Get Mystery Box with random crypto!

በተቃውሞ ሳቢያ ተዘግቶ የነበረው የደጀን መንገድ፤ ትናንት ለሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት አገልግሎት | የዛሬ መረጃ ®

በተቃውሞ ሳቢያ ተዘግቶ የነበረው የደጀን መንገድ፤ ትናንት ለሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት አገልግሎት ክፍት ሆነ

በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ምክንያት ለሶስት ቀናት ተዘግቶ የነበረው የደጀን መንገድ፤ ትናንት ጠዋት ላይ መከፈቱን አንድ የከተማይቱ አስተዳደር ኃላፊ እና ነዋሪዎች ተናገሩ። ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች፤ ከአዲስ አበባ በደጀን ከተማ በኩል ወደ ባህር ዳር ለሚደረግ ጉዞ ገና ትኬት መቁረጥ አለመጀመራቸውን ገልጸዋል።

ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ከተማ የሚወስደው አውራ ጎዳና፤ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን በምትገኘው ደጀን ከተማ የተዘጋው፤ ባለፈው ሳምንት አርብ መጋቢት 29፤ 2015 ዓ.ም ነበር። የአማራ ክልል “ልዩ ኃይል መበተንን የሚቃወሙ” የተባሉ ነዋሪዎች፤ በከተማዋ መግቢያ እና ውስጥ ባሉ ቦታዎች መንገዱን ከዘጉ በኋላ በደጀን በኩል የሚያልፉ የህዝብ እና የጭነት ሀገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎች መተላለፍ አቁመው ቆይተዋል።

ትናንት ማክሰኞ ሚያዝያ 3፤ 2015 ጠዋት ከሁለት ሰዓት ገደማ ጀምሮ ግን፤ ለቀናት ተዘግቶ የነበረው መንገድ ተከፍቶ ቆመው የነበሩ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ እንደጀመሩ የከተማዋ ኮሚዩኒኬሽን ቡድን መሪ አቶ ሞኙ ሆዴ አሳየ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia