Get Mystery Box with random crypto!

Tikvah-University

የሰርጥ አድራሻ: @tikvahuniversity
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 213.59K

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-04-29 15:56:57
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3 እስከ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ሐምሌ 9 እስከ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል።

መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
20.2K views12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 15:21:44
"ትምህርት ለትውልድ" በተባለውና የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል በተጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ከ25.3 ቢሊየን ብር በላይ ሀብት መሰብሰቡን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

ባለፈው ዓመት መጨረሻ በተጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ፤ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አሰተዳደሮች ከ25.3 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ሀብት መሰብሰቡን በሚኒስቴሩ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገልፀዋል።

በ2016 ዓ.ም ብቻ በትምህርት ለትውልድ መርሐግብር ከ4 ሺህ በላይ አዳዲስ የቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡

የትምህርት ቤቶች ማሻሻያ እና ማስፋፊያ ሥራ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ለማጠናቀቅ እየተሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
21.4K views12:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 12:16:43
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በጌዴኦ ዞን ለሚገኙና ዘንድሮ የመልቀቂያ ፈተና ለሚወስዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ጀመረ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በበጎ ፍቃደኛ መምህራን በመታገዝ በተለያዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት የማስጀመሪያ መርሐግብር አከናውኗል፡፡

በጉዲኦ ዞን ከሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አምስት ትምህርት ቤቶች ላለፉት ሦስት ዓመታት አንድም ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ አለማሳለፋቸውን የዲላ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት እና ስነ-ባህሪ ተቋም ያደረገው ጥናት ያሳያል፡፡

በመሆኑም የማጠናከሪያ ትምህርቱ በጌዴኦ ዞን የሚታየውን ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር ማነስን ለማሻሻል ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

የማጠናከሪያ ትምህርቱ ለአንድ ወር ከአንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን፤ በተመረጡት ትምህርት ቤቶች አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
25.2K views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-28 14:55:16
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በክረምት የስልጠና መርሐግብር የሚሳተፉ ተማሪዎች ምዝገባ ጀምሯል።

እነማን ይመዘገባሉ?
የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች

የምዝገባ ጊዜ፦
ከሚያዝያ 17 እስከ ግንቦት 7/2016 ዓ.ም

ስልጠናው መቼ ይጀምራል?
ከሐምሌ 1 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም
(ለሁለት ወራት) (በሳምንት ለአራት ቀናት)

ስልጠናው ትኩረት የሚያደርግባቸው፦

➭ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሰረታውያን፣
➭ ሮቦቲክስ፣
➭ ፕሮግራሚንግ፣
➭ ማሽን ለርኒንግ እና ሌሎችም።

ምዝገባ የማድረጊያ አማራጮች፦

forms.gle/9B79pzGLdo84W2LY8

https://www.aii.et/summer-camp-registration-form-for-student/

@tikvahuniversity
31.7K views11:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-28 14:37:07
#ጥቆማ

በ Ethiopian Capital Market (ካፒታል ገበያ) የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ይሳተፉ!

መቼ?
ነገ ሰኞ ሚያዚያ 21/2016 ዓ.ም ጠዋት 2:30

የት?
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ

ስልጠናውን ማን ይሰጠዋል?
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለሙያዎች

@tikvahuniversity
27.5K views11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-28 14:26:34
#የቻናል_ጥቆማ

ለኢንጂነሪንግ ተማሪዎች እና Construction ዘርፍ ላይ ለተሰማራችሁ በሙሉ

የኮንስትራክሽን፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ የአርክቴክቸር ተማሪ ነዎት? በጠቅላላ ኮንስትራክሽን የተሰማሩ ባለሙያ ነዎት?

በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ የሌክቸር ትምህርቶች፣ መጻሕፍት፣ ቪዲዮዎች እና ጠቃሚ የኮንስትራክሽን ዕውቀት ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን!

ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣
አዲስ የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች፣
እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች፣
በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ሌክቸር የምታገኙበት፡፡

Join Us :-

on Telegram

https://t.me/ethioengineers1
https://t.me/ethioengineers1

on TikTok

tiktok.com/@ethiocons
tiktok.com/@ethiocons
26.8K views11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-27 21:55:43
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 154 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም የሰለጠኑ 110 እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን የተከታተሉ 44 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

በመጀመሪያ ዲግሪ ከተመረቁት መካከል107ቱ በጤና ሳይንስ የትምህርት መስኮች የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
33.9K views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-27 21:49:30
#HawassaUniversity

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የካንሰር ህክምና ማዕከል የፊታችን ሰኞ የጨረር ህክምና መስጠት ይጀምራል።

ማዕከሉ ለመጀመሪያ ዙር ፈቃደኛ ሆነው በተገኙ 30 ታካሚዎች ነው የጨረር ህክምና አገልግሎት መስጠት የሚጀምረው። #ኢፕድ

@tikvahethiopia
31.5K viewsedited  18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-27 19:32:13
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል።

በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ ሲሉ አሳውቀዋል።

ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፤ ፈተናው በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ብለዋል።

#MoE

@tikvahethiopia
26.2K views16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-27 13:00:40
#DebreBerhanUniversity

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በሥራ ገበታቸው ላይ ከታዩ አንድ ወር እንዳለፋቸው አል-ዐይን አማርኛ የተቋሙን አንድ አመራር በመጥቀስ ዘግቧል፡፡ ፕሬዝዳንቱ "የት እንዳሉ እንደማይታወቅ" ዘገባው ጠቅሷል፡፡

ከሦስት ዓመት በፊት የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በቢሯቸው ከታዩ አንድ ወር አልፏቸዋል ተብሏል።

"ፕሬዝዳንቱ ከመጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ. ም ጀምሮ በሥራ ላይ አይተናቸው አናውቅም" ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር ለአል-ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡

"ከተጠቀሰው ቀን አንስቶ ፕሬዝዳንቱ የት እንደሔዱና መቼ እንደሚመለሱ አናውቅም" ያሉት የተቋሙ አመራር፤ "ፕሬዝዳንቱ በቢሮ መታየት ካቆሙ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ባልታወቁ ኃይሎች መታገታቸውን ሰምተናል" ሲሉም አክለዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መሰወርን አስመልክቶ አል-ዐይን አማርኛ የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ፣ የሰሜን ሸዋ ኮማንድ ፖስት፣ ትምህርት ሚኒስቴር እና የደብረ ብረሃን ከተማ ፖሊስ ምላሽ እንዲሰጡ ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን ገልጿል። የፕሬዝዳንቱ ቤተሰብ ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጡ አል-ዐይን ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረትም አልተሳካም።

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትን በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው እንዲሁም ትምህርት ሚኒስቴር የሚሉትን ወደናንተ እናደርሳለን፡፡ #አልዐይንአማርኛ

@tikvahuniversity
15.8K views10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ