Get Mystery Box with random crypto!

በሱዳን የተኩስ አቁም ስምምነቱ ቢራዘምም ውጊያው ቀጥሏል! የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ተኩስ አቁሙን | የዛሬ መረጃ ®

በሱዳን የተኩስ አቁም ስምምነቱ ቢራዘምም ውጊያው ቀጥሏል!

የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ተኩስ አቁሙን ለማራዘም የተስማሙ ቢሆንም ትናንት ተዋጊ ጄቶች ዋና ከተማዋ ካርቱም ያሉ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ይዞታዎች ደብድበዋል።

የጦር ሰራዊቱ እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በተደጋጋሚ ሲጣስ የነበረውን የተኩስ አቁም እንዲያራዝሙ ሳውዲ አረቢያ እና ዩናይትድ ስቴትስ ግፊት ማድረጋቸውን ተከትሎ ጥቂት ሰዐት ሲቀረው በተጨማሪ 72 ሰዐት ለማራዘም መስማማታቸውን ይፋ አድርገዋል።

ውጊያው እንዲቆም ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ የውጭ አካላት ተወካዮች በተኩስ አቁሙ መራዘም መደሰታቸውን ገልጸዋል።የአፍሪካ ህብረት፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፥ ሳውዲ አረቢያ፥ የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች፥ ብሪታኒያ እና ዩናይትድ ስቴትስ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

"ሁለቱ ወገኖች ይበልጡን ዘላቂ በሆነ መንገድ ግጭቱ እንዲቆም ወደሚያስችል ንግግር ለማምራት ብሎም የሰብዐዊ ረድዔት ያለእንቅፋት መግባት ለማስቻል ዝግጁ መሆናቸው አስደስቶናል" ብለዋል።በተያያዘ ዜና ትናንት ተዋጊ አውሮፕላኖች በዋና ከተማዋ ሰሜናዊ ጠርዝ አካባቢ ሲበሩ እንደነበር የመድፍ እና የከባድ አውቶማቲክ መሳሪያ ተኩስም ይሰማ እንደነበር ዕማኞች ገልጸዋል።

ነገ ቅዳሜ ሁለት ሳምንት በሚደፍነው የሱዳን ውጊያ ቢያንስ 512 ሰዎች ሲገደሉ 4193 መቁሰላቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚንስቴር መረጃ ያሳያል።ዳርፉር ውስጥም ውጊያው ማገርሸቱን ዘገባዎች አመልክተዋል።

http://t.me/TodayNewsEthiopia