2022-06-01 11:09:57
#AASTU
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሀገረኛ የመጠጥ አይነቶችን በማዘመን ለገበያ ለማቅረብ እየሠሩ መሆናቸው ተገለጸ።
የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች "ማሬ ባህላዊ ጠጅ እና ጠላ መጠጦች አምራች ድርጅት" በሚል ስም ተደራጅተው በዘመናዊ መልኩ በላብራቶሪ የተሠራ ጠላ እና ጠጅ አምርተዋል፡፡
መጠጦቹ የጥራት ደረጃቸው ተወስኖ፤ የግብዓት አይነታቸውም በግልፅና በውል ታውቆ በዘመናዊ መልክ የተመረቱ መሆናቸው ተገልጿል።
ተማሪዎቹ ባደረጉት ጥናትና ምርምር ባህላዊው አዘገጃጀት የሚወስደውን የጊዜና የጉልበት መጠን በመቀነስ ከእጅ ንክኪ ነጻ በሆነ መልኩ ለማምረት የሚያስችል የሙከራ ጥናት አድርገዋል።
ሙከራው የምርቶቹ የመቆምጠጥ፣ ጌሾ የመብዛበት ወይም ቶሎ ያለመፍላት የጥራት ጉድለቶችን ያስቀራል ተብሏል።
በዚህም በየትኛውም ስፍራና በሁሉም የአይር ፀባይ በዕኩል ደረጃ ሊጠጣ የሚችልና ለረጅም ጊዜ ሊቆይ የሚችል ጠጅ እና ጠላ በማምረት ላይ ይገኛሉ፡፡
የኬሚካል ምህንድስና ተማሪዎች የሆኑት ኤርሚያስ ዋቅሹማ፣ ሀመረ ጋሻው፣ ማርታ ሳሙኤል እና ኬብሮን ግዛቸው በዘመናዊ መልክ የተመረቱትን ጠጅ እና ጠላን በቅርቡ ለገበያ እንደሚያቀርቡ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡
ፕሮጀክቱን ስኬታማ ለማድረግና ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ይደርስ ዘንድ የባለሀብቶች፣ የተቋማት፣ የመጠጥ ፋብሪካዎች እና ሌሎች ተባባሪ አካላት ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል።
ለማንኛውም ጥያቄዎችና አስተያየቶች በዩኒቨርሲቲው ኢሜል አድራሻ pir@aastu.edu.et መልዕክታችሁን ማድረስ ትችላላችሁ፡፡
@tikvahuniversity
14.4K views08:09