Get Mystery Box with random crypto!

Tikvah-University

የሰርጥ አድራሻ: @tikvahuniversity
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 214.08K

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 252

2022-05-22 12:05:12
#Wollo_University

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 823 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና በእንስሳት ሕክምና ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ከዛሬ ተመራቂዎች ውስጥ 106ቱ በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ከደረሰበት ውድመት መልሶ በመቋቋም የመማር ማስተማር ሥራውን ዳግም በማስጀመር፤ ለተማሪዎቹ ቅዳሜ እና እሁድ የማካካሻ ትምህርት በመሰጠት ለምርቃት እንዲበቁ መደረጉን ገልጿል።

@tikvahuniversity
16.7K views09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 20:48:04
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት በፍተሻ ላቦራቶሪ የISO/IEC 17025 ዓለም ዐቀፍ ዕውቅና አገኘ።

ኢንስቲትዩቱ ዓለም ዐቀፍና ብሔራዊ መሥፈርት  ማሟላቱ በፊዚካልና ኬሚካል ፍተሻዎች መረጋገጡን ተከትሎ በኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ዕውቅና ተሰጥቶታል።

ኢንስቲትዩቱ ዕውቅና ማግኘቱ በአማራ ክልል ለሚገኙ እና በጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ ለተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ለሚያመርቷቸው ምርቶች የጥራት የላቦራቶሪ ፍተሻ ውጤት መስጠት ያስችለዋል።

በ2003 ዓ.ም የተቋቋመው የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልገሎት፤ መስፈርቶችን ላሟሉ 13 ተቋማት የአክሪዲቴሽን አገልግሎት ዕውቅና መስጠቱን በዚህ ሳምንት መግለጹ ይታወቃል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥቁር  አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሌላው በሕክምና ላቦራቶሪ ዕውቅና የተሰጠው የትምህርት ተቋም ነው።

@tikvahuniversity
11.7K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 19:47:56
#የትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ማቋቋሚያ ደንብን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

ምክር ቤቱ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በቦርድ እንዲመራም ወስኗል።

በዚህም ለባለሥልጣኑ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመዋል፦

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የቦርድ ሰብሳቢ ሆነዋል።

ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ ተስፋዬ ዳባ፣ ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) እና ሳህረላ አብዱላሂ በአባልነት ተመድበዋል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አንዱዓለም አድማሴ (ዶ/ር) የሥራ አመራር ቦርዱ አባል እና ፀሀፊ ሆነዋል።

@tikvahuniversity
13.3K views16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 13:26:29
#Update
#Mizan_Tepi_University

በ2014 ዓ.ም ወደ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ግንቦት 17 እና 18/2014 ዓ.ም እንደሆነ መገለጹ ይታወሳል።

አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ቦታ፦

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ~ ቴፒ ግቢ

የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ~ ሚዛን ግቢ

ዩኒቨርሲቲው ሚዛን አማን እና ቴፒ ከተሞች ላይ ወደየካምፓሶቹ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አውቶብሶች እንደተዘጋጁ ገልጿል።

ተጨማሪ መረጃ እና ድጋፍ ለማግኘት፦

ለሚዛን አማን
• 09-28-03-95-25
• 09-67-94-52-86
• 09-17-86-53-07
• 09-21-29-18-36

ለቴፒ
• 09-25-01-88-58
• 09-30-63-63-73

@tikvahuniversity
18.1K viewsedited  10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 11:53:50
የት ለመማር ወሰኑ?

በ Software Engineering እና በ Information Technology and Systems በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርትዎን ለመማር ወደ #ቢትስኮሌጅ ቢመጡ አብዝተው ያተርፋሉ።

በአራት ዓመት ውስጥ በዲግሪ ብቻ ሳይሆን ብቁ ሰራተኛ ሆነውም ይመረቃሉ።

ከፍተኛ ልምድ ያላቸው መምህራን፣ ጥራታቸውን የጠበቁና በዘመናዊ መልክ የተደራጁ የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ-መፅሀፍት፣ የኮምፒዩተር ላብራቶሪዎች እና እጅግ ዘመናዊ የአይቲ መሠረተ ልማት #በቢትስኮሌጅ የተሟሉ ናቸው።

ለማመልከት እና ለበለጠ መረጃ፦

ድረ-ገጽ www.bitscollege.edu.et

0982363636
0978028655

#BITSCollege
17.4K viewsedited  08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 11:51:26
#Update

በሰሜን ጎንደር ዞን በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያልወሰዱ እና ፈተናውን ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በሙሉ በቀጣይ ዓመት ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

የዞኑ ትምህርት መምሪያ ተማሪዎቹ በቀጣይ ዓመት ለሚሰጠው ፈተና ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

በዚህም የማጠናከሪያ ትምህርት ከግንቦት ወር ጀምሮ ለሁለት ወራት እንደሚሰጥ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ገልጿል።

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያልወሰዱ እና ፈተናውን ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች ከ2014 ዓ.ም ተፈታኞች ጋር በድጋሚ ፈተናውን እንዲፈተኑ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ መወሰኑ ይታወሳል።

(በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ ስለጉዳዩ የጻፈው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
15.7K views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 11:25:09 #Samara_University

10ኛው ሀገር ዐቀፍ የቱሪዝም ጥናት እና ምርምር ኮንፈረንስ በሠመራ እየተካሄደ ነው።

የክልሉን የቱሪዝም ሀብት ማስተዋወቅና በጦርነት እና በኮሮቪድ-19 ወረርሽኝ የተቀዛቀዘውን የጎብኚዎች ፍሰት ማነቃቃት የጉባኤው ዓላማ መሆኑ ተገልጿል።

በቱሪዝም የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎች በመድረኩ ለውይይት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።

ኮንፈረንሱን የኢትዮጵያ ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዮት፣ የአፋር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና የሠመራ ዩኒቨርስቲ በጋራ አዘጋጅተውታል፡፡

@tikvahuniversity
15.1K viewsedited  08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 11:06:58
#Bahir_Dar_University

የጨርቃ ጨርቅ እና ፋሽን ዓለም ዐቀፍ ጉባኤ፣ ባዛርና ኤግዚቢሽን በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።

በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ ግቢ በተከፈተው አውደ ርዕይ ሸማች እና አምራቾች እየተገበያዩ ይገኛሉ።

በጉባዔው ጥናታዊ ፅሁፎችና የልምድ ተሞክሮዎች የቀረቡ ሲሆን የጨርቃ ጨርቅ እና ቆዳ ውጤቶችም ለእይታ ቀርበዋል።

ዛሬ ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ዓለም ዐቀፍ የፋሽን ትርዒት የሚቀርብ ሲሆን የመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ይሆናልም ተብሏል።

ጉባዔው በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና በኢትዮጵያ ቴክስታይል ኢንስቲትዩት በጋራ ተዘጋጅቷል።

@tikvahuniversity
17.1K views08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 22:18:07
#Addis_Ababa_Education_Bureau

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የአካዳሚክ ካላንደር ማሻሻያ አድርጓል።

የ8ኛ ክፍል ከተማ ዐቀፍ ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 29/2014 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ከሰኔ 20 እስከ 23/ 2014 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

የውጤት ማስረጃ የሚሰጥበት ቀን ሐምሌ 05/2014 ዓ.ም።

(ዝርዝር መረጃው ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
8.5K views19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 21:16:02
#Werabe_University

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ ከ3 ሺህ 200 በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

የመማር ማስተማር ሥራ ከጀመረ ወዲህ ዘንድሮ ለአምስተኛ ዙር አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የሚቀበለው ዩኒቨርሲቲው፤ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ግንቦት 15 እና 16/2014 ዓ.ም ለመቀበል ጥሪ አድርጓል።

ለአዲስ ገቢ ተማሪዎቹ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መኪናዎች መዘጋጀታቸውን የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት መሀመድ አዎል (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

በ2010 ዓ.ም የማስተማር አገልግሎት መስጠት የጀመረው ወራቤ ዩኒቨርሲቲ አሁን ላይ ከ5 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በመደበኛና በተከታታይ መርሃ ግብሮች በማስተማር ላይ ይገኛል።

@tikvahuniversity
11.8K views18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ