2022-06-04 19:28:18
#KiburCollege
ክቡር ኮሌጅ በተለያዩ መስኮች በአጫጭር ስልጠና ያሰለጠናቸውን ከ310 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል።
ሠልጣኞቹ በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለመግባት ዝግጅት ላይ የሚገኙ ናቸው።
ከአዲስ አበባ እና ሰበታ ከተሞች ከሚገኙ የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከ500 በላይ ተማሪዎች በስልጠናው የተሳተፉ ሲሆን ከ310 በላዩ ስልጠናቸውን አጠናቅቀው የተሳትፎ ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።
ተማሪዎቹ ለቀጣይ ሙያቸውና ህይወታቸው አስፈላጊ የሆኑ ክህሎቶችን ያገኙበት መሆኑን የክቡር ኮሌጅ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ መኩሪያ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጸዋል።
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰትን ተከትሎ በቂ የትምህርት እገዛ እንዳልተደረገላቸው ያስታወሱት ሥራ አስኪያጁ፤ ስልጠናው በዚህ ረገድ ያለውን ክፍተት ለመሙላት የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም ከአንድ እስከ ሦሥት ሳምንት የቆዩ አጫጭር ስልጠናዎች በ12 የተለያዩ ዘርፎች እንደተሰጠ ገልጸዋል።
ከግንቦት 04/2014 ዓ.ም ጀምሮ በተሰጠው ነጻ የክህሎት ስልጠና፤ ተማሪዎቹ የህይወትና የቴክኖሎጂ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ ተደርጓል።
ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ምሁራን እና የፈጠራ ባለሙያዎች በማጠቃለያ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል።
@tikvahuniversity
11.2K views16:28