Get Mystery Box with random crypto!

Tikvah-University

የሰርጥ አድራሻ: @tikvahuniversity
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 214.08K

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 246

2022-05-31 22:26:19
#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም የተመደቡለትን አዲስ ገቢ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ለመቀበል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያጠናቀቀ መሆኑን አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው በተወሰኑ ችግሮች ምክንያት የ2014 ዓ.ም መደበኛ ተማሪዎችን ለመቀበል የዘገየ ቢሆንም አሁን ላይ ለችግሮቹ መፍትሄ በመስጠት ተማሪዎቹን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ገልጿል፡፡

የውሃ ችግርን ሙሉ በሙሉ በመቅረፍ ዩኒቨርሲቲው የራሱ የሆነ በቂ የውሃ አቅርቦት እንዲኖረው መደረጉን የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንት አስማረ መለሰ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

የተማሪዎች የመኝታ ክፍል ችግርን ለመፍታት በተሠራ ሥራ፤ እያንዳንዳቸው 716 ተማሪዎችን የመያዝ አቅም ያላቸው ሦሥት ህንጻዎች በማስገንባት ርክክብ መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን ከ3 ሺህ 440 በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

@tikvahuniversity
7.0K views19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 15:09:08
#ነጻ_የትምህርትና_የሥራ_ዕድሎች_በፊንላንድ
#RiftValleyUniversity

ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ሲልክሮድ አካዳሚ እና ኤዱኔሽን ፊንላንድ ከተባሉ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር በፊንላንድ ነጻ የትምህርት እና የሥራ እድሎች የሚገኝበት ዕድል አመቻችቷል።

ፍላጎት ያላቸውና መስፈርቶችን የሚያሟሉ አመልካቾች
በነሐሴ 2014 ዓ.ም እና በመስከረም 2015 ዓ.ም ፊንላንድ ለምታደርገው ቅበላ ተማሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

በመሆኑም በቅድመ-ምረቃ፣ ድህረ-ምረቃ፣ ሁለት ዲግሪ በአንድ ጊዜ የትምህርት ዕድሎች ተጠቃሚ ለመሆን እና የሥራ ዕድሎች ለመስጠት ምዝገባ እያካሄደ ነው።

ከዚህ በታች የሚገኘውን ማስፈንጠሪያ በመክፈት ያመልክቱ፦

https://riftvalleyuniversity.org/2022/05/scholarship-opportunities/?noamp=available

@tikvahuniversity
16.5K views12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 11:32:53
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን አዲስ የተመደቡ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።

ዩኒቨርሲቲው የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ በደሴ እና በኮምቦልቻ ካምፓሶች ከግንቦት 21-23/2014 ዓ.ም (ግንቦት 23 በቅጣት) እንደሚከናወን መግለጹ ይታወቃል።

ዩኒቨርሲቲው በ2014 የትምህርት ዘመን 4 ሺህ የሚጠጉ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ተመድበውለታል።

@tikvahuniversity
17.8K views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 11:32:08
#FreelanceEthiopia

በትርፍ ሰዓትዎ ከሚሰርዋቸው ሥራዎች ጀምሮ እንደ ትምህርት ደርጃዎ፣ የሥራ ልምድዎ እና ፍላጎትዎ በሁሉም አይነት ዘርፎች ሁሉንም አይነት ሥራዎች በአንድ ቦታ ያገኛሉ።

ለመቀላቀል ተከታዩን ሊንክ ይጫኑ፦

https://t.me/+HZktkFNrwzg3Y2Fk
15.1K views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 11:16:56
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 'የቃልኪዳን ቤተሰብ' ፕሮጀክት

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ"አንድ ተማሪ አንድ ቤተሰብ" የቃልኪዳን ፕሮጀክት ከጀመረ ሦሥት ዓመታትን አስቆጥሯል።

"የቃልኪዳን ቤተሰብ" በመባል የሚታወቀው ፕሮጀክቱ፤ በዩኒቨርሲቲው አዲስ ገቢ ተማሪዎች እና በጎንደር ከተማ ነዋሪዎች መካከል ጥብቅ ትስስር የሚፈጥር ነው።

ፕሮጀክቱ ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች የእንግድነት ስሜት እንዳይኖራቸው እና የባህልና ቋንቋ ትስስርን ለማጠናከር ያግዛል ብለዋል።

በተማሪዎች እና በቃልኪዳን ቤተሰባቸው መካከል የትስስርና የቤተሰብነት የቃልኪዳን የስምምነት ፊርማ ይከናወናል።

የስምምነት ውሉ የሚደረገው በተማሪው እና ፍቃደኛ በሆነው ቤተሰብ መካከል ሲሆን በሦሥት ቅጅ ተሞልቶ አንዱ ቅጅ ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ሁለተኛው ቅጅ ለቃልኪዳን ቤተሰብ እንዲሁም ሦሥተኛው ቅጅ ለቃልኪዳን ተማሪ የሚሰጥ ነው።

ፕሮጀክቱ ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው ወቅት የብቸኝነት ስሜት እንዳይሰማቸው ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን ከ5 ሺህ 300 በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎች መቀበሉ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
16.4K viewsedited  08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 18:31:27
#የህግ_መውጫ_ፈተና

የ2014 ዓ.ም ብሔራዊ የህግ መውጫ ፈተና ከሰኔ 20 እስከ 24/2014 ዓ.ም ይሰጣል።

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ፈተናውን መውሰድ የምትፈልጉ ተማሪዎች እስከ ግንቦት 25/2014 ዓ.ም መመዝገብ ትችላላችሁ ብሏል።

( ለፈተናው የሚያስፈልጉና መሟላት ያለባቸው ጉዳዮች ዘርዝር ከላይ ተያይዟል። )

@tikvahuniversity
13.3K views15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 11:52:09
#JinkaUniversity

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ግንቦት 25 እና 26/2014 ዓ.ም እንደሆነ መግለጹ ይታወሳል።

ዩኒቨርሲቲው አዲስ ገቢ ተማሪዎች ባሉበት ሆነው የኦንላይን ምዝገባ ለማድረግ መከተል ያለባቸውን ሂደት ዘርዝሮ አስቀምጧል።

( ዝርዝር ሂደቱ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
16.6K views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 11:23:54
#ማስታወሻ
#ScholarshipTip

የህንድ መንግስት በ2022/23 ለ55 ኢትዮጵያዊያን ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥ አሳውቋል።

በህንድ ባህላዊ ግንኙነት ም/ቤት (ICCR) የቀረበው ነፃ የትምህርት ዕድሉ፤ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ድህረ ዶክትሬት የትምህርት ፕሮግራሞች የተካተቱበት ነው።

በህንድ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች/ተቋማት የሚሰጠው ዕድሉ፤ ከክፍያ ነፃ የትምህርት አገልግሎቶች እና ነፃ የአየር በረራ ትኬት ለአሸናፊዎች ያቀርባል።

አመልካቾች ዕድሚያቸው ከ18 እስከ 30 መሆን ያለበት ሲሆን እስከ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች/ተቋማት ማልከት እንደሚችሉም ተገልጿል።

የማመልከቻ ጊዜው ነገ ግንቦት 23/2014 ዓ.ም ያበቃል።

ለማመልከት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ፦

https://a2ascholarships.iccr.gov.in

@tikvahuniversity
16.5K views08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 11:21:51
#FreelanceEthiopia

በትርፍ ሰዓትዎ ከሚሰርዋቸው ሥራዎች ጀምሮ እንደ ትምህርት ደርጃዎ፣ የሥራ ልምድዎ እና ፍላጎትዎ በሁሉም አይነት ዘርፎች ሁሉንም አይነት ሥራዎች በአንድ ቦታ ያገኛሉ።

ለመቀላቀል ተከታዩን ሊንክ ይጫኑ፦

https://t.me/+HZktkFNrwzg3Y2Fk
14.8K views08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 16:45:27
#JimmaUniversity

በጅማ ዩኒቨርሲቲ በኦሮሞ ፎክሎር እና ስነ-ጽሁፍ፣ በሙዚቃ እንዲሁም በቪዥዋል አርት እና ቲያትር ጥበባት የትምህርትመስኮች በመደበኛ መርሃ ግብር ለመማር ያመለከታችሁ የመግቢያ ፈተና ግንቦት 25/2014 ዓ.ም እንደሚሰጥ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ፈተናው በተጠቀሰው ቀን በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ከጠዋቱ 3:00 እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ፈተናውን ለመውሰድ የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ዋናው ትራንስክሪፕት እና ማንነትን የሚገልጽ መታወቂያ ያስፈልጋል ተብሏል። (ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

ለፈተናው የተመረጡ አመልካቾች ዝርዝርን በተከታዩ የዩኒቨርሲቲው ሊንክ በመግባት መመልከት ይቻላል፦

https://www.facebook.com/JimmaUniv/

@tikvahuniversity
13.5K views13:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ