Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ መንግሥት በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የቀረበበትን የሰብአዊ መብት ጥሰት ክስ በፍፁ | የዛሬ መረጃ ®

የኢትዮጵያ መንግሥት በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የቀረበበትን የሰብአዊ መብት ጥሰት ክስ በፍፁም አይቀበልም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተከስቷል ሲል የደረሰበትን ድምዳሜ የኢትዮጵያ መንግሥት በፍፁም እንደማይቀበለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ጉዳዩን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር በጋራ ካደረጉት ምርመራ አንፃር ሲታይ ምንም አዲስ ግኝት ያልተካተተበት ነው ብሏል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያቀረበበትን ባዶ ውግዘት በፍፁም እንደማይቀበለው ገልጿል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ያወጣው መግለጫ አንድን ወገን ብቻ መወንጀል ላይ ያነጣጠረ መሆኑንም ነው ሚኒስቴሩ በመግለጫ የጠቆመው።