46:57
ማሻ አላህ

ኢትዮጲያዊው ወጣት ዓለም አቀፉን የቁርአን ውድድር በአሸናፊት አጠናቀቀ !!

በሳኡዲ አረቢያ አዘጋጅነት በአለም አቀፍ ደረጃ 156 አገራት በተሳተፉበት የቁርአን ውድድር ኢትዮጵያን የወከለው ኢትዮጵያዊው መሀመድ ኑሩ አንደኛ በመውጣት አሸናፊ ሆኗል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia
1.4K viewsedited  18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 15:53:21 በዓለም የነዳጅ ዋጋ መጨመሩ ተሰማ

ለዋጋ መጨመሩ ዋና መንስኤ የነዳጅ ላኪ አባል ሀገራት (ኦፔክ) ለዓለም ገበያ የሚያቀርቡትን የነዳጅ መጠን ለመቀነስ ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል።

በስምነቱ መሰረትም አባል ሀገራቱ የእለታዊ የነዳጅ ምርታቸውን በ1 ነጥብ 16 ሚሊየን በርሜል ለመቀነስ መስማማታቸውን ተከትሎ እንደሆነ መረጃው ያሳያል።

ነዳጅ ላኪ አባል ሀገራቱ ከሚቀጥለው ግንቦት ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ጠቅሰው በዓለም የነዳጅ ገበያው መጠን በአንድ በመቶ ይቀንሳል ተብሏል፡፡

በዚህ ውሳኔ መሰረትም የዓለም ነዳጅ ዋጋ በመጭው ጊዜ በበርሜል የ10 ዶላር ጭማሪ እንደሚያሳይ ተመላክቷል፡፡

http://t.me/TodayNewsEthiopia
3.1K views12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ