2023-03-08 16:43:41
ከጎረቤት ጋር የጀመረችውን ፍቅር ስላወቀባት ልጇን የተመረዘ በሶ አጠጥታ ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገችው እናት!
በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ በአይጥ መርዝ የተመረዘ በሶ ለልጇ አጠጥታለች የተባለችዉ የ32 ዓመቷ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሏ ፖሊስ አስታወቀ።
በዞኑ ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ቶሚ ገረራ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችዉ ወይዘሮ ጎረቤት ከሚገኝ አባወራ ጋር በድብቅ የፍቅር ግንኙነት መጀመሯ በሰዎች ዘንድ የሚወራዉ ወሬ ከ16 አመቱ ታዳጊ ልጇ ጆሮ ገብቶ ኖሮ የሰማዉን ነገር በአይኑ አይቶ ለማረጋገጥ በትእግስት ነገሩን ሲከታተል ቆይቷል።
ልጅ እናቱ በመንደርተኛዉ የታማችበትን የፍቅር ግንኙነት ትክክል መሆኑ የእርግጠኛ በሆነ ጊዜ በምድራዊ ህይወት መልካም ስምና ክብርን የሚያኮስስ በሰማያዊዉ ቤትም የፈጣሪን ህግ በመጣስ የሚያስጠይቅ ነዉና ልጅ ለእናቱ የእናትነት ክብር ሳይነፍግ በትህትና ቀርቦ መክሮ ሊመልሳት በሞከረ ጊዜ በእሺታ ተቀብላዉ ነበር።
የልጇን ምክር ተቀብላ በእሺታዋ ከመፅናት ይልቅ የእሱን ምክር ወደጎን ትታ ከሰዉየዉ ጋር የነበራትን ግንኙነት አጠናክራ ቀጠለች በዚህም በሰዉ ትዳር ላይ ተደርባ የጀመረችዉ ፍቅር እናቱን ሊያሳጣዉ እንደሚችል ስጋት የገባዉ ልጅ በድጋሚ እናቱን መክሮ ሊመልስ ጥረት ማድረጉ ቀጠለ።
እናት ከጎረቤት የምትሰማዉ የፍቅር ቋንቋ ከልጇ ምክር ጋር ስታነፃፅረዉ የልጇ ምክር ለጆሮዋ ያልተመቸ ሆኖ ቢሰማት የጀመረችዉ የፍቅር ግንኙነት ከማቋረጥ ይልቅ ልጇን ከአጠገቧ ገለል ልታረገዉ ከዉሳኔ ደረሰች።
የካቲት 23 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት አካባቢ የ16 ዓመቱ ታዳጊ ከወላጅ እናቱ የቀረበለት ቤት ያፈራዉን ማእድ ከቀማመሰ በኋላ ለተመገበዉ ምግብ ማወራረጃ ይሆን ዘንድ ያዘጋጀችለት በሶ ጠጥቶ ፈጣሪዉንም እናቱንም አመስግኖ ከቤት ወጣ ይላል።
ታዳጊዉ ከደቂቃዎች በኋላ ከወደ ሆዱ በሚሰማዉ የህመም ስሜት ምክንያት ፊቱን ላብ አጥምቆት እራሱን ስቶ ይወድቅና ነብስ ዉጪ ግቢ ጭንቀቱ በረታ።
የአካባቢዉ ህብረተሰብ ታማሚዉን አፈፍ አድርጎ በፍጥነት ነበር ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ያደርሱታል። ሀኪሞች የወጣቱ ዉስጥ መመረዙ በሁኔታዉ በመረዳታቸዉ ህይወቱን ለማትረፍ አስፈላጊዉ ህክምና ቢያደርጉለትም ከቆይታ በኋላ የወጣቱ ህይወት ማለፉ እዉን ሆነ።
እናት ዘጠኝ ወራትን በሆዳ አመታትን በጀርባዋ ተሸክማ የደሟ ተዋፅኦ የሆነዉን ወተት ከጡቶችዋ እያስማገች የምታሳድግ አሳድጋም ለቁምነገር ለማብቃት ስለ ፍቅሯ ዋጋ የምትኸፍል መሆኗ የሚታወቅ ሀቅ ነዉ።
በሶዶ ዙሪያ ወረዳ የቶሚ ገረራዋ እናት ግን ለልጇ ከምግብ በኋላ ለማወራረጃነት በሰጠችዉ የተበጠበጠ በሶ ዉስጥ የአይጥ መርዝ አድርጋበት ኖሮ ለዘለአለሙ መልሳ ላታገኘዉ የአብራኳ ክፋይ እንዲህ ባለ ጭካኔ እቺን አለም ሊሰናበት የግድ ሆነ።
እቺህ ተጠርጣሪ ልጇን የሰዋችለት የጎረቤት ፍቅር ከነ አካቴዉ መልሳ ላታገኘዉ እንደምትችል አልጠረጠረችምና አሁን በፈፀመችዉ የግድያ ወንጀል ተጠርጥራ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ ማጣራት ጀምሯል።
ከሀለት ያጣች ሆና በድርጊቷ ብትፀፀት የፈሰሰ ዉሃ አይታፈስም አይነት ግራ ተጋብቶ ዉስጥን ጭንቀት ቢሞላዉ ዉጤቱ የዜሮ ብዜት ነዉና ምንስ ሊፈይ መረጃው የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን ነው።
http://t.me/TodayNewsEthiopia
3.0K views13:43