Get Mystery Box with random crypto!

#የመምህራን_የሙያ_ብቃት_ምዘና በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮ | Tikvah-University

#የመምህራን_የሙያ_ብቃት_ምዘና

በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች የሙያ ብቃት ምዘና የጽሑፍ ፈተና ተሰጥቷል።

ከ8 ሺህ 500 በላይ መምህራን የሙያ ብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበው የነበረ ቢሆንም የተጠበቀውን ያህል ተመዛኞች አልተገኙም ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በስምንት ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ት/ቤቶች ምዘናው እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል።

የምዘና ፈተናውን ወስደው ማለፍ ያልቻሉ እስከ ሦሥት ጊዜ መፈተን የሚችሉ ሲሆን ሦሥት ጊዜ ተፈትኖ ማለፍ ያልቻለ መምህር ከማስተማር ሥራ እንደሚገለል ባለስልጣኑ ያዘጋጀው መመሪያ ያዛል።

"የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የሌላቸው መምህራን ማስተማር እንደማይችሉ" መመሪያው ይገልጻል።

በአዲስ አበባ የመምህራን የብቃት ምዘና መሰጠት የተጀመረው በ2005 ዓ.ም ነበር።

@tikvahuniversity