Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት  በሸገር ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ የሚገኘው | የዛሬ መረጃ ®

የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት  በሸገር ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ የሚገኘው የመሰጂዶች ፈረሳ በአሰቸኳይ እንዲቆም አሳሰበ

በኦሮሚያ ክልል "በሸገር ሲቲ" እየፈረሱ ያሉት መሰጂዶች በአሰቸኳይ እንዲያስቆም ለኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ደብዳቤ   መጻፉን አስታውቋል።በጠቅላይ ምክር ቤቱ በደብዳቤ፤ በኦሮሚያ ብሔራዊ  ክልላዊ መንግሥት እየፈረሱ ያሉ መስጂዶች በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ ጠይቋል።

የፈረሱ መስጂዶች በሸገር ከተማ አስተዳደር በፍጥነት እንዲሰሩና ሕዝበ ሙስሊሙን አስተዳደሩ በይፋ ይቅርታ መጠየቅ እንዳለበት በፃፈው ደብዳቤ አሳስቧል።የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለጠቅላይ ምክር ቤቱ በተፃፈው ደብዳቤ መሠረት:-

1.በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ዉንዴሳ ወረዳ ልዩ ሥፍራ ቀርሳ በቀን 14/07/15

2. በሸገር ከተማ ሰበታ ክፍለ ከተማ መጉላ ቶውፊቅ መስጂድ 19/08/15

3. በሸገር ከተማ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ወረዳ ልዩ ስሙ አን ኢ ሳይት ሰላም መስጂድ  በቀን 24/08/25

4. በሸገር  ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ አሸዋ ሜዳ በቀን 25/08/15 መፍረሳቸውና ጉዳዩ ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ደብዳቤ መጻፉም ተገልጿል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia