2022-05-29 11:21:44
የቴክኒክና ሙያ ምዘናን ወደ ዓለም ዐቀፍ ደረጃ የሚያሸጋግር ስምምነት ተፈረመ።
በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ታንዛኒያ መካከል ሲደረግ የነበረው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ምዘናን ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያሳድጋል የተባለው ፕሮጀክት በሦሥቱ አገሮች ተፈርሞ ጸድቋል።
በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና የሚመረቁ ተማሪዎችና መምህራን በሦሥቱ አገሮች ተንቀሳቅሰው የመስራት ዕድል ይፈጠርላቸዋል ተብሏል፡፡
ስምምነቱ በዘርፉ ቀጠናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም ዐቀፋዊ ተወዳዳሪነት ያላቸው ምሁራንን ለማፍራት ያስችላል መባሉን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡
የሦሥቱ አገሮችን የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ለማሳደግ በዓለም ባንክ የሚደገፍ "የምስራቅ አፍሪካ አገሮች የክህሎት ሽግግር (EASTRIP)" የተባለ ፕሮጀክት ወደ ሥራ መገባቱ ይታወቃል፡፡
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ባዘጋጀው ዓውደ ጥናት ላይ እንደተገለጸው፤ ሦሥቱ አገሮች የተስማሙበት ወጥ የሆነ የጋራ የምዘና ሥርዓት ሲሠራ ቆይቶ የኬንያ እና ታንዛኒያ ሚኒስትሮች በተገኙበት ስምምነት ሆኖ ጸድቋል፡፡
በስምምነቱ መሠረት ኢትዮጵያ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ቀጠናዊ የምዘና መስጫ ማዕከል እንደምትሆን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አሰግድ ጌታቸው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እስካሁን በቴክኒክና ሙያ እስከ ደረጃ ስምንት ሥልጠና ትሰጥ የነበረ ሲሆን ስምምነቱ እስከ 10 እና 11 ደረጃዎች ከሚሰጡ አገሮች ጋር መደረጉ በኢትዮጵያ የሚሰጠውን ደረጃ እንደሚያሳድገው ሪፖርተር ዘግቧል።
@tikvahuniversity
16.0K views08:21