Get Mystery Box with random crypto!

ለበሬ መግዛ የተቀመጠ ከ263ሺ ብር በላይ በሻማ ምክንያት ከጥቅም ውጪ ሆነ ክስተቱ ግንቦት 2 | የዛሬ መረጃ ®

ለበሬ መግዛ የተቀመጠ ከ263ሺ ብር በላይ በሻማ ምክንያት ከጥቅም ውጪ ሆነ


ክስተቱ ግንቦት 2 2015 ዓ/ም ነው ያጋጠመው፣ አቶ ግዛቸው ወርቅነህ እና ጓደኛቸው አዲሱ ሳላስብ የተባሉት የቻግኒ እና የጨረቃ ነዋሪዎች በሬ ለመግዛት በሚል ወደ ግልገል በለስ ከተማ ይሄዳሉ፣ ግልገለ በለስ ደርሰው በዋጋ ባለመግባባት የበሬ ግዢው ሳይፈፀም በመቅረቱ ግሪን ላንድ ከሚባለው ሆቴል በመሄድ አልጋ ይዘው ከቆዩ በሁዋላ ማታ ላይ መብራት ባለመኖሩ ምክንያት የተለኮሰውን ሻማ ሳያጠፉ ሻይ ቡና እንበል በሚል ከምሽቱ 4:00 ሰዓት አካባቢ ወጣ እንዳሉ ለፋስት መረጃ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ሻማው የተቀመጠበትን እቃ በእሳት መያዝ ይጀምራል በእሱ ብቻ አላበቃም ከስር ያለውን የአቶ ግዛቸውን ሻንጣ የእሳቱ ሰለባ ይሆናል። የቃጠሎ ሽታ መኖሩን እና ጭሱን ያየው የሆቴሉ ባለቤት እና በቦታው የነበሩ ሰዎች በሩን ገንጥለው በመግባት እሳቱን ለማጥፋት የቻሉ ሲሆን ሁለቱ ጓደኛሞች የሰውን መሯሯጥ አይተው ወደ አልጋቸው ሮጠው ቢደርሱም የአቶ ግዛቸው ሻንጣ በውስጡ ከያዘው የበሬ መግዣ ብር 280,000 ጋር በእሳቱ የተቃጠለ ሲሆን ከተቃጠለው ብር ውስጥ በተደረገው የመለየት ስራ አገልግሎት ላይ ሊውል የሚችል 16,200 ብር የተለየ ሲሆን ቀሪው 253,800 ያህሉ በእሳቱ ተቃጥሎ ከጥቅም ውጩ መሆኑን ከግ/በለስ ፖሊስ ፋስት መረጃ ሰምቷል።

የጓደኛው የአዲሱ ሳላስብ ሻንጣ ከሻማው ራቅ ብሎ የነበረ በመሆኑ በውስጡ ከነያዘው 220,000 ብር ጋር ምንም ጉዳት ሳይደርሰበት ሊተርፍ ችሏል::

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
http://t.me/TodayNewsEthiopia