Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ግብረ ኃይሉ “በአማራ ክልል ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ኃይሎች ላይ እርምጃ | የዛሬ መረጃ ®

ሰበር ዜና

ግብረ ኃይሉ “በአማራ ክልል ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ኃይሎች ላይ እርምጃ እየወሰደኩ ነው” አለ!!

የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል “በአማራ ክልል ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ እርምጃ እየወሰድኩ ነው” አለ።

የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ባወጣው መግለጫ፤ ለአማራ ሕዝብ እንታገላለን በሚል በውስጥም በውጭም በመቀናጀት የራሳቸውን ህቡዕ አደረጃጀት የፈጠሩ አካላት ከመሰል ቡድኖች ጋር በመቀናጀት የሕዝቡን የቁርጥ ቀን ልጆች መልሰው እየበሉ ይገኛሉ። “እነዚህ ኃይሎች በትናንትናው ዕለትም የአማራ ክልል ብልፅግና ጽሕት ቤት ኃላፊ የሆነውን ግርማ የሺጥላን በመግደል አስነዋሪ ድርጊታቸውን አስመስክረዋል” ብሏል ግብረ ኃይሉ።

“በአማራ ክልል ሕገመንግስታዊ ሥርዓቱን በማፍረስም ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠርም ሲጥሩ መቆየታቸውን” መግለጫው አመላክቷል።

የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይልም ይህን ተከትሎ አስፈላጊና ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ነው የገለጸው።

ይሄ ጽንፈኛ ኃይል በአማራ ክልል ሳይገደብ እንደ ሀገርም መንግስትን በኃይል ከስልጣን ለማስወገድ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም ያለው የጋራ ግብረ ኃይሉ መግለጫ÷ ከዚህ የጥፋት መንገዳቸው እንዲመለሱ በተደጋጋሚ የተሰጣቸውን ዕድል ከመጠቀም ይልቅ አሁንም በሕ ገወጥ ተግባራቸው መቀጠላቸውን አመልክቷል፡፡

በዚህ ህገ ወጥ ተግባራቸውም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በሕግ እየታየ የሚገኙ በርካታ የቡድኑ አባላት መኖራቸውንም ግብረ ኃይሉ አስታውቋል፡፡ መንግስት በሀገሪቱ ብሎም በክልሉ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ በሌሎቸም የሕገ ወጥ ቡድኑና ቡድኑን በገንዘብና በሐሳብ በህቡእ በሚደግፉ አካላትና ግለሰቦች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ነው ያስታወቀው፡፡

በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ የፅንፈኛ ቡድኖቹ ደጋፊዎች በዚህ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጅ ላይ የተፈፀመውን ግድያ ከመኮነን ይልቅ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ገዳይ ቡድኖቹን ሲደግፉ ተስተውለዋል ብሏል መግለጫው፡፡ሐሳብን በሐሳብ ከማሸነፍ ይልቅ ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት ባፈነገጠ መልኩ በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ የፈጸሙትን ፅንፈኛ ቡድኖች ሕዝቡ በአንድነት በማውገዝ ኢትዮጵያዊ ጨዋነቱን ሊያስመሰክር ይገባልም ብሏል፡፡

በአቶ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ የፅንፈኛ ኃይሎቹን ትክክለኛ መልክና ገፅታ ለሕዝቡ በይፋ ያጋለጠ ነው ብሏል የደኅንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ኃይል፡፡ መንግስት ለሕዝቡ ሰላምና ደኅንነት መረጋገጥ ግዴታውን ለመወጣት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ የጀመረ በመሆኑ÷ ሕዝቡም ይሄንን ተገንዝቦ የፌደራል እና የክልል የፀጥታ አካላት ተጠያቂነትን ለማስፈን የጀመሩትን እንቅስቃሴ ጥቆማና መረጃ በመስጠት እንዲደግፍ ጥሪ አቅርቧል፡፡ የፅንፈኛ ኃይሎቹን አስነዋሪ ተግባር በመሸፋፈን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች መሰረተ ቢስ ወሬዎችን ከሚያሰራጩ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ሕብረተሰቡ ራሱን እንዲጠብቅ ግብረ ኃይሉ አሳስቧል፡፡

http://t.me/TodayNewsEthiopia